ወሬ ነጋሪ Tube

ወሬ ነጋሪ Tube Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ወሬ ነጋሪ Tube, Media, Addis Ababa.

በተለያዬ ጊዜ ሁለት ህፃናትን በማታለል የደፈሩ የ65 ዓመት አዛውንት በ25 ዓመት እንዲሁምያሳደጋትን የእንጀራ ልጁን የደፈረው ግለሰብ በ11 ዓመት ከዘጠኝ ወር ፅኑ እስራትመቀጣታቸውን የአዲስ...
26/06/2020

በተለያዬ ጊዜ ሁለት ህፃናትን በማታለል የደፈሩ የ65 ዓመት አዛውንት በ25 ዓመት እንዲሁም
ያሳደጋትን የእንጀራ ልጁን የደፈረው ግለሰብ በ11 ዓመት ከዘጠኝ ወር ፅኑ እስራት
መቀጣታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ገላን ጉራ አካባቢ በሚገኝ የአንድ የግል ድርጅት ውስጥ
በጥበቃ ስራተኛነት ሲሰሩ የነበሩ የ65 ዓመት ግለሰብ በተለያዬ ጊዜየ 8 እና የ9 ዓመት እድሜ
ያለቸውን ሁለት ህፃናት በማታለል ወንጀሉ እንደተፈፀመባቸው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
የህጻናትና ሴቶች ምርመራና እንክብካቤ ዲቪዚዮን ኃላፊ ኮማንደር አጸደ ወርዶፋ ገልፀዋል፡፡
የ64 አመቱ አዛውንት የፈፀሙትን የወንጀል ድርጊት የተመለከተው በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ
ፍርድ ቤት አቃቂ ቃሊቲ ምድብ ወንጀል ችሎት በሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት
ተከሳሹን ያስተምራል ሌሎችን ያስጠነቅቃል በማለት በ25 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ
መወሰኑን ኮማንደሯ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ግለሰቡ በ2011 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ በተለያዩ ጊዜያት ብር እሰጣችኋለሁ ቤቴ ውሰጥ
ትጫወታላችሁ በማለት እና በማግባባት ተከራይተው ወደ ሚኖሩበት ቤት ህፃናቱን ካስገቧቸው
በኋላ በህጻናቱ ላይ በድግግሞሽ ወንጀሉ እንደተ ፈፀመባቸው በፖሊስ የምርመራ ሂደት
መረጋገጡን ዳኛ አቶ ዮናስ መኮንን አብራርተዋል፡፡
በተመሳሳይ ዜና በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ
ከህፃንነቷ ጀምሮ ያሳደጋትን የ15 ዓመት የእንጀራ ልጁን የደፈረው ግለሰብ በ11 ዓመት ከ9 ወር
ጽኑ እስራት እንደተቀጣ ኮማንደር አጸደ ወርዶፋ ጨምረ ውገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በህፃናት ላይ የሚፈፀመውን ልዩ ልዩ ጥቃቶችን ለመከላከል
ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ኮማንደሯ አስታውቀው ህጻናትና ሴቶች ልዩ ትኩረት
የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ዜጎች ወንጀሉን እንዲከላከሉ ግንዛቤ ከማስጨበጥ ባሻገር
አጥፊዎች ላይ አሰተማሪ ውሳኔ እንዲወሰንባቸው ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው የፍትህ አካላት ጋር
ያለውን ቅንጅት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡
ምንጭ:-አዲስ አበባ ፖሊስ

26/06/2020
https://youtu.be/busgbmyMpp0
17/06/2020

https://youtu.be/busgbmyMpp0

''በአራጣ የተያዘ ጭን'' አስገራሚ እውነተኛ ለማመን እና ለማሰብ የሚከብድ ታሪክ....

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ወሬ ነጋሪ Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category