Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

  • Home
  • Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ ሀገራዊ፣ አካባቢያዊ እና የጉራጌን ህዝብ ባህል ቋንቋ ኢኮኖሚ ፣ ፖለቲካ ፣ ማህበራዊ እንዲሁም ሁለንተናዊ ጉዳዮች የምንጦምርበት ገጽ ነው።
(1)

 #ሿሿሰሞኑን ሿሿ የሚሰሩ ሌቦች ወልቂጤ ላይ ተበራክተዋል። በተለይ አደባባይ አካባቢ በዛ ብለው እየቆሙ  እና ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ መስለው እየገቡ ከብዙ ሰው ገንዘብና ስልክ እየዘረፉ ነው። ...
22/07/2025

#ሿሿ
ሰሞኑን ሿሿ የሚሰሩ ሌቦች ወልቂጤ ላይ ተበራክተዋል።

በተለይ አደባባይ አካባቢ በዛ ብለው እየቆሙ እና ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ መስለው እየገቡ ከብዙ ሰው ገንዘብና ስልክ እየዘረፉ ነው።

በዚህ አስር ቀን ውስጥ ብቻ በቅርብ የማውቃቸው ሶስት ሰዎች ስልክ ተወስዶባቸዋል።

ሁለቱ የተሰረቁት ባጃጅ ውስጥ ሌቦቹ ተሳፋሪ መስለው መሀል አስገብተዋቸው ነው።

የአንዱ ግን ይለያል ነገሩ ሲያስረዳም ''ትከሻዬ አካባቢ ነካ አደረገኝ ከደቂቃዎች በኋላ ስነቃ ስልኬ ከኪሴ የለም'' ብሏል።

ከኮሪደር ልማት ስራው ጎን ለጎን የደህንነት ካሜራ ታሳቢ መሆን አለበት ምክንያቱም የጸጥታው አካል ሁሉም ቦታ ላይ መገኘት አይችልም።

በነገራችን ላይ አሁንም ቢሆን ወልቂጤ ከተማ ስጋት የሌለበትና በምሽት ጭምር በነጻነት መንቀሳቀስ የሚቻልበት ከተማ ነው።

ግን አንዳንድ ጥቃቅን ነገሮች በጊዜ መፍትሄ ካልተበጀላቸው በኋላ ከባድ ደረጃ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ።

Via Melaku Nemani

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

 #ቴምር እሪል-እስቴት‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣቸው በመጠናቀቅ ላይ ያሉ እና እየተሰሩ ያሉ ሳይቶቻችን መሐከል ተክለሃይማኖት; ፒያሳ እና አያት ለሽያጭ...
22/07/2025

#ቴምር እሪል-እስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣቸው በመጠናቀቅ ላይ ያሉ እና እየተሰሩ ያሉ ሳይቶቻችን መሐከል
ተክለሃይማኖት; ፒያሳ እና አያት ለሽያጭ ያወጣቸው ሳይቶች

🎯ተክለሀይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት
👉3 መኝታ 110ካሬ--123ካሬ
👉10%ቅድመ ክፍያ 1,067,000ብር
👉ቀሪውን 90% በ11 ዙር ከፍለው የሚጨርሱት
🎯ፒያሳ ሊሴ ትምህርት ቤት አጠገብ
👉ከባ1መኝታ 63ካሬ እስከ 146ካሬ
👉ቅድመ ክፍያ 10%=715,000ብር ጀምሮ
👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው የሚጨርሱት

🎯አያት
👉2 መኝታ እና 3 መኝታ
👉87ካሬ ጀምሮ እስከ 133ካሬ
👉 10%ቅድመ ክፍያ 765,600 ብር ጀምሮ
👉ቀሪውን 90% በ8ዙር ወይም በ16ዙር ከፍለው የሚጨርሱት

