
22/07/2025
#ሿሿ
ሰሞኑን ሿሿ የሚሰሩ ሌቦች ወልቂጤ ላይ ተበራክተዋል።
በተለይ አደባባይ አካባቢ በዛ ብለው እየቆሙ እና ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ መስለው እየገቡ ከብዙ ሰው ገንዘብና ስልክ እየዘረፉ ነው።
በዚህ አስር ቀን ውስጥ ብቻ በቅርብ የማውቃቸው ሶስት ሰዎች ስልክ ተወስዶባቸዋል።
ሁለቱ የተሰረቁት ባጃጅ ውስጥ ሌቦቹ ተሳፋሪ መስለው መሀል አስገብተዋቸው ነው።
የአንዱ ግን ይለያል ነገሩ ሲያስረዳም ''ትከሻዬ አካባቢ ነካ አደረገኝ ከደቂቃዎች በኋላ ስነቃ ስልኬ ከኪሴ የለም'' ብሏል።
ከኮሪደር ልማት ስራው ጎን ለጎን የደህንነት ካሜራ ታሳቢ መሆን አለበት ምክንያቱም የጸጥታው አካል ሁሉም ቦታ ላይ መገኘት አይችልም።
በነገራችን ላይ አሁንም ቢሆን ወልቂጤ ከተማ ስጋት የሌለበትና በምሽት ጭምር በነጻነት መንቀሳቀስ የሚቻልበት ከተማ ነው።
ግን አንዳንድ ጥቃቅን ነገሮች በጊዜ መፍትሄ ካልተበጀላቸው በኋላ ከባድ ደረጃ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ።
Via Melaku Nemani
Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