Beshlo tube

Beshlo tube This pave non political and military. It gives services about social and economic advertisements

08/06/2022

የአንድ የዩኒቨርሲቲ መምህር የሆነ ፕሮፌሰር የሚከተለውን ድንቅ ጥናት እንዳገኘ በቅርቡ ይፋ አድርጓል !!

ጥናቱም የእንግሊዘኛ ፊደሎችን ከመጀመሪያው አስከመጨረሻው በቅደም ተከተል አስቀመጠ ። A b c d e f g h i j k l m n o p q r s t u v w x y z ። የነዚህን ፊደላት አሃዳዊ ቅደም ተከተል ኣስቀመጠ ። 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12 13 14 15 16 17 18 19 20 21 22 23 24 25 26

በጥናቱም ለያንዳንዱ ፊደላት በቁጥር ቅደም ተከተል ሚዛን ሰጠ ለ"A"=1 ፣ ለ"B"=2 ......... እያለ አስከ "Z" =26ን ሰጠ ። በመጨረሻም የቃላት ደረጃን መመዘን ያዘ ።

1.

(H+a+r+d+w+o+r+k)
(8+1+18+4++23+15++18+11)=98%

2. #እውቀት

(K+n+o+w+l+e+d+g+e)
(11+14+15+23+12+5+4+7+5)=96%

3. #ፍቅር

(L+o+v+e)
(12+15+22+5)=54%

4. #እድል

(L+u+c+k) = 47%
በዚህ መሰረት ከላይ የጠቀስናቸው ቃላት አንዳቸውም መቶ ፐርሰንት (100%)ለውጥ ሊሰጡ አንደማይችሉ አስቀመጠ ።
ታዲያ (100%) ሊሰጠን ሚችለው ጉዳይ ምንድን ነው? ገንዘብ ይሆን እንዴ ??

5. #ገንዘብ
(M+o+n+e+y)=(13+15+14+5+25)=72%
አይደለም ምን አልባት አመራር ይሆን ?

6. #አመራር

(L+e+a+d+e+r+s+h+i+p)
(12+5+1+4+5+18+19+8+9+16)=97% አሁንም አይደለም! ለሁሉም ነገራት መፍትሄ አለው ። አስተሳሰብ ፣ አካሄድ አኳኋናችንን ስንቀይር ይቀየራል ። ስለዚህ አስተሳሰብ ሁኔታን ሞከረ

7. #አስተሳሰብ (አመለካከት)

(A+t+t+i+t+u+d+e)
(1+20+20+9+20+21+4+5)=100%
የ100% ለውጥ ሊያመጣልን የሚችለው #የአስተሳሰብ ለውጥ መሆኑን አረጋገጠ ።

✅✅‼ ፌስቡክን ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም ፡፡ ማወቅ መልካም ነው ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው ፡፡ በምድር ላይ የምናደርጋቸው መልካም ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል ፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና ፡፡

✅✅‼ ስለዚህ አንተም ይህ አሁን ያነበብከው ፅሁፍ ትምህርት ሰጪ ሆኖ ካገኘሀው የእርስዎ ዘመዶችህ እንዲያነቡትና ትምህርት እንዲወስዱ ዘንድ ሼር ያድርጉላቸው ። ቻናላችንንም Join አድርገው ይቀላቀሉን ።👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q