🎯30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ቅናሽ አለን
👇👇👇👇👇👇👇
✍️የንግድ ሱቅ
👉 ፒያሳ አድዋ 00 ሙዚየም ፊትለፊት ( በመንግሥት የተገነባው 10ሺ መኪና ከሚያቆመው ተርሚና አጠገብ)
✍️2B+G+5 moder commercial mall only
✍️ከ20 ካሬ ጀምሮ
👉900ሺ ብር ቅድመ ክፍያ
✍️1አመት ከግማሽ የሚረከቡት
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251924479891
WhatsApp https://wa.me/251924479891

አድማስ የገበሬዎቻችን ዐይንን አጠፉት!(በውስጥ መስመር ለዘቢዳር ሚዲያ የተላከ) ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።አንዳንዶች ድርጅቶችን ይፈጥራሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ የጎለመሱ ድርጅቶችን ያፈ...
21/07/2025

አድማስ የገበሬዎቻችን ዐይንን አጠፉት!
(በውስጥ መስመር ለዘቢዳር ሚዲያ የተላከ)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አንዳንዶች ድርጅቶችን ይፈጥራሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ የጎለመሱ ድርጅቶችን ያፈርሳሉ፡፡ አድማስ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩንየን ሁለተኛው ዓይነት እጣ ፈንታ ገጥሞታል፡፡

የአሁን አያድርገውና ማህበራዊ ንብረትነቱ በጉራጌ ዞን አርሶ አደሮች የሆነውና በአንድ ወቅት ሥሙ የናኘና በአገር አቀፍ ደረጃ ከሚጠቀሱ የገበሬዎች ማህበራት መካከል ነበር፡፡ ይህም በመሆኑ ሠራተኞቹ በተለያዩ የውጭ አገራት ሄደው ለእራሳቸው እውቀትን ለድርጅቱ ደግሞ እንዲስፋፋ የሚያስችለው ድጋፍን ይዘው ተመልሰዋል፡፡

ምን አልባትም እንዚህ ሰዎች ልባቸው ቢከጅል የገበሬ አባቶቻቸውን ህልም እንደያዙ መቅረት የሚችሉባቸው የአውሮፓ አገራት ነበር የሄዱት፡፡ ነገር ግን የገበሬዎቹን ህልም ማጨናገፍ የሻቱ አልመሰለኝም፡፡

ባለፉት ዓመታት አድማስ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒየን በየወረዳው የገበሬዎች ማሳ ምርታማ እንዲሆን በተደረገው ጥረት የአጋዥነት ሚና ነበረው፡፡ ከማሳ ወጥቶ ማህበርተኞችን የፋብሪካ ባለቤት እስከማድረግ የደረሰ ድርጅትም ነው፡፡ የዘይት ማጣሪያ ፋብሪካውን እንዲሁም የቡና ማበጠሪያ ማዕከሉን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አድማስ የገበሬዎች የህብረት ሥራ ዩኒየን በቅርብ ዓመታት መቀመጫቸውን ጉራጌ አካባቢ ካደረጉና አካባቢ በቀል ከሆኑ ትርፋማ የንግድ ማህበራት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነበር።

ድርጅቱን እዚህ ደረጃ ላይ ለማድረስ ብዙዎች ዋጋ ከፍለውበታል፡፡ ይሁን እንጂ አሁን ላይ የድርጅቱ ንብረቶች ላይ ባልተከፈለ ዕዳ ምክንያት የሀራጅ ማስታወቂያ ወጥቶባቸዋል፡፡ በድርጅቱ አሠራር ችግሮች መኖራቸው እየታወቀ ብዙዎች በ"እከክልኝ ልከክልህ" ታልፈዋል፡፡ የገበሬዎች ማህበር እንደመሆኑና ብዙ ገንዘብ እንደሚያንቀሳቅስ ድርጅት ኃላፊዎች ሲቀየሩ ወይም ከቦታቸው ሲነሱ ኦዲት ተደርገው አያውቁም። ተደርገውም ከሆነ እስከአሁን የተጠየቀ አላየሁም፡፡ ግን ደግሞ በቅርብ ዓመታት ድርጅቱ ከፍተኛ ምዝበራ ሲካሄድበት እንደነበር ለእውነት በርካታ አመላካች ነገሮች ነበሩ፡፡

