Biruh Entertainment

Biruh Entertainment Biruh Entertainment is Ethiopian social media New Media channel and website News. Documentary Tourism Travel Entertainment Information and more Video everyday

BIRUH ENTERTAINMENT
Ethiopian social media New Media channel and website News.

የወንዶች ጉዳይ ………..መጡ በአዲስ ጉዳይ? አዎ! ከጥቂት ቀናቶች በኋላ ከናንተ ጋር!
26/08/2025

የወንዶች ጉዳይ ………..መጡ በአዲስ ጉዳይ? አዎ! ከጥቂት ቀናቶች በኋላ ከናንተ ጋር!

ቻናል ዋን መደበኛ ስርጭቱን እሁድ ነሐሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ይጀምራል ።ኢትዮ-ሳት ላይ በ 11545 H 45000 ፍሪኩዌንሲ ስካን በማድረግ ቻናል ዋንን በጥራት እንከታተል! #አንድ...
24/08/2025

ቻናል ዋን መደበኛ ስርጭቱን እሁድ ነሐሴ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ይጀምራል ።
ኢትዮ-ሳት ላይ በ 11545 H 45000 ፍሪኩዌንሲ ስካን በማድረግ ቻናል ዋንን በጥራት እንከታተል!
#አንድለእኛ

በኢትዮጵያዊያ የሀበሻ ባህል ልብስ ተዉበዉ ገቡከሀምሌ 20 እስከ 25 ቀን 2017  የተባበሩት መንግሥታት ሥርዓት ምግብ ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ይካሄዳል ።ከ4ሺህ 700...
27/07/2025

በኢትዮጵያዊያ የሀበሻ ባህል ልብስ ተዉበዉ ገቡ

ከሀምሌ 20 እስከ 25 ቀን 2017
የተባበሩት መንግሥታት ሥርዓት ምግብ ጉባኤ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ይካሄዳል ።

ከ4ሺህ 700 ተሳታፊዎች በሚኖሩት በዚህ ጉባኤ በስብሰባው ለመታደም ከገቡ ሀገራት የ51 ዓመቷ የኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ ቅዳሜ ከሰአት በኋላ የገቡ ሲሆን አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ የባህላዊ አለባበስ መገለጫ የሆነውን የሀበሻ ቀሚስ የባህል ልብስ ጥለቱ የኡጋንዳን ብሔራዊ ሰንደቅ አላማን ቀለም ያለበት ለብሰዉ ነዉ የገቡት ።

ከአውሮፕላኑ ሲወረዱ የተነሱት ፎቶ
Biruh Entertainment

ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን (ዶ/ር) ሐምሌ  2 ቀን 2017 ዓ.ም በሚኖርበት አሜሪካ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል።ሥርዓተ ቀብሩ ነገ ቅዳሜ  ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ...
25/07/2025

ጋዜጠኛ ታደሰ ሚዛን (ዶ/ር) ሐምሌ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በሚኖርበት አሜሪካ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ይታወሳል።

ሥርዓተ ቀብሩ ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ቤተሰቡ እና ወዳጆቹ በተገኙበት አራት ኪሎ በሚገኘው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል::

ቤተሰቦቹ
ነፍስን በአፀደ ገነት ያኑራት🙏

5 ሚሊየን ብር የወጣበት የድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ 4ተኛ የሙዚቃ አልበም ተለቀቀ“ቅን” የተሠኘው የድምፃዊ የግጥምና ዜማ ደራሲ አቤል ሙሉጌታ 4ተኛ የሙዚቃ አልበም በድምፃዊው የዩቱብ ቻናል  ላ...
20/07/2025

5 ሚሊየን ብር የወጣበት የድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ 4ተኛ የሙዚቃ አልበም ተለቀቀ

“ቅን” የተሠኘው የድምፃዊ የግጥምና ዜማ ደራሲ አቤል ሙሉጌታ 4ተኛ የሙዚቃ አልበም በድምፃዊው የዩቱብ ቻናል ላይ ተለቋል ።

ይህ በርካታ የሀገራችን የሙዚቃ ባለሙያዎችን ያሳተፈውና የሀገራዊ፣የማህበራዊ፣የፍቅር፣የፍልስፍናና ታሪካዊ ጉዳዮችን የሚያነሳው የሙዚቃ አልበም በዛሬው እለት ለአድማጮች በራሱ የአቤል ሙሉጌታ የዩቲዩብ ቻናል ተለቋል ።

የድምፃዊ የግጥምና ዜማ ደራሲ አቤል ሙሉጌታ 4ተኛ አልበም 14 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ስራውን ሰርቶ ለማጠናቀቅም 5 ዓመታትን መውሰዱ ተነግሯል፡፡

የሁሉም ትራኮች ግጥምና ዜማ በራሱ በድምፃዊው በአቤል ሙሉጌታ ሲሰሩ በቅንብር ካሙዙ ካሳ፣አቤል ጳውሎስ፣ታምሩ አማረ፣አዲስ ፍቃዱ፣ሮቤል እንዳለ፣አብርሃም ኪዳኔና