Wedaje Asif Multimedia Production

Wedaje Asif Multimedia Production ህይወት ባማረ ጎዳና

ጠብታን በአዳማ    በኦልያድ አዳራሽ / #ማለዳ 2 ሰዓትይህንን ፖስት ሁላችሁም ሼር በማድረግለፕሮግራሙ ተደራሽነት አግዙን!ለበለጠ መረጃ:- 0913514352 – 0927986637
24/08/2022

ጠብታን በአዳማ
በኦልያድ አዳራሽ / #ማለዳ 2 ሰዓት

ይህንን ፖስት ሁላችሁም ሼር በማድረግ
ለፕሮግራሙ ተደራሽነት አግዙን!

ለበለጠ መረጃ:- 0913514352 – 0927986637

 #ጠብታ የመጀመሪያ ዙር መድረክ  በአዳማ ከተማ | በአዲስ መሰናዶእሁድ ነሐሴ 22 | ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ       ለስኬታማ ትውልድ   መኖሩ አስፈላጊ ነው! ! #እንዳያመልጥዎ
11/07/2022

#ጠብታ የመጀመሪያ ዙር መድረክ
በአዳማ ከተማ | በአዲስ መሰናዶ

እሁድ ነሐሴ 22 | ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ


ለስኬታማ ትውልድ መኖሩ አስፈላጊ ነው!
!

#እንዳያመልጥዎ

04/07/2022

ሀራም የሆነ ፍቅር ልክ ! ምንም ያክል
ከርሱ ብትጠጣ አያስደስትህም!
እንዲያውም ጥማትህን ይጨምረዋል። ! አሚን!

03/07/2022

ውድ ከረዥም መጠፋፋት ጊዜ በኋላ ተመልሰናል! አዳዲስ ጉዳዮችን ይጠብቁን

ሂጃብ የነፃነት ማወጃ መሳሪያ ነው!በ አኪፍ ጃፍሪረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ተሳትፈውበት በነበረ አንድ ጦርነት ላይ አንዲት ሰሀባ ልጇ ተገደለባት፡፡ የልጇን ሸሂድነት የሰማችው እናት ይህንኑ ለማረጋገ...
03/07/2022