ካለፉት 5 ዓመታት ጀምሮ ያ ባለ ግርማ የነበረ ትርፋማ ድርጅት ቅጥ አምባሩ እንደጠፋ ነው ስንታዘብ የነበረው፡፡ ሁኔታው ከዞኑ አመራሮች የተሰወረ አልነበረም፡፡ ከነበረው ዝና አንፃር ከሌሎች ከተሞች ጭምር መጥተው ልምድ እንዳልቀሰሙበት ትርፍ እንኳን ባያመጣ በእዳ ሊሸጥ ሐራጅ ወጣበት ሲባል በእጅጉ ያሳዝናል፡፡

በሌሎች አካባቢ ያሉ የገበሬ ህብረት ማህበራት መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት እያደጉና እየፈረጠሙ ባለበት ወቅት ስመ ገናናው አድማስ በሐራጅ እየተሸጠ ነው ሲባል በተቋሙና በአካባቢያችን የሰፈነው ብልሹ አስተዳደር የሚያጋልጥ ይመስለኛል። የአድማስ አቅም ምን ያህል እንደነበረ ከዚሁ የሐራጅ ማስታወቂያ መገመት ይቻላል። በጥቂቶች ችግር ምክንያት የበርካቶች ጥሪት በሐራጅ እንዳይሸጥ የዞኑ መንግስት ጣልቃ ገብቶ/ከባንኩ ጋር ተደራድሮ/ ሀራጁን ማስቀረት የሚችል ከሆነ ቢሞክር ጥሩ ነው፡፡

ለተቋሙ ውድቀት ተጠያቂ የሆኑ አካላት ሕግ ፊት እንዲቀርቡ ማድረግ ግን የዞኑ አስተዳደር ትንሹ ኃላፊነት ይመስለኛል። በዚሁ አጋጣሚ በዞኑ አካባቢ የሰፈነው ብልሹ አስተዳደር እና ሙስና በአግባቡ ይፈተሽ እላለሁ። ድርጅቱ ለዩኒየኑ ባለቤቶችና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ተጨማሪ ማብራርያ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡
(ጨረታው የወጣበት ሊንክ በመልክት ሳጥን ውስጥ ተቀምጧል)

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

በውስጥ የደረሰን መልዕክት!==================በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እና ዙርያዋ በተደጋጋሚ ዘረፋ እየተፈፀመ ይገኛል።  በትላንትናው ዕለት ለሊት ሀምሌ 12 ከለሊቱ 8:15 ለጊ...
20/07/2025

በውስጥ የደረሰን መልዕክት!
==================

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ እና ዙርያዋ በተደጋጋሚ ዘረፋ እየተፈፀመ ይገኛል። በትላንትናው ዕለት ለሊት ሀምሌ 12 ከለሊቱ 8:15 ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቀ ዘራፊዎች የከተማው ቄራ ውስጥ በመግባት ለእርድ የተዘጋጁ 16 ከብቶችን በመዝረፍ ሃ/አለቃ ካሳሁን ደስታ የተባለን የፖሊስ አባል በመግደልና ተጨማሪም አንድ አባል በማቁሰል ከብቶቹን ይዘው ተሰውረዋል።

የከተማው ቄራ ላይ ዘረፋ ሲፈፀምበት ለአራተኛ ጊዜ ነው እንዲሁም በከተማው መግቢያ እና መውጫ ላይ በተደጋጋሚ የሰው ነብስ እየጠፋ ይገኛል። ነገሮች እየተባባሱ ያሉት የቀቤና ልዩ ወረዳ ከጉራጌ ዞን መዋቅር ከተገነጠለበት ቀን ጀምሮ ከተማዋ ሰላም አጥታለች ክልሉም ሆነ የዞኑ መንግስት ዝምታን መርጠዋል።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

