OBN አማርኛ +

OBN አማርኛ + OBN (Oromia Broadcasting Network)
Voice of The People.

05/12/2024

Hidha Haaromsaa guddichaafii Paan Afriikaanizimii

14/07/2024
የፊንፊኔ ከተማ  የኮሪደር ልማት ስፋት እና ይዘት አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል ነው:- የፊንፊኔ ከተማ  ከንቲባ ጽሕፈት ቤትበኮሪደር ልማት ስራዎች ከተሰሩት መካከል:-1. የመንገድ መሰረተ...
03/07/2024

የፊንፊኔ ከተማ የኮሪደር ልማት ስፋት እና ይዘት አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል ነው:- የፊንፊኔ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት

በኮሪደር ልማት ስራዎች ከተሰሩት መካከል:-
1. የመንገድ መሰረተ ልማቶች
• ከ48 ኪ.ሜ በላይ የተሽከርካሪ መንገድ፣
• ከ96 ኪሎ ሜትር በላይ ሰፋፊ የእግረኛ መንገድ በግራና በቀኝ ተሰርቷል
• 100 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገድ፣
• 4 የመሬት ውስጥ የእግረኛ (underpass) መንገዶች፣
• 5 ኪ.ሜ የመሮጫ ትራክ፣
• ⁠2 ትልልቅ የተሽከርካሪ ድልድዮች፣
• ⁠3 ዘመናዊ የእግረኛ ድልድዮች፣
• አጠቃላይ ከ240 ኪ.ሜ በላይ መንገድና ተያያዥ መሠረተልማቶች፣
2. የትራንስፖርት ስርዓት
• በአንድ ጊዜ 6,369 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችሉ 32 ዘመናዊ ፓርኪንጎች (ከዜሮ ወለል እስከ ሶስት ቤዝሜንት ያላቸው)፣
• በአንድ ጊዜ 517 ተሸከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም የሚያስችሉ 9 የባስ እና ታክሲ ተርሚናሎች፣
• በአንድ ጊዜ 268 ባሶችንና ታክሲዎችን ለአጭር ጊዜ የመጫንና ማውረድ አገልግሎት የሚሰጡ 85 የመንገድ ዳር የባስና ታክሲ ቤይ፣
• 50 ኪሎ ሜትር የትራንስፖርት ደህንነት ማረጋገጥ የሚያስችል የብልህ (ITS) ስርዓት።
3. የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስራዎች ፦
• 430 ዘመናዊ ስማርት ፖሎች (ስክሪንና ዘመናዊ የደህንነትካሜራዎች ያሉት)
• ከተማችን የደህንነት ካሜራዎች ባለቤት እንድትሆን 48 ኪሎ ሜትር የስርዓት ዝርጋታ
• 1,582 መደበኛ የመንገድ መብራቶች (Normal street lights)
• ከ96 ኪሎ ሜትር በላይ የአደጋ መንስዔ የሆኑ ያረጁና እንደሸረሪት ድር የተተበተቡ የኤሌክትሪክ መስመሮች እና ፖሎችን አንስቶ ወደ ምድር ውስጥ የመቅበር ስራ (ከ96 ኪሎ ሜትር በላይ ተከናውኗል)
4. የህዝብ መዝናኛዎችና ማረፊያዎች መስፋፋት
• 32 የውሃ ፏፏቴዎች፣
• 20 ሄክታር የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ መልሶ ማልማት ስራዎች 8 ወንዞች በተቀናጀ መልኩ እየለሙ ይገኛሉ፡፡
• 120 ዘመናዊ የመንገድ ዳር የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች (Public toilets) ፣
• 50 ሄክታር በላይ የከተማ አረንጓዴ ልማት ስራዎች፣
• 70 የህዝብ መናፈሻ ስፍሪዎች እና የፈጣን ምግብ አገልግሎት መሸጫ ቦታዎች
5. የውሃና ፍሳሽ ማስወገጃ ሥራዎች
• 48 ኪ/ሜ የጎርፍ ማስወገጃ ስርዓት ዝርጋታ
• ከ17.8 ኪ.ሜ በላይ አዲስ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች ዝርጋታ፣
• ከ69 ኪ.ሜ በላይ (6 ኪሎ ሜትር ከፍተኛ የውሃ ማሰራጫ መስመር እና 63 ኪሎ ሜትር መለስተኛ የውሃ ማሰራጫመስመር) ዝርጋታ፣
• ለእሳትና ድንገተኛ አደጋ መቆጣጠሪያ አገልግሎት የሚውል ባለ 110 ሚሊ ሜትር HDPE የቧንቧ ዝርጋታን ተከትሎ 71 የፋየርሃይድራንት (Fire Hydrant) ደረጃ መትከል
6. የቴሌኮሚኒኬሽን መሰረተ ልማት ስራዎችን በተመለከተ
• ከ70 ኪሎ ሜትር በላይ የቴሌኮም ግንባታ ዳክት፣
• 75 ኪሎ ሜትር የመዳብ ኬብል ዝርጋታ፣
• 152 ኪሎ ሜትር የፋይበር ኬቢል አዘዋውሮ የመዘርጋት ስራ፣
• 57 የኔትዎርክ ማከፋፈያ ሳጥኖች ተከላ፣
• 1,627 ምሰሶዎች ተከላ፣
ምንጭ፡- የፊንፊኔ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን የሚያገናኝ የ220 ኪሎ ሜትር መንገድ ሊገነባ ነው ኦቢኤን ሰኔ 20/2016-ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን እ.ኤ.አ በግንቦት 2023 የተፈራረሙትን የ738 ሚሊዮን ዶ...
27/06/2024

