
12/08/2025
አዲስ ፍጥጫ‼️
ኢራን በትናንትናው ዕለት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴርን ጨምሮ አጠቃላይ አስር ከፍተኛ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራሮችን ለመግደል ማቀዷን ስም ዝርዝራቸውን ይፋ አድርጋለች።
ይህን ተከትሎ እስራኤል ከኢራን ሊመጣ ከሚችል ጥቃት እራሷን ለመከላከል ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሁሉም የጦር አመራሮች እና የሞሳድ የስለላ ድርጅት ዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቅ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን የእስራኤል ሚዲያዎች ዘግበዋል።
በኢራን ከሚገደሉ ስም ዝርዝር ውስጥ የሚገኙት የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር "የኢራኑን መሪ አያቶላህ አልካሜኒ ከተደበቁበት ጥልቅ ዋሻ(Bunker)ሲወጡ ሰማዩን እንዲመለከቱና ማንኛውንም ድምፅ በትኩረት እንዲያዳምጡ እመክራለሁ፣የቀዩ ሰርግ ደጋሾች(Israel air force & Mossad) ዛሬም አሉ"ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ኢራን በቅርቡ 40 የሚጠጉ J-10C የተባለ የቻይና ስውር ተዋጊ አውሮፕላን መረከቧ የሚታወስ ነው።
(አዩዘሀበሻ)
======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s