Kal Sports

Kal Sports Sports-related content in one place

26/11/2025

በኢስቴቫኦ ዊልያን የተጸጸተው ሪያልማድሪድ

24/11/2025

“ራይስ ትልቅ መሪ ነው” ቡካዮ ሳካ

ወሳኝ ጨዋታ የሚጠብቀው ማንችስተር ዩናይትድበእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሀግብር የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ ኦልድትራፎርድ ላይ በማንችስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን መካከል ሲደረግ ቀያይ...
24/11/2025

ወሳኝ ጨዋታ የሚጠብቀው ማንችስተር ዩናይትድ

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት መርሀግብር የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ ኦልድትራፎርድ ላይ በማንችስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን መካከል ሲደረግ ቀያይ ሰይጣኖቹ ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻሉ 3ኛ ላይ ከሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ 1 ማጥበብ ይችላሉ፡፡

በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በተካሄዱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የለንደኖቹ ክለቦች አርሰናል እና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ወሳኝ 3 ነጥብ ሲያሳኩ ማንችስተር ሲቲ እና ሊቨርፑል ደግሞ ባልተጠበቀ መልኩ ሽንፈት ገጥሟቸዋል፡፡

ዛሬ ምሽት 5፡00 ላይ የ12ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ሲደረግ ማንችስተር ዩናይትድ የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተንን ያስተናግዳል፡፡

አሁን ላይ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 18 ነጥቦችን ሰብስበው 10ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ቀያይ ሰይጣኖቹ ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ የሚችሉ ከሆነ ነጥባቸውን ከፍ በማድረግ 3ኛ ላይ ከተቀመጠው ማንችስተር ሲቲ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ 1 ማጥበብ ይችላሉ፡፡

ባለፉት 5 ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት ያልገጠማቸው እና 3 አሸንፈው በ2 አቻ የተለያዩት የሩበን አሞሪም ልጆች የምሽቱን ጨዋታ እጅግ አጥብቀው ይፈልጉታል፡፡

ከጨዋታው በፊት አስተያየታቸውን የሰጡት የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም አሁን ላይ በተሻለ መልኩ እየተጫወትን ነው፤ዉጤት ስናገኝ በራስ መተማመናችን ይበልጥ ከፍ ይላል፤በዚህም ለእያንዳንዱ ጨዋታ ዝግጁ መሆን አለብን ሲሉ ተጨዋቾቻቸውን አሳስበዋል፡፡

በባለ ልምዱ አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ እየተመራ 15 ነጥቦች በመሰብሰብ በደረጃው 13ኛ ላይ የተቀመጠው ኤቨርተን በተመሳሳይ እንደ ማንችስተር ዩናይትድ ሁሉ ደረጃውን ለማሻሻል ወሳኝ መርሀግብር ይጠብቀዋል፡፡

ባለፉት ሳምንታት ወጥ የሆነ አቋም ማሳየት የተሳናቸው ቶፊዎቹ ካለፉት 5 ጨዋታዎች 2 ያሸነፉ ሲሆን በ2 ተሸንፈው እንዲሁም በ1 ጨዋታ ደግሞ ነጥብ ተጋርተዋል፡፡

21/11/2025

ተጠባቂዎቹ የ12ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ፍልሚያዎች

“በእንግሊዝ ጥቁር ኮከብ ተጨዋች አይፈለግም” ኢያን ራይትበእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱ የቀድሞ ከዋክብቶች መካከል አንዱየሆነው የአርሰናል ታሪካዊ ተጨዋች ኢያን ራይት እ...
21/11/2025

“በእንግሊዝ ጥቁር ኮከብ ተጨዋች አይፈለግም” ኢያን ራይት

በእንግሊዝ እግር ኳስ ታሪክ ስማቸው በጉልህ ከሚነሱ የቀድሞ ከዋክብቶች መካከል አንዱየሆነው የአርሰናል ታሪካዊ ተጨዋች ኢያን ራይት እንግሊዝ በራሱ የሚተማመን ጥቁር ኮከብ ተጨዋች ለመመልከት ዝግጁ አይደለችም ሲልጠንከር ያለ ሀሳብ ሰጥቷል፡፡

ለወትሮ ቢሆን ተጨዋቾች ለማሞገስ እና ለመተቸት ቅርብ የሆኑት የእንግሊዝ ሚድያዎች በተለይም ከቅርብ ጊዝያት ወዲህ በሪያልማድሪዱ አማካይ ጁድ ቤሊንግሀም ላይ የተለያዩ ዘገባዎችን በማቅረብ ላይ ተጠምደዋል፡፡

ቤሊንግሀምን በተለያየ መልኩ ስሙን እያነሱ ለሚገኙት ጠንከር ያለ ትችት የሰነዘረው የቀድሞ የአርሰናል ታሪካዊ ተጨዋች ኢያን ራይት ነው፡፡