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን የሚያገናኝ የ220 ኪሎ ሜትር መንገድ ሊገነባ ነው

ኦቢኤን ሰኔ 20/2016-ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን እ.ኤ.አ በግንቦት 2023 የተፈራረሙትን የ738 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ስምምነት ተከትሎ ሁለቱን ሀገራት የሚያገናኝ 220 ኪሎ ሜትር መንገድ ሊገነቡ ነው።

የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ የሽግግር ህግ አውጪ ምክር ቤት የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን ድንበር ተሻጋሪ መንገድ ለመገንባት የተፈረመውን የገንዘብ ስምምነት አጽድቋል።

ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል እያደገ ያለውን ትብብር እና የጋራ ተጠቃሚነት ግንኙነት በማሳየት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ያለመ ነው።

ስምምነቱ በጉባዔው በሙሉ ድምጽ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ለፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የመጨረሻ ፍቃድ መቅረቡን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

13/06/2024

ለሳፋሪ አገልግሎት ተሽከርካሪነት ሀገር ውስጥ የተቀየሩ ባለአንድ ጋቢና ፒክ

ቱሪዝም በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም ቅድሚያ ከተሰጣቸው ዘርፎች አንዱ እንደመሆኑ መሰረተ ልማትን እና አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ብሎም በዘርፉ ልምድን ማዳበር ቁልፍ የትኩረት አ...
13/06/2024

ቱሪዝም በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም ቅድሚያ ከተሰጣቸው ዘርፎች አንዱ እንደመሆኑ መሰረተ ልማትን እና አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ብሎም በዘርፉ ልምድን ማዳበር ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫ ነው። ብዛት ያላቸው ብሔራዊ ፓርኮች እና የዱር እንስሳት ሃብት ባላት ሀገራችን የሳፋሪ ልምምድን ማስፋፋት ቱሪስቶችን ለመሳብ ወሳኝ ተግባር ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በየካቲት 2016 የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ100 ቀናት ግምገማ ወቅት ለቱሪዝም አገልግሎት የሚሰጡ የሳፋሪ ተሽከርካሪዎች እንዲመረቱ ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሰጡትን አቅጣጫ ተከትሎ ኢንደስትሪ ሚኒስቴር በሀገር ውስጥ ለሳፋሪ አገልግሎት ተሽከርካሪነት የተቀየሩ ባለአንድ ጋቢና ፒክ አፕ መኪናዎችን በናሙናነት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስረክቧል። መኪናዎቹን ለሳፋሪ አገልግሎት እንዲመቹ አድርጎ በመለወጥ ሂደት ውስጥ አምራቾች በሀገር ውስጥ በስፋት የመለወጥ ልምድ እና አቅም ለማዳበር ችለዋል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት በምርት ስራው የተሳተፉና አቅም ያላቸው አምራቾች የምርት ስራውን ሂደት እንዲያስፋፉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

Address

Adama
2919

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when OBN አማርኛ + posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share