ወጣት ፀጋው ታደሰ በትላንትናው ዕለት ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ፖሊስ “ለጥያቄ ትፈለጋለህ" ብሎ ወስዶታል። ወጣት ፀጋው ታደለ ትላንት አርብ ሐምሌ 11/2017 ወራቤ ከተማ ከሚገኘው መስሪያ ቤ...
19/07/2025

ወጣት ፀጋው ታደሰ በትላንትናው ዕለት ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ፖሊስ “ለጥያቄ ትፈለጋለህ" ብሎ ወስዶታል።

ወጣት ፀጋው ታደለ ትላንት አርብ ሐምሌ 11/2017 ወራቤ ከተማ ከሚገኘው መስሪያ ቤቱ በወራቤ ከተማ ፖሊሶች ለእስር መዳረጉ ዘቢዳር ሚዲያ አረጋግጣለች።

ዘቢዳር ሚዲያ ፀጋው ለእስር የተዳረገበት ምክንያት ለማጣራት ባደረገችው ሙከራ "በማሕበራዊ ትስስር ገፅህ ህዝብ መንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ እያደረክ ነው" በሚል መሆኑን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ፀጋው በወራቤ ከተማ ፖሊስ ከተያዘ በኃላ ተላልፎ ተሰጥቶ በትላንትናው ዕለት ወደ ቡታጀራ ተወስዶ በከተማው ፖሊስ ማቆያ ይገኛል።

ፀጋው በወራቤ ከተማ በባንክ ማናጀርነት ሆኖ እየሰራ ሲሆን የክስታኔ ምሁራን መማክርት እና የአዳብና ማህበር መስራች መሆኑ ይታወቃል።

ፀጋው ለጉራጌ አንድነት ተግተው ከሚታገሉ ምሁራኖች መካከል በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ሲሆን በተለያዩ ጊዜአት የህዝብን ጥያቄ አንስተው ለሚታሰሩ ወገኖች ቀድሞ ቦድረስ ሁለንተናዊ ድጋፍ ሲያደርግ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

የአካባቢው ምንጮቻችን የፀጋው እስር ምክንያት በሶዶ ወረዳዎች ያለውን የፀጥታ እጦት በመቃወም ለእስር እየተዳረጉ ካሉ ወጣቶች የተለየ ሊሆን እንዳልሆነ ይገልፃሉ።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

13ኛው ጉዞ አረንጓዴ ልማት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በምስ/ጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ ጎሴሳለን ቀበሌ ተካሔደ።የልማት ማህበሩ  የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሺሰማ ገ/ስላሴ እንዳሉት ባለፋት 12 ተ...
19/07/2025

13ኛው ጉዞ አረንጓዴ ልማት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በምስ/ጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ ጎሴሳለን ቀበሌ ተካሔደ።

የልማት ማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሺሰማ ገ/ስላሴ እንዳሉት ባለፋት 12 ተከታታይ አመታት በየወረዳው የተራቆቱ አካባቢዎች በችግኝ በመሸፍን ለአረንጓዴው መላበስ የበኩሉን ሲወጣ ቆይቷል ብለዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ችግኝ ከመተከሉ ባሻገር የጉራጌ አንድነትን ይበልጥ የሚያጎለብት ነው ብለዋል።

እንደ ጉልባማ ስራ አስኪያጅ አቶ ቅባቱ ተሰማ መሰረት በጉዞ አረንጓዴ ልማት ፕሮግራም እስካሁን ከ1 ሚሊየን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። ከተተከሉ ችግኞች 84 እጁ መጽደቃቸው አስታውቀዋል።

በዛሬው እለትም በ43 ሄክታር መሬት 25 ሺ ችግኞች እንዲተከሉ ሲሆነ3 በቀጣይ ደኑና የማልማት ስራ ይሰራል ተብሏል።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

 #ቴምር እሪል-እስቴት‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣቸው በመጠናቀቅ ላይ ያሉ እና እየተሰሩ ያሉ ሳይቶቻችን መሐከል ተክለሃይማኖት; ፒያሳ እና አያት ለሽያጭ...
18/07/2025

