
07/10/2025
በፌደራል መንገዶች ባለስልጣን የሚሰራው የወልቂጤ ከተማ መንገድ እና ጎን ለጎን የሚሰራው የኮሪደር ስራ ግንባታ አለመፋጠን ከተማውን ለከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ እና አዋራ ዳርጎታል። አሽከርካሪዎች፣ እግረኞችና የንግድ ተቋማት ላይ ጫናው በግልፅ ይታያል።
ሌላው የሚስተዋለው ችግር እየተሰራ ያለው መንገድ ጥበት ነው። መንገዱ የወደፊቱ ይቅርና የአሁኑ የከተማው የትራፊክ ፍሰት እንኳን በአግባቡ ማስተናገድ የሚችል አይደለም። የመንገድ አካፋይ መሰራቱ ጥሩ ቢሆንም የመንገዱ ጥበት ግን ገና ከወዲሁ ችግሩ አፍጦ እየታየ ነው። የከተማው አስተዳደር ከመንገዶች ባለስልጣን ጋር በመሆን ከወዲሁ መፍትሄ ቢያበጅ የተሻለ ይሆናል!
የከተማው ነዋሪ ወይም ተመላላሽ ከሆኑ አስተያየትዎን ያካፍሉን።
Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