ሂጃብ የነፃነት ማወጃ መሳሪያ ነው!
በ አኪፍ ጃፍሪ
ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ተሳትፈውበት በነበረ አንድ ጦርነት ላይ አንዲት ሰሀባ ልጇ ተገደለባት፡፡ የልጇን ሸሂድነት የሰማችው እናት ይህንኑ ለማረጋገጥ በጅሃድ ላይ ወደ ወደቁት የሸሂዶች ሜዳ አመራች፡፡ ሰሃቢቷ ሂጃብ በወጉ ለብሳ ኒቃብም ተሸፍና ነበር፡፡ ይህን የተመለከቱ ሰዎች ‹‹እንዲህ ለብሰሽና ተሸፍነሽ ከዚህ ሁሉ ሬሳ መሃል ልጅሽን እንዴት ልትለይ ነው?›› አሏት፡፡ ሰሃቢቷም ስትመልስ ‹‹አላህ (ሱ.ወ) በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አማካይነት የነብዩ ሚስቶች ልጆቻቸውንና ምዕመናን ሴቶች መከናነቢያቸውን በላያቸው ላይ ለቀቅ እንዲያደርጉ አዟል፡፡ እኔ በደረጃ ከነብዩ ሚስቶች፣ ልጆቸውና ከምዕመናን ሴቶችም በታች ነኝ ወላሂ ልብሴንና ሃያዔን ከማጣ ልጄ ቢጠፋ ይሻላል አለቻቸው፡፡
አዎን! ሂጃብ አንዲት ሴት ሀያዋን የምትገልፅበት እንዲሁም ነፃነቷን የምታውጅበት መሳሪያ ነው፡፡ አሰ-ሰዒድ የተባሉ ሰው ‹‹አንዳንድ ምግባረ ብልሹ ሰዎች በተለይ ጨለማ በሚሆንበት ጊዜ ሴቶችን እየጠበቁ ይደፍሩ ነበር፡፡ አንዲት ሴት ሂጃብ አድርጋ ካያት ‹‹ይቺ ሴት ጨዋናት›› በማለት አይተናኮሏትም ነገር ግን ሂጃብ የሌላት ሴት ካጋጠመቻቸው ‹‹ይህቺ ባሪያ ነች›› በማለት ይዘው ያስጨንቋታል፡፡ብለዋል፡፡
ሰዎች በጨዋነትና ንፅህናቸውን ሳያሳድፉ ለመኖር የሚያደርጉትን ጥረት አፈር ድሜ ለማብላት እና መንፈሳዊ ህይወታቸውን ለመመሰቃቀል ሌት ተቀን ይማይተኙ ጠላቶች እንዳሏቸው ህይወታቸውን ለማመሰቃቀል ቅጥያዎችና የእርሱ ሥራ አስፈፃሚዎች ለመሆን በወንዶች እና በሴቶች መካከል ሲኖር የሚገባውን ጤናማ የሆነ ፆታዊ መስተጋብር እንደሁም ሁለንተናዊ ክብር በማውደም ተግባር ላይ መሰማራታቸው እውነት ነው፡፡ የሴጣንን እርምጃዎች የሚከተሉት ህዝቦች ዓይናቸውን በጨው የታጠቡ ለሴት ልጅ ተቆርቋሪ ነኝ ባዮች ይህንን ስውር የሆነ ፀረ ኢስላም የሆነ አቋማቸውን የሚያራምዱት በደልን በመዋጋት ዙሪያ ጥምጥም ሄደው ሴት ልጅ ሂጃቧን አውልቃ ውብ ገላዋን ለውበት አድናቂዎች ብታጋልጥም እንዲሁ የሰውነት አቋማን የሚያሳዩ አልባሳት ብትጠቀም ማራኪ እንደምትሆን ድርቅ ብለው በመስበክ ነው፡፡ እነዚህን ሰይጣናዊ መንገዶቻቸው ውስጥ ዋነኛውና የመጀመሪያ ስልቱ ጨዋነቷን የሚያሳዩ አልባሳቷን አውልቃ በምትኩ ወደ ውርደት የሚያሽቀነጥሯትን ብጭቅጫቂ ልብሶች እንድትለብስ በመጎትጎት ነው፡፡ በመሆኑም ብዙ ሴቶች ይህንን የሴጣን ጥሪ ተቀብለው የዕውር ድንብራቸውን የመጓዝ የዘመናዊዎችን ፋሽኖችንና ሞዴሊስቶች የአኗኗር ዘይቤ ለመኮረጅና እነርሱን ለመመስል ሲማስኑ ይታያል፡፡ እንዲህ አይነቱ ህብረተሰብ ከሃይማኖት ተጽእኖ በራቀና ፍጹም ዓላማዊ በሆነ ሞራላዊ አልባ የህይወት ጉዞ የሚነጉድ እንደሆነ ገሃድ ነው፡፡
አላህ ሱ.ወ በሀዲሰል ቁዱሱ እንዲህ ሲል ይናገራል {አንተ ነብይ ሆይ! ለሚስቶችህ ለሴት ልጆችህም ለምዕመናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው ላይ በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው ይህ እንዲታወቁ እና በባለጌዎች እንዳይደፈሩ ለመሆኑ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሃሪ አዛኝ ነው፡፡} {አል-ቁርዓን}

03/07/2022

ዙልሂጃ 4
ሱብሀነላህ ወልሀምዱሊላህ ወላኢላሀኢለላህ ወላሁአክበር

 የአራሂሙን በጎ አድራጎት ድርጅት           የማዕከል ምርቃት #ቦታ በአዳማ ከተማ 11 ቀበሌ ከአይሻ መስጂድ50 ሜትር ከፍ ብሎ! #ቀንእሁድ ጥቅምት 21/2014ዓ.ል #ሰዓትከጠዋቱ 2:...
22/10/2021


የአራሂሙን በጎ አድራጎት ድርጅት
የማዕከል ምርቃት

#ቦታ
በአዳማ ከተማ 11 ቀበሌ ከአይሻ መስጂድ
50 ሜትር ከፍ ብሎ!

#ቀን
እሁድ ጥቅምት 21/2014ዓ.ል

#ሰዓት
ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ


1. ዶ/ር ሙሐመድ ዘይን
2. ኡስታዝ ኢንጅነር በድሩ ሁሴን
3. ሸይኽ አሚን ኢብሮ
4. ወ/ሮ ሀናን ማህሙድ( )
5. ሙንሺድ አሊ አሚን
6. ዶ/ር ጅብሪል ቀመር
7. ሸይኽ አብደላህ ኢድሪስ #ይገኙበታል!

በተጨማሪም የሀይማኖት አባቶች እና የመንግስት
ከፍተኛ ባለስልጣናትም የሚገኙበት ይሆናል::

!