ራይት እንደሚለው ከሆነ ደግሞ እንግሊዝ በራሱ የሚተማመን ትልቅ አቅም ያለው ኮከብ ለማየት ዝግጁ አይደለችም ሲል ተናግሯል፡፡

አሁን ላይ ቤሊንግሀምን የሚተቹት በምን ምክንያት እንደሆነ እንኳን አላውቅም ያለው የአሁኑ የእግር ኳስ ተንታኝ ኢያን ራይት እንግሊዝ አሁን በጥሩ ጉዞ ላይ ስለሆነች እና የሚያወሩት ስላጡ ብቻ ሌላ አጀንዳ ለመቅረጽ የሚያደርጉት ጥረት እንደሆነ ነው የሚሰማኝ ሲል ምልከታውንአስቀምጧል፡፡

ራይት አያይዞም ቤሊንግሀም በትልቅ ደረጃ እየተጫወተ የሚገኝ እና በራስ መተማመን ያለው ተጨዋች ነው ይህም ደግሞ ጥቁርስለሆነ በዚህ ልክ ራሱን እንዲያሳይ አይፈልጉም፤ነገር ግን እሱን ያስቆማሉ ብዬ አላምንም፤እኔ በምንም ሁኔታ ከጁድ ቤሊንግሀም ጎን አቆማለሁ ሲል ድጋፉን ገልጾለታል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት እንግሊዝ በአለም ዋንጫ ማጣርያ አልባኒያን ባሸነፈችበት ጨዋታ ላይ ምርጥ ብቃቱን ያሳየው እና የእለቱ ኮከብ በመባል የተመረጠው የ22 አመቱ ወጣቱ አማካይ ጁድ ቤሊንግሀም ተቀይሮ ከሜዳ ሲወጣ በአሰልጣኝቶማስ ቱሀል ውሳኔ ደስተኛ አለመሆኑን ተከትሎ ትልቅ የመነጋገርያ ርእስ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

20/11/2025

“ምቤሞ ጫና የማይሰማው ልዩ ተጨዋች ነው” ሀርግሬቭስ

20/11/2025

ወደ ሜዳ ለመመለስ የጓጓው ኮል ፓልመር

ህይወት በማድሪድ እንዳሰበው ቀላል ያልሆነለት አርኖልድ! በብዙ መልኩ ተጠብቆ የልጅነት ክለቡ ሊቨርፑልን በመልቀቅ ወደ ስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያልማድሪድ በክረምቱ ያቀናው እንግሊዛዊው ተከላካይ ...
20/11/2025

ህይወት በማድሪድ እንዳሰበው ቀላል ያልሆነለት አርኖልድ!

በብዙ መልኩ ተጠብቆ የልጅነት ክለቡ ሊቨርፑልን በመልቀቅ ወደ ስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያልማድሪድ በክረምቱ ያቀናው እንግሊዛዊው ተከላካይ ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ እንዳሰበው ሳይሆን በፈተና የተሞላ ጊዝያትን በማሳለፍ ቀጥሏል፡፡

ባሳለፍነው ክረምት የዝውውር መስኮት አበይት የመነጋገርያ ርእስ ከነበሩ ጉድዮች መካከል የ26 አመቱ የተከላካይ መስመር ተጨዋች ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ 20 አመታት ያህል ያሳለፈበት አንፊልድን በመልቀቅ ወደ ሪያልማድሪድ ማቅናቱ አንዱ እንደነበር ይታወሳል፡፡

አርኖልድ ከክለቦች አለም ዋንጫ ዋንጫ ጀምሮ ከሎስብላኮቹ ስብስብ ጋር መቀላቀል ቢችልም አጀማመሩ በተጠበቀው ልክ አልሆነም፡፡

በተጨማሪም ተደጋጋሚ ጉዳቶች ማስተናገዱ ደግሞ ተጨዋቹ በማድሪድ አጀማመሩ ያማረ እንዳይሆን አድርጎበታል፡፡

የባለ ልምዱ ተከላካይ ዳኒ ካርቫሀል የረጂም ጊዜ ተተኪ ይሆናል ተብሎ ቤርናባው የደረሰው አርኖልድ አሁን ላይ ከጉዳቱ ሙሉ በሙሉ ማገገሙ ቢገለጽም በቀጣይ ወደ ምርጥ ብቃቱ ለመመለስ ቀላል የማይባል ፈተና ይጠብቀዋል፡፡

በመጪው ክረምት በሚደረገው የ2026ቱ አለም ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ አቅሙን ማሳየት የሚጠበቅበት አርኖልድ ከወቅቱ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቶማስ ቱሀል ማስጠንቀቂያ አዘል መልእክት ተላልፎለታል፡፡