06/06/2022

የኢትዮጵያ 86ቱ ብሄር ብሄረሰቦች ስም ያውቃሉ ?
እነሱም
1. ትግራይ
2. አፋር
3. አማራ
4. ኦሮሞ
5. ሶማሌ
6. ሲዳማ
7. አገው
8. ዎላይታ
9. ከምባታ
10. ሀዲያ
11. ጋሞ
12. ጉራጌ
13. ኢሮብ
14. አርጎባ
15. ቱለማ
16. ስልጤ
17. ሺናሻ
18. አኝዋክ
19. ኑዌር
20. ሀመር
21. ኩናማ
22. ጉምዝ
23. በርታ
24. በና
25. አሪ
26. ሙርሲ
27. ቡሜ
28. ካሮ
29. ፀማይ
30. ኮንሶ
31. ዳሰነች
32. ቦረና
33. ገርባ
34. አላባ
35. አርቦሬ
36. ባጫ
37. ቤንች
38. ባስኬቶ
39. ቡርጂ
40. ጫራ
41. ጋዋዳ
42. ጌዲኦ
43. ጊዶሌ
44. ጎፋ
45. አደሬ
46. ከፊቾ
47. ኮንታ
48. ኒያንጋቶም
49. ናኦ
50. ቀቤና
51. ሱርማ
52. ጠንባሮ
53. የም
54. ወርጂ
55. ዲዚ
56. ዶንጋ
57. ዳውሮ
58. ዲሜ
59. ምዓን
60. ኮሞ
61. ማረቆ
62. ሞስዬ
63. ኦይዳ
64. ቦዲ
65. ፈዳሼ
66. ኮሬ
67. ማሌ
68. ማኦ
69. መሰንጎ
70. መዠንገር
71. ቀዋማ
72. ቀጨም
73. ሸኮ
75. ዘየሴ
76. ዘልማም
77. ሽታ
78. ቤተ እስራኤል
79. ማሾላ
80. ኮጉ
81. ድራሼ
82. ገባቶ
83. ጌዲቾ
84. ብራይሌ
85. ሙርሌ
86. ኮንቶማ .... ናቸው።

ምንጭ - የኢትዮጵያ ታሪክ

በኔ አስተሳሰብ ግን ይሄ ውላ አላስፈላጊ ነገር ነው ብሄር የሚባል ነገር ባይኖር መልካም ነበር......አንድ ሀገር ብቻ ነበር መሆን ያለባት።
═══════❁✿❁ ═══════
📚📚🗞🗞 ለምርጥ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ። 👇👇👇👇👇https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q

Yesga waga bemechemeru hulum sew sga gezto lememegeb alchalem.Yihn yewaga chimari lemekenes tekamiwoch begara tederajite...
05/06/2022

Yesga waga bemechemeru hulum sew sga gezto lememegeb alchalem.
Yihn yewaga chimari lemekenes tekamiwoch begara tederajiten mn madreg alebn bemilew agenda ris lay enweyay
enweyayibet.

24/05/2022

🔶️?? 💠🔶️ ይነበብ

አንድ ትልቅ ድርጅት ውስጥ በትንሽ ደሞዝ ተቀጥሬ እሰራ ነበረ
በብዙ መስዋዕትነት ያገኘውት ስራ ስለሆነ እንደራሴ ስራ አድርጌ ጠንክሬ ያለ እረፍት እሰራ ነበረ።

ታዲያ የእዚህ ድርጅት ማናጀር እኔን ፍጽሞ አይወደኝም ነበረ ምክንያቱ ደግሞ እሱ ለሚያደርገቸው ለሙስና ስራዎች ተባባሪ ባለመሆኔ ነው
በዚህ የተናደደው የድርጅቱ ማናጀር በተጭበርበር ሰነድ እኔ ከድርጅቱ ብር የሰረኩ አስመስሎ ለድርጅቱ ባለቤት አሳየ።

የድርጅቱ ባለቤትም ወስዶ አሳሰረኝ ማናጀር እስር ቤት መጥቶ አያሽ አይደል እኔ #እንደዚህ ነኝ ብሎ ስቆብኝ ሄደ ስለ ራሴ መብት ለመከራከር ምንም አቅም ብር ሆነ ዘመድ አልነበረኝም ስለዚህ ያለ ምንም ጥፋቴ ሦስት ወር እስር ቤት ከቆየሁ በሓላ የድርጅቱ ባለቤት መጥቶ ከእስር ቤት አስፈታኝ።

ወንጀለኛ ነኝ አይደል ለምን አስፈታሀኝ ስለዉ ጥፋቱ የአንቺ አለመሆኑን ደርሼበታለሁ ይቅርታ ከዛሬ ጀምሮ አንቺ የድርጅቱ #ማናጀር ነሽ
እሱ ደግሞ በተራው እስር ቤት ይገባል እሱ ግን እንዳቺ #አይወጣም እዛው ይቀመጣል አለኝ።