 !★★★★★★አንዲት ጥቁር እና መርዘኛ እባብ እሳት ውስጥ ገብታ ስትቃጠል አንድ ልበ መልካም ወጣት በደመነፍስ በእጁ ከእሳቱ ጎትቶ ያወጣታል። በዚህ መሃል ይህች እባብ ያንን ልበ መልካም ወጣ...
28/09/2021

!
★★★★★★

አንዲት ጥቁር እና መርዘኛ እባብ እሳት ውስጥ ገብታ ስትቃጠል አንድ ልበ መልካም ወጣት በደመነፍስ በእጁ ከእሳቱ ጎትቶ ያወጣታል። በዚህ መሃል ይህች እባብ ያንን ልበ መልካም ወጣት ትነድፈዋለች። እሱም በድንጋጤ መልሶ ወደ እሳቱ ይወረውራታል። እባቧ ከእሳቱ ለማምለጥ መወራጨት ስትጀምር አሁንም ያ ወጣት በማዘን በአካባቢው ባገኘው ረዘም ያለ ዘንግ እባቧን መልሶ ያወጣታል።

ይህን ክስተት በቅርብ ርቀት ይመለከት የነበረ አንድ ግለሰብ ወጣቱን ይጠይቀዋል፤ "ወዳጄ ሆይ አንተ ልትረዳት ስፈልግ በአፀፋው እባቧ ነደፈችህ፤ አንተ ግን አሁንም መልሰህ እሷን ለመርዳት ትታገላለህ። ጎድታህ የለ ለምን እንድትቃጠል አልተውካትም?"

ልበ ቀናው ወጣትም "ልክ ነህ ወዳጄ እንዳልከው እባቧ ልረዳት ስፈልግ ነድፋኛለች፤ ነገር ግን ይህን ያደረገችው መናደፍ ተፈጥሯዊ ባህሪዋ ስለሆነ ነው። እኔም እየነደፈችኝም ቢሆን የምረዳት የተቸገረን መርዳት ባህሪዬ ስለሆነ ነው። የእባቧ መናደፍ መልካምነቴን እንዲቀይር አልፈቅም።"
★★★★★★

ሰዎች አንተ ላይ በሚፈፅሙት ያልተገባ ተግባር ምክንያት መልካምነትህን መቀየር ከጥበብ አይደለም። ባይሆን !

አንብበው ሲጨርሱ ላይ ሰለዋት ያውርዱ!

!
Ayub Adem

27/04/2021

❗️ሰበር ዜና



የመጀመሪያው እስላማዊ ወጣቶች ማዕከል እና ቤተመፅሀፍት

ከ 7 አመታት በላይ በአክፍሮት ሀይላት እጅ የነበረውን ቤተ-መፅሀፍት በእጃችን ለማስገባት ጥቂት ጊዜያቶች ቀሩን

አልሃምዱሊላህ ከብዙ አመታቶች በኋላ በሁሉም ተማሪዎች ልብ ውስጥ እንደ ቁጭት እና ምኞት ሲነሳ የነበረውን '' የሙስሊም ወጣቶች እስላማዊ ማዕከል '' በአላህ ፍቃድ ለአዳማ ህዝብ እውን ሊሆን 2 ወራቶች ብቻ ቀሩት።

እናም ይህንን ስራ እውን ለማድረግ ብዙ ጥረት ያደረግን ሲሆን ከብዙ ጥረት በኋላ በእጃችን የገባ ሲሆን ይህንን ቦታ የ6 ወር ቅድመ ክፍያ ከፍሎ ለመረከብ እና አንዳንድ የላይብረሪ ቁሳቁሶችን ለማሟላት 75,000 ብር ብቻ ስላስፈለገን በዚህ ሰደቀቱል ጃሪያ ስራ ላይ የበኩልትን አሻራ ይጣሉ።
ለዚህ ታላቅ አሻራ 100ብር ብቻ የሚሰጠን 750 ሰው እንፈልጋለን።
በዚህ እስላማዊ ማዕከል የበለጠ ተጠቃሚ ሚሆኑት

👉የቲሞች እና መሳኪኖች
👉ህፃናት እና ሴቶች
👉የከተማው ሙስሊም ተማሪዎች በመሆኑ የዚህ ኸይር ስራ ተቋዳሽ ይሁኑ
ለበለጠ መረጃ :- 09 88 96 75 45 / 09 34 13 32 37 ደውለው ያነጋግሩን።

📮የባንክ አካውንት ቁጥር

🔻1000 3095 47431

👉ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

02/04/2021


!

#ፕሮፋይል #ሼር ያድርጉ!

Address

Adama

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wedaje Asif Multimedia Production posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wedaje Asif Multimedia Production:

Share