#ቴምር እሪል-እስቴት

‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ ለሽያጭ ያወጣቸው በመጠናቀቅ ላይ ያሉ እና እየተሰሩ ያሉ ሳይቶቻችን መሐከል
ተክለሃይማኖት; ፒያሳ እና አያት ለሽያጭ ያወጣቸው ሳይቶች

🎯ተክለሀይማኖት ሆስፒታል ፊት ለፊት
👉3 መኝታ 110ካሬ--123ካሬ
👉10%ቅድመ ክፍያ 1,067,000ብር
👉ቀሪውን 90% በ11 ዙር ከፍለው የሚጨርሱት
🎯ፒያሳ ሊሴ ትምህርት ቤት አጠገብ

👉ከባ1መኝታ 63ካሬ እስከ 146ካሬ
👉ቅድመ ክፍያ 10%=715,000ብር ጀምሮ
👉ቀሪውን 90% በ17ዙር ከፍለው የሚጨርሱት

🎯አያት
👉2 መኝታ እና 3 መኝታ
👉87ካሬ ጀምሮ እስከ 133ካሬ
👉 10%ቅድመ ክፍያ 765,600 ብር ጀምሮ
👉ቀሪውን 90% በ8ዙር ወይም በ16ዙር ከፍለው የሚጨርሱት

🎯30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ቅናሽ አለን
👇👇👇👇👇👇👇
✍️የንግድ ሱቅ
👉 ፒያሳ አድዋ 00 ሙዚየም ፊትለፊት ( በመንግሥት የተገነባው 10ሺ መኪና ከሚያቆመው ተርሚና አጠገብ)
✍️2B+G+5 moder commercial mall only
✍️ከ20 ካሬ ጀምሮ
👉900ሺ ብር ቅድመ ክፍያ
✍️1አመት ከግማሽ የሚረከቡት
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
👇👇👇👇👇👇
+251924479891
WhatsApp https://wa.me/251924479891

የማረቆ ልዩ ወረዳ ለምስራቅ ጉራጌ ዞን መዋቅር ማቋቋሚያ የሚረዳ አስር የሰንጋዎች ድጋፍ አደረገ።የማረቆ ልዩ ወረዳ ለምስራቅ ጉራጌ ዞን መዋቅር ማቋቋሚያ በገቡት ቃል መሰረት አስር ሰንጋዎች ...
16/07/2025

የማረቆ ልዩ ወረዳ ለምስራቅ ጉራጌ ዞን መዋቅር ማቋቋሚያ የሚረዳ አስር የሰንጋዎች ድጋፍ አደረገ።

የማረቆ ልዩ ወረዳ ለምስራቅ ጉራጌ ዞን መዋቅር ማቋቋሚያ በገቡት ቃል መሰረት አስር ሰንጋዎች ቡታጅራ ከተማ በመገኘት ድጋፍ አድርገዋል።

ድጋፉን ያስረከቡት የማረቆ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል አማሮ ድጋፉ ለወንድም እህት ወገን ለሆኑ ለዞኑ ማህበረሰብ አብሮነታችን ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።

ዞኑ ለማቋቋምና የተሻለ አገልግሎት ለማህበረሰቡ እንዲሰጥ በሚደረገው ጥረት ልዩ ወረዳው በቀጣይ ከጎናቸው በመሆን መሰል ድጋፎችን ስራዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል።

ድጋፉን የተቀበሉት የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሀሰን ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ድጋፉ ወንድም እህት ለሆኑት ማህበረሰብ አብሮነታችንና አንድነታችን ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በቀጣይም ሁለቱ መዋቅሮች በመዳጋገፍና በመተባበር የተለያዩ የልማት ስራዎችን እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በምስራቅ መስቃንና በማረቆ ልዩ ወረዳ አካባቢ የተፈጠሩ ግጭቶችን በክልሉ አመራር ቆራጥ ውሳኔ ሰጪነትና በሁለቱም መዋቅር አመራሮች በጋራ በመስራት ወደተሻለ ሰላም መምጣቱን አንስተው በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚሰራ ጠቅሰዋል።