አንተ/ቺ ብቻ ቅን ተማኝ ሰው ሁን/ኚ እንጅ የጠላት መሮጥ ላንተ ከፍታ ይሰጥሀል እንጅ መቼም ውድቀት አይሆንም።

ትንሽ ችግር ሲደርስ ቅን በመሆኔ ነው አይደል እንደዚህ የሆንኩት ብላችሁ አትማረሩ ፈጣሪ ለፍርድ አይቾክልምና በተቻለ መጠን ቅን ለመሆን ሞክሩ ።
============================
✅✅‼ አዳዲስና ትምህርት ሰጪ የሆኑ ፅሁፎች በየቀኑ በቴግራም እንዲደርሳችሁ ትፈልጋላችሁ እንግዲያውስ ይሄ ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ነው ግቡና Join አድርጉን ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q

24/05/2022

ሴት ልጅ በጣም የምትጠላው ነገር
1♦ከሌሎች ሴቶች ጋር የሚያወዳድራትን ወንድ አትወድም ።

2♦አውቆ እንድትቀና የሚያደርጋት ወንድ አትወድም

3♦ከራሱ ጋር የሚያፎካክራት እራሱን ከፍ አድርጎ እሷን ዝቅ የሚያደርጋት ለምሳሌ እኔ ወንድ ነኝ አንቺ ሴት ነሽ የሚላትን አትወድም ።

4♦ ሴት ልጅ የሚዋሻትን ወንድ ትጠላለች ምንም ሆንክ ማንም እውነቱን ንገራት አትዋሻት በእውነታኛነትህ ትወደሀለች
♥ሴት ልጅ ሰነፍ ወንድ አትወድም
♥ሴት ልጅ በራስ መተማመን የሌለውን ወንድ አትወድ
♥ሴት ልጅ እራስ መተማመኑ እጅግ የገነነ ሰዎችን የሚንቅ ወንድ አትወድም ስለዚህ ሁሉን በልክ አድርገው ።

5♦ሴት ልጅ በስሜቷ የሚጫወት ወይም የጊዜ ማሳለፍያ የሚያደርጋት ወንድ ትጠላለች ምክንያቱም ስሜቷ እውነተኛ ስለሆነ

6♦ሴት ልጅ ክብሯን ቤተሰቧን የሚነካባት ወንድ አትወድም ምክንያቱም ለቤተሰብ ቅርብ ነች

7♦ሴት ልጅ ድምፁን ከፍ አድርጎ የሚያወራትን የሚሰድባትን የሚመታትን ወንድ
እሷ ላይ ወንድ መሆን የሚፈልግን ወንድ አትወድም ለሷ ወንድ የሆነውን እንጂ
═════════❁✿❁ ═════════
============================
✅✅‼ አዳዲስና ትምህርት ሰጪ የሆኑ ፅሁፎች በየቀኑ በቴግራም እንዲደርሳችሁ ትፈልጋላችሁ እንግዲያውስ ይሄ ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ነው ግቡና Join አድርጉን ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q

24/05/2022

ሙዝ ለጤና የሚኖረው 15 ጠቀሜታዎች

1. ጥርስን ያነጣል!!
ጥርስዎን ሁልጊዜ ሲቦርሹ ለሁለት ደቂቃ ያህል በሙዝ ልጣጭ/ልጫ ጥርስዎን ይሹት ከዚያም አስደናቂ ለውጥ ያገኙበታል።

2. በተለያዩ ነፍሳቶች ሲነከሱ ቁስልዎን ያስታግስልዎታል!!
ነፍሳቱ የነከስዎት ቦታ ላይ በሙዝ ልጫ በማሸት የሚኖረውን እብጠትና ህመም መቀነስ ይቻላል።

