
18/03/2025
የመኑ ታጣቂ ቡድን ሃውቲ በአሜሪካ የጦር መርከብ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገለጸ።
ጥቃቱ 53 የመናውያን ለሞቱበት የቅዳሜው የአሜሪካ የአየር ድብደባ አጻፋ መሆኑንም ነው ያስታወቀው።
በኢራን ድጋፍ እንደሚደረግለት የሚታመነው ሃውቲ ባወጣው መግለጫ በቀይ ባህር በምትገኘውና አውሮፕላን ተሸካሚዋ "ዩኤስኤስ ሃሪ ቱርማን" መርከብ ላይ በ24 ስአት ውስጥ ሁለት ጊዜ ጥቃት ማድረሱን ጠቁሟል።
ቡድኑ በመርከቧ ላይ ጥቃት ለማድረስ 18 ሚሳኤሎችና ድሮኖች መጠቀሙን ያስታወቀ ሲሆን፥ ዋሽንግተንም በየመን የአየር ጥቃቷን መቀጠሏ ተገልጿል።
ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://bit.ly/4bv1tb7