ቶማስ ቱሀል ሌላኛው የቀድሞ የሊቨርፑል ተከላካይ እና በአሁኑ ወቅት በጀርመኑ ክለብ ባየርሌቨርኩሰን በመጫወት ላይ የሚገኘው ጃሬል ኳንሳን በምሳሌነት በማንሳት ከሳምንት ሳምንት በወጥነት የሚጫወቱ ተጨዋቾች በቡድኔ ውስጥ ቅድሚያ ቦታ ይሰጣቸዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጥሩ ያልሆነ የውድድር አመትን እያሳለፈ የሚገኘው የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በክለቡ ወሳኝ ሚና ከነበራቸው ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድን ማጣቱ ትልቅ ክፍተት እንደፈጠረበት በጉልህ የታየ ሆኗል፡፡

19/11/2025

ተጨዋቾች ለምን በቀላሉ ጉዳት ያስተናግዳሉ?

19/11/2025

“ልጄ የሮናልዶ ቀንደኛ ደጋፊ ነው” ትራምፕ

18/11/2025

ጁልያን አልቫሬዝን ለማስፈረም
የተጧጧፈው ፉክክር

የአመቱ የአፍሪካ ኮከብ ተጨዋች ማን ይሆናል?በየአመቱ የሚዘጋጀው የአፍሪካ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን ለማሸነፍ ሞሮኳዊው የፓሪሴንት ዤርሜይን ተከላካይ አሽራፍ ሀኪሚ፤ግብጻዊው የሊቨርፑል ኮከብ ሞ...
18/11/2025

የአመቱ የአፍሪካ ኮከብ ተጨዋች ማን ይሆናል?

በየአመቱ የሚዘጋጀው የአፍሪካ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን ለማሸነፍ ሞሮኳዊው የፓሪሴንት ዤርሜይን ተከላካይ አሽራፍ ሀኪሚ፤ግብጻዊው የሊቨርፑል ኮከብ ሞሐመድ ሳላህ እንዲሁም ናይጄርያዊው የጋላታሳራይ አጥቂ ቪክቶር ኦስሜን ተፋጠዋል፡፡

ልክ እንደ ሌሎች አህጉራት ሁሉ በየአመቱ ከሚዘጋጁ ሽልማቶች መካከል የሆነው በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የሚዘጋጀው ሽልማት የ2025 አሸናፊ ማን ይሆናል የሚለው ጉዳይ ተጠባቂ ሆኗል፡፡

አሁን ላይ የመጨረሻ 3 እጩዎች ይፋ የተደረጉ ሲሆን የዘንድሮውን ሽልማት ለማሸነፍ ሰፊ ቅድመ ግምቶችን ማግኘት የቻለው ሞሮኳዊው የፓሪሴንት ዤርሜይን የቀኝ መስመር ተከላካይ አሽራፍ ሀኪሚ ይገኝበታል፡፡

በፓሪሱ ክለብ አስደናቂ የውድድር አመትን ማሳለፍ የቻለው የ27 አመቱ ሀኪሚ ክለቡ በታሪኩ ለመጀመርያ ጊዜ የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ሲያሳካ ቀዳሚ ተዋናይ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም በውድድር አመቱ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ፤የፈረንሳይ ሊግ አ ጨምሮ የውስጥ ውድድር ዋንጫዎችን በሙሉ ማሸነፍ ችሏል፡፡

ሌላኛው የዚህ ሽልማት ተፋላሚ የሆነው ግብጻዊው የ33 አመቱ የሊቨርፑል ኮከብ ሞሐመድ ሳላህ ሲሆን.በውድድር አመቱ ምርጥ የተባለ ጊዝያትን ማሳለፍ ችሏል፡፡

ሳላህ ቀያዮቹ በታሪካቸው 20ኛውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን እንዲያሳኩ የአንበሳውን ድርሻ መወጣቱ ይታወሳል፡፡

በመጨረሻ 3 እጩዎች ውስጥ የተካተተተው ሌላኛው ናይጄርያዊው የጋላታሳራይ አጥቂ ቪክቶር ኦስሜንሲሆን በተመሳሳይ ምርጥ የተባለ የውድድር አመትን ያሳለፈበት ሆኗል፡፡

የ26 አመቱ ኦስሜን ክለቡ ጋላታሳራይ የተርኪሽ ሱፐር ሊግዋንጫ እንዲያሳካ ሀላፊነቱን በሚገባ መወጣት ችሏል፡፡

የሽልማቱ አሸናፊ በነገው እለት በሞሮኮ ራባት ይፋ ይሆናል፡፡

ባሳለፍነው የውድድር አመት ይህንን ሽልማት ማሸነፍ የቻለው ናይጄርያዊው የአታላንታ የፊት መስመር ተጨዋች አዴሞላ ሉክማን እንደነበር አይዘነጋም፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kal Sports posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Kal Sports:

Share