3. የተጎዳን የሰውነት ቆዳን ያስተካክላል!!
ሙዝ የተበላሸ ወይም የተጐዳ የፊት ቆዳን በሚያምር አዲስ የፊት ቆዳ የመተካት ምትሀታዊ ሀይል አለው።

4. ለእፅዋት ማዳበሪያነት ያገለግላል!!
ደረቅ የሙዝ ልጫ ተወዳዳሪ የሌለው የአትክልትና እፅዋት ማዳበሪያ ነው።

5. የፊት መሸብሸብ ወይም መጨማደድን ይከላከላል!!
ሙዝ ከፍተኛ የክሬምና የተፈጥሮ ማር ካላቸው ምግቦች የሚመደብ ሲሆን አንዳንድ ሴቶች የፊት መሸብሸብን ለመከላከል ሲሉ ከሙዝ የተሰሩ የፊት ክሬሞችን በሳምንት ለ3 ጊዜ ያህል ይጠቀማሉ።

6. የቆዳ መሰንጠቅን ይከላከላል!!
የሰውነት ቆዳዎ እያሳከክዎትና እየተሰነጣጠቀ ተቸግረዋል? ህመምዎ(ችግርዎ) ይገባኛል፤በጣም እድለኛ ነዎት!! እንደዚህ ያድርጉ የተሰነጠቀውን የሰውነትን ቆዳ በሙዝ ልጫ(ልጣጭ) ይሹት እንደዚያ ሲያደርጉ በሙዙ ልጫ ላይ ያለው ተፈጥሮአዊ ኢንዛይም በተሰነጠቀው ቆዳዎ ላይ በመግባት ስራውን ይሰራል ማለት ነው።

7. ጥሩ የአይስክሬም መስሪያ ነው!!
በጣም ጣፋጭ ነገር ይወዳሉ? ነገር ግን ለማዘጋጀት ጊዜ ወይም ገንዘብ የለዎትም? እንግዲውስ እንዲህ ያድርጉ በጣም የቀዘቀዘ ሙዝ ቆራርጠው ወደ አይስክሬም መስሪያ ያስገቡት ከዚያም አስደናቂ ጣዕም ያለው አይስክሬም ይመገባሉ።

8. ክንታሮትን ያድናል!!
ሙዝ በፓታሲየም የበለጸገ ነው። ይህ ንጥረ ነገር ክንታሮትን የማዳን አቅም አለው ስለዚህ ሙዝ ተፈጥሮአዊ የክንታሮት መድሀኒት ሆኖ ያገለግላል።

9. ሰውነታችን በስለት ሲቆረጥ ወይም ሲያብጥ የማዳን ሀይል አለው!!
ሙዝ ሰውነታችን በግጭት ወይም በሌላ ምክንያት ሲያብጥ ወይም ስለት ነገር ሲቆርጠን በውስጡ ፓታሲየም የተባለ ንጥረ ነገር ስላለው ሰውነታችን ለማገገም የሚያደርገውን ሂደት ያግዛል ወይም ያፋጥነዋል።

10. ሙዝ ወፎችንና ቢራቢሮዎችን የመሣብ ሀይል አለው!!
ወፎችንና ቢራቢሮዎች ልክ እንደሠው ልጅ ሁሉ የሙዝን ቃና በጣም ይወዱታል።ስለዚህ ሙዝ ይህን ያህል የመሣብ አቅም ስላለው ወፎችን የመመልከት ፍላጎት ካለዎት በአካባቢዎ ሙዝ ይጣሉላቸው ከዚያም በአስደናቂው ቃና ወደርስዎ ይስባሉ።

11. የቆዳ ውጤቶችንና የብር ጌጣጌጦችን (silver) ያፀዳል!!
የቆዳ ዉጤቶችንና ከብር የተሰሩ ጌጣጌጦችን ለማፅዳት ለመርዛማ ኬሚካሎችን ለመግዛት ገንዘብዎን አያጥፉ በምትኩ በሙዝ ልጫ(ልጣጭ) በደንብ ካሹት በኋላ በጨርቅ ይጥረጉት።

