
20/05/2025
ይድረስ ለኢትዮዽያ ህዝብ
አንድ አንድ መረጃዎች እንደሚያመላክቱን በትምህርት ደረጃቸው ብቁ ያልሆኑ የጤና ባለሞያዎች አላግባብ በሆነ መንገድ ከጤና ጣቢያ ወደ ትልልቅ ሆስፒታል ተዘዋውረው እንዲሰሩ እየተደረጉ እንደሚገኙ ነው።
በዚህ መሀል ለሚፈጠረው የህክምና ስህተት ተጠያቂ የሚሆነው ማነው? አዘዋዋሪው አካል እንዲሁም ተዘዋዋሪው ባለሞያው ነዋ።
የአስተዳደር መግለጫዎች ሆስፒታል ያለምንም መስተጓጐል ስራ ቀጥሏል ይላሉ። የኢትዮዽያ ጤና ተቋሞች አደለም ይሄ ሁላ ባለሞያ ስራ አቁሞ በደህና ጊዜውም መስተጓጐል የወትሮ ልምዱ ነው ። ይሄን ደግሞ ሆስፒታል የታከመ፣ ሰው የጠየቀ ከምንም በላይ ደግሞ ሰው ያስታመመ ያውቀዋል። የውሸት መግለጫውን ለማን እንዳሰቡት ፈጣሪ ይወቀው። ነገሩን ያጤኑትም አይመስል።
የላቤን ላግኝ ፣ ልጆቼን ላስተምር ፣ ተቋሙ ይሟላ ፣ በስራ ቦታዬ ደህንነቴ ይጠበቅልኝ ያለን ባለሞያ ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ እንደምትመለከቱት ነገሩን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እየወሰዱትም ይገኛሉ።
የኢትዩዽያ ህዝብ ሆይ በሀገራችሁ በተሟላ ተቋም እና በብቁ የጤና ባለሞያ የመታከም መብት አላችሁ!! በዚህ ሰሞን የጤና ባለሞያ አለ ብሎ የተቀበላችሁ ማንኛውም የመንግስት ሆስፒታል ውስጥ የሚሰራ ማንኛውም የጤና ባለሞያ አቅጣጫ እንኳን በቅጡ ማመላከት ካልቻለ “ለመሆኑ እዚህ ነው የምትሰራው?” ብለህ ጠይቀው ። አካባቢህ ላለ ሌላ የሆስፒታል ተጠቃሚም አሳውቅ ። የጤና ባለሞያውን አሰራር እና ተግባር በህብረት በማድፈጥ ተከታተሉ። ለሚፈጠር ማንኛውም የህክምና ስህተት ተጠያቂ ይሆናልና የፎቶም መረጃ ያዙ!!
ስነምግባር ጠፍቷልና ብቻህን አትጋፈጥ። አብሮህ ካለው ሰው ጋር በህብረት ተረጋግተህ መብትህን ጠይቅ። በሆስፒታል ጥበቃም አካላዊ እርምጃ ከተወሰደ የቪዲዮ ማስረጃ ሰብስቡ!!
ለተፈጠረባችሁ እንግልት ከልብ እናዝናለን። ከፈጣሪ ጋር በቅርብ ጊዜ በተሻሻለ የህክምና ስርዐት ዳግመኛ እንገናኛለን!!
Share Share Share‼️
©️EHPM
BBC News Amharic ARSI POST