የድጋፍ ርክክቡ ወቅት የሁለቱም መዋቅሮች የፊት አመራሮች ተገኝተዋል።

ዘገባው የምስራቅ ጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

ኢቢሲ ሆሳዕና ስቱዲዮ ሊገነባ ነው፡፡በዚሁ ወቅት የክልሉን ጸጋዎች ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ የጎላ ሚና ይኖረዋል ሲሉ የ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ...
15/07/2025

ኢቢሲ ሆሳዕና ስቱዲዮ ሊገነባ ነው፡፡

በዚሁ ወቅት የክልሉን ጸጋዎች ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ የጎላ ሚና ይኖረዋል ሲሉ የ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌትነት ታደሰ በበኩላቸው፤ የኢቢሲ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ የሆነው ሆሳዕና ስቱዲዮ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥራ እንዲጀምር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

አክለውም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም፤ እያከናወናቸው ያሉ የልማት ሥራዎች ውጤታማ ናቸው ነው ያሉት።

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)፥ ኢቢሲ የሕዝቦችን አንድነት እና ትስስር የሚያጠናክር ዘገባ እንዲሰራ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል በማለት አብራርተዋል።

ኢቢሲ በአጭር ጊዜ እራሱን በቴክኖሎጂ አበልጽጎ የፈጣን እና ታማኝ መረጃ ምንጭ እየሆነ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የሚዲያ አድማሱን በክልሎች ማስፋቱ ሊበረታታ ይገባል ብለዋል።

የኢቢሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌትነት ታደሰ፥ ኢቢሲ በክልሎች እያስገነባቸው ያሉትን ስቱዲዮዎች በማጠናቀቅ እና የቴክኖሎጂ ግብዓት በማሟላት፤ የመረጃ ተደራሽነቱን እያሰፋ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

(ኢቢሲ)

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ የትምህርት መሰረተ ልማት ማሻሻል መቻሉን የምሁር አክሊል ወረዳ አስተዳደር ገለጸ።በወረዳው የአዳዲስ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ፣ የጥገና ስራ፣ ግብአት...
15/07/2025

ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ሀብት በማሰባሰብ የትምህርት መሰረተ ልማት ማሻሻል መቻሉን የምሁር አክሊል ወረዳ አስተዳደር ገለጸ።

በወረዳው የአዳዲስ የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ፣ የጥገና ስራ፣ ግብአት ሟሟላት፣ መጸዳጃ ቤቶችና ሌሎችም የትምህርት መሰረተ ልማቶች ለሟሟላት መሰራቱን ተናግረዋል።

በዚህም ተወላጅ ባለሀብቶች፣ የቀድሞ ተማሪዎች ህብረት፣ በጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ ህብረተሰቡና በመንግስት 37 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ ታቅዶ 80 ሚሊዮን 108 ሺህ 937 ብር በማሰባሰብ የትምህርት መሰረት ልማት ማሻሻል ተችሏል፡፡ ለአብነት በወረዳው የምሁርና ጨዛ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በከተማና ከሀገር ውጭ በሚኖሩ ተወላጆች 22 እስታንዳርዳቸው የጠበቁ ዘመናዊ የመምህራን መኖሪያ ቤቶች ተገንብተዋል፡፡

የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ያነጋገራቸው የምሁር አክሊል ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብስራት ገብሩ እና የዘርፉ ተጠሪ አካላት እንድተናገሩት በወረዳው በበጀት አመቱ ከተወላጅ ባለሀብቶች፣ ከህብረተሰቡና ከሌሎችም ረጂ ድርጅቶች የትምህርት ዘርፍ ማሻሻያ የተደረገ ሲሆን የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