12. ሙዝ በፀረ-ተባይ መድሀኒትነት ያገለግላል!!
ማንም ሰው ቢሆን እፅዋት ተጎድተው ማየት አይፈልግም!! የሙዝ ልጫን ቆራርጠው በእፅዋቱ አካባቢ ከ6-7 ሳ.ሜ አርቀው ይቅበሩዋቸው ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአካሎቹ ላይ ያሉት ተባዮች ይሞታሉ።

13.የውሻን በሽታ ይከላከላል!!
በፍቅር የሚወድዎትን ውሻዎ በቀላሉ ጤናውን ይጠብቅልዎታል።

14. ውሀን ያጣራል!!
የተለያዮ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የሙዝ ልጫ/ልጣጭ በወንዝ ውሀ ውስጥ የሚገኙትን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን መጦ የመያዝ አቅም አለው።

15. በሽታ የመከላከል አቅምዎን ይጨምራል።
============================
✅✅‼ አዳዲስና ትምህርት ሰጪ የሆኑ ፅሁፎች በየቀኑ በቴግራም እንዲደርሳችሁ ትፈልጋላችሁ እንግዲያውስ ይሄ ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ነው ግቡና Join አድርጉን ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q

24/05/2022

#ሃያ ሶስቱ የማኅበራዊ ሕግጋቶች

1. 🟣 ይሰለቹሃል
አስሬ አትደውል ፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም ። ተሰልቺ ትሆናለህ!

2. 🔻'ሼም ነው' ነው
የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!

3.🔺 አይባልም
"እንዴ እስካሁን አላገባሕም ? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው ? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ " አይባልም ።

4.🔷 ክፈል
አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል ። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ ።

5.🔴 ነውር ነው
ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር ፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ ።

6.⚫ አታቋርጥ
ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ ። ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው ።

7. 🔶አታብሽቅ
ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው ። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው ። ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ ።

8.🔵 አመሥግን
ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር ሰዎችን አመሥግን ማመስገን ግድ ነውና ።

9.🟠 ያለስስት አድንቅ
ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው ፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል ምከራቸው ።

10. 🔺ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ
ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው ። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ ።

11. 🔻ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ
ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል ። የውጤቱን ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው ። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል ።

12. 🟤 ስነ ስርዓት
ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው ።

13. 🙏ክብር ለሁሉም
ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው ። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም ።

14. 📱ስልክህን አስቀምጥ
ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው ። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው ።

15.🔴 አድብ
ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው ።

16. 🚫 ተቆጠብ
ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው ። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ ።

17. መነጽርህን አውልቅ
ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ ። ክብርም ነው!

18.⛔ አትሳሳት
በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ ።

19. Ⓜ️ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው ። ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው ።

20.💠 ዕቃ መልስ
የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ ።

21.🔷 አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉህ
የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው ። ሌሎች እንዲወያዩበትና እንዲተቹት ክፍት አድርገው ፤ አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ ። ነገርህን ደገፉትም አልደገፉት ምንጊዜም ቢሆን ላነሳኸው ሐሳብ ጥሩ ግብዓት አይጠፋም ። ልክ አልሆን ወይ እያልክ ወይም ሐሳቤ ያንስ ይሆን ወይ ብለህ አትሸማቀቅ ፤ ተሸማቀህ ትቀራለህ!

22🔴 ሴት ልጅ ታናሽህም ትሁን ታላቅህ ተገቢውን ክብር ስጣት ። ሴትን ማክበር እናት ፣ እህትና ሚስትን ማክበር ነውና ።

እባካችሁ ለሌላም ሰው ሼር አድርጉለትና ከዚህ ችግር እንዲወጣ አድርጉለት
============================
✅✅‼ አዳዲስና ትምህርት ሰጪ የሆኑ ፅሁፎች በየቀኑ በቴግራም እንዲደርሳችሁ ትፈልጋላችሁ እንግዲያውስ ይሄ ትክክለኛ የቴሌግራም ቻናላችን ነው ግቡና Join አድርጉን ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q

Address

Yeka
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Beshlo tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Beshlo tube:

Share