Ermias Ze Anathoth

Ermias Ze Anathoth Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ermias Ze Anathoth, Digital creator, Addis Ababa.

ገብረ ሥላሴ፤ የሥላሴ ባሪያ

ꍟꂦ꓄ꉓ ✝️ - ȶɦɛ ȶʀʊɛ քǟȶɦ օʄ ʟɨɢɦȶ

ወለነሰ ተሣየጠነ ክርስቶስ እመርገማ ለኦሪት በዘወድአ በእንቲአነ ወጾረ መርገማ እስመ ከመዝ ይቤ መጽሐፍ “ርጉም ውእቱ ኵሉ ዘስቁል ዲበ ዕፅ።” ገላ ፫፥፲፫

“በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን” ገላትያ 3፥13

"... ፍጡነ ይርከበነ ሣህልከ እግዚኦ፤ አቤቱ ይቅርታህ ፈጥኖ ይደረግልን" ቅ.ዲዮስቆሮስ ቁ-፸ተገድሎ የማያልቀው ሕዝብ ዛሬም በአርሲ መከራና ስቃይ ውስጥ ይገኛል። አቤቱ ጌታ ሆይ ማረን 😢
09/11/2025

"... ፍጡነ ይርከበነ ሣህልከ እግዚኦ፤ አቤቱ ይቅርታህ ፈጥኖ ይደረግልን" ቅ.ዲዮስቆሮስ ቁ-፸

ተገድሎ የማያልቀው ሕዝብ ዛሬም በአርሲ መከራና ስቃይ ውስጥ ይገኛል።

አቤቱ ጌታ ሆይ ማረን 😢

08/11/2025

"ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ይህች ሰንበት የመከራችን ፍጻሜ ትሆን ዘንድ ለምኚልን።" 🌹

ሰላም ሰላም ለልደትከ እንግዳእምነ ማርያም ድንግል ውስተ ቤተልሔም ዘይሁዳሠራዬ ኃጢአት ክርስቶስ ወመቅለሌ ዕፁብ ዕዳልደትከ ሶበ ተሰምዐ ለኢየሩሳሌም በዐውዳሰብዓ ጢሮስ ለንግሥከ አወፈዩ ጋዳ ...
07/11/2025

ሰላም ሰላም ለልደትከ እንግዳ
እምነ ማርያም ድንግል ውስተ ቤተልሔም ዘይሁዳ
ሠራዬ ኃጢአት ክርስቶስ ወመቅለሌ ዕፁብ ዕዳ
ልደትከ ሶበ ተሰምዐ ለኢየሩሳሌም በዐውዳ
ሰብዓ ጢሮስ ለንግሥከ አወፈዩ ጋዳ

ተዝካረ ልደቱ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ

እንኳን አደረሰን !

… ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥ እጅግ ተቸግረናልና። 💔😢🥺
05/11/2025

… ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥ እጅግ ተቸግረናልና። 💔😢🥺

“የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የጻድቃንህንም ሥራ ለምድር አራዊት፤” መዝሙር 79፥2

…. ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥ እጅግ ተቸግረናልና።

"አሳዳጆቻችን በአንገታችን ላይ ናቸው፤ እኛ ደክመናል ዕረፍትም የለንም።" ሰቆ ኤርምያስ 5:5
04/11/2025

"አሳዳጆቻችን በአንገታችን ላይ ናቸው፤ እኛ ደክመናል ዕረፍትም የለንም።" ሰቆ ኤርምያስ 5:5

ሰላም ዕብል ለአክናፊከ ስድስቱ፤ዘመንገለ የማን ሠለስቱ፤ወመንገለ ፀጋም ሠለስቱ ተክለሃይማኖት ወልድከ በረከተከ ይፈቱ፤ሶበ ኀሠሠከ ጊዜ ኀደጎ ዕለቱ፤ለረድኤቱ ክንፈከ አስተፋጥን ሎቱ።እናንተ የ...
02/11/2025

ሰላም ዕብል ለአክናፊከ ስድስቱ፤
ዘመንገለ የማን ሠለስቱ፤
ወመንገለ ፀጋም ሠለስቱ ተክለሃይማኖት ወልድከ በረከተከ ይፈቱ፤
ሶበ ኀሠሠከ ጊዜ ኀደጎ ዕለቱ፤
ለረድኤቱ ክንፈከ አስተፋጥን ሎቱ።

እናንተ የምድር ጨው ናችሁ (ማቴ 5፥13) እንዳለ ጌታ ዓለምን ካለማመን ወደ ማመን የመለሱ ሐዲስ ሐዋርያ የጣዖታትን ቤት በቃለ እግዚአብሔር መዶሻ ያፈረሱ አቢያተ ክርስቲያናትን በወንጌል መሠረት ያነፁ ቅዱስ አባታችን ተክለሃይማኖት ረድኤት በረከታቸው አይለየን !

የጻድቁ በረከት ይጠብቀን

💚💛❤ አሜን 💚💛❤

ማኅበረ ሐዋርያት ሰባክያን ….
02/11/2025

ማኅበረ ሐዋርያት ሰባክያን ….

ማኅበሩ በዛሬው ዕለት ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ለ 2018 ዓ.ም ሐምሌ ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማክበሪያ ከአባላቱ መሰብሰብ ችሏል !

ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም

ማኅበረ ዲያቆናት ዘሽሮሜዳ ሥላሴ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 7ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በተለያዩ የቤተ ክርስቲያናችን የአገልግሎት ጉዳዮች ላይ መክሯል።

በዚህም በገጠራማ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የተቸገሩ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲሁም የአብነት ትምህርት ቤቶችን ከዚህ ቀደሙ በተሻለ ሁኔታ መደገፍ የሚችልበትን አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ለሚያገለግሉ አንድ የአብነት መምህር የአንድ ዓመት ደመወዝ አጽድቋል።

ማኅበራችን በ 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት በደብራችን የአብነት ትምህርት ቤት ለማስገንባት ብዙ እንቅስቃሴዎችን ያደረገ ቢሆንም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ዕቅዱን ሳያሳካ ቀርቷልተ

እንደሚታወቀው ከ 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በደብራችን መከበር በተጀመረው የሐምሌ ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማኅበሩ ታላላቅ የአብነት መምህራንን በመጋበዝ ሥርዓተ ማኅሌቱ ይትበሃሉን ጠብቆ በታላቅ ድምቀት እንዲከበር በኃላፊነት ሲሠራ ቆይቷል።

በዛሬው ዕለትም ለሐምሌ 2018 ዓ.ም ቅዱስ ገብርኤል በዓል ማክበሪያ ከአባላቱ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ለማግኘት ተችሏል።

ኢንኅድግ ማኅበረነ !

29/10/2025

“ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፥ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን።” ሮሜ ፰፥፴፮

በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ ፲፬ ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸው ተሰምቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዝተን እየተለማመድነው የመጣነው የኦርቶዶክሳውያን ሞት ሊበቃ እና የሰው ልጆች ሁሉ የመኖር ሰብዓዊ መብት ሊረጋገጥ ይገባል።

በአካባቢው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በተደጋጋሚ በአማኙ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት ሊያስቆሙ እና መፍትሔ ሊያበጁለት ይገባል።

ለወደፊቱም ቢሆን እንደ ቤተ ክርስቲያን የሚጠበቁብንን በርካታ ሥራዎች አለመሥራታችን ትውልዱን ዋጋ እያስከፈለው እንዳይኖር ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ መሥራት የሚገባን አያሌ ተግባራት መኖራቸውን መዘንጋት የለብንም።

በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን ዕረፍተ ነፍስን ያድልልን፤ ለቤተሰቦቻቸው አጽናኝ ቅዱስ መንፈስን ይላክላቸው።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !

19/10/2025

የሰላምና የፍቅር ተምሳሌት በነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ሕልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን።

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ሀገር ወዳድ፤ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት መገለጫ ተወዳጅ የኢትዮጵያውያን አባት ነበሩ። በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ዕረፍት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለኢትዮጵያውያን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።

"ነገር ግን አውሬው ተያዘ" ራዕ 19፥20በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የጥላቻ ንግግር በግል የማኅበራዊ ገጽ ላይ ሲለጥፍ የቆየው ግለሰብ በእስር ተቀጣ ! የኢሉ አባ ቦር ዞን፣ ሁ...
08/10/2025

"ነገር ግን አውሬው ተያዘ" ራዕ 19፥20

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የጥላቻ ንግግር በግል የማኅበራዊ ገጽ ላይ ሲለጥፍ የቆየው ግለሰብ በእስር ተቀጣ !

የኢሉ አባ ቦር ዞን፣ ሁሩሙ ወረዳ ፍርድ ቤት በግል የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን በሚመለከት የጥላቻ ንግግር እና የሐሰት መረጃዎችን ሲያሰራጭ በነበረ ግለሰብ ላይ የ 1 ዓመት ከ 6 ወር እስራት ወስኗል ።

ዘገባው የ TMC ነው።

06/10/2025

ለተአምርኪ አሐሊ እሙ ፤
ማኅሌተ ጽጌ ዘይሰመይ ስሙ።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251910193560

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ermias Ze Anathoth posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ermias Ze Anathoth:

Share