 #ድምድወትጉራጌ፣ ከተማና ከተሜነት ተጭኖ ያስቀራቸው ወይም ኅብረተሰቡ አስፈላጊ አይደሉም ብሎ የተዋቸው  አንዳንድ የሚገርሙ  ባህሎች ነበሩት፡፡ ከነኝህ  ባህሎች አንዱ ድምድወት ነው፡፡  ድ...
15/07/2025

#ድምድወት

ጉራጌ፣ ከተማና ከተሜነት ተጭኖ ያስቀራቸው ወይም ኅብረተሰቡ አስፈላጊ አይደሉም ብሎ የተዋቸው አንዳንድ የሚገርሙ ባህሎች ነበሩት፡፡ ከነኝህ ባህሎች አንዱ ድምድወት ነው፡፡

ድምድወት፣ መንታዎች ወይም ተቀራራቢ ዕድሜ ያላቸው ወንድማማቾች በተመሳሳይ ቦታና ቀን የጋብቻ ሥነ-ሥርዓታቸውን የሚያከናውኑበት ሥርዓት ነው፡፡

ድምድወት የሚከናወንበት ደማቁ የመስከረም ወር፣በአካባቢው ወንዶችና ሴቶች፣እንዲሁም ከሴት ሙሽራዎች አካባቢ በመጡ ወጣቶች ጭፈራ ይቀልጣል፡፡

በዚያች የሠርግ ምሽት፣ያቺ ዘገር (የጫጉላ ጎጆ) አራት ሙሽሮችን ታስተናግዳለች፡፡ አስደናቂ ክንውኖች የሚከናወኑት በመጀርያው የጫጉላ ምሽት ነው፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ፣ በዚህ ዕለት፣ የአካባቢው ጎረምሶች በሌሊት ተደብቀው በዘገሯ አካባቢ ያንዣብባሉ፡፡

የሙሽሮች የቅርብ ቤተሰቦች ደግሞ ጎረምሶቹ ወደ ዘገሯ እንዳይጠጉ ይከላከላሉ። ከምሽቱ ክንውን ለአንድ ሳምንት የምትሆንና ትንሽ እውትነት ያላት ቀልድ ሁሌም አትጠፋም።

‹‹እንዳትሸነፊ!›› የሴቶች መካሪ ታበረታታለች።
‹‹ይህን ዘዴ ተጠቀም!›› (ዘዴው እየተጠቆመ ነው የሚመከረው)።

የወንድ ሚዜዎች!
አንዳንድ ጊዜ ሁለት ሴቶች በጋራ ለመከላከል ይሞክራሉ። ድምጽ ላለማሰማት ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል። መውደቅ መነሳቱ አይጣል ነው። ግብግብ ከሌለማ! የመሸናነፍ ሰሜት ከሌለማ! ታዲያ የኋላ ኋላ ታላቅየው ሙሽሮ፤ ‹‹ሄታሽ ኧተሞ!›› ትላለች፡፡ ከእንግዲህማ እህት ዓለም! ከእንግዲህማ እንገብር እንጂ!! እንገብር እንጂ!! እንደማለት።

ሌላው ከድምድወት ጋር አብሮ የሚነሳውና ለረጅም ጊዜ ሲቀለድ የኖረው፤ ታላቅዬው ሙሽራ፣ ‹‹ቀረሺም ቅርስ!›› ወይም ‹‹ፊሽካ ተነፍቷል!›› አለ ተብሎ የሚነገረው ቀልድ ነው።

Kibru BookStore

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

ስለእኒህ ሰው ምን ያክል ታውቁ ይሆን??ይህ ሐውልት ካሳንቺስ ቤንዚል ማደያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ ስር (ዘመን ባንክ አጠገብ) ነው የሚገኘው::Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ
15/07/2025

ስለእኒህ ሰው ምን ያክል ታውቁ ይሆን??

ይህ ሐውልት ካሳንቺስ ቤንዚል ማደያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ ስር (ዘመን ባንክ አጠገብ) ነው የሚገኘው::

Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

Address


Telephone

+251977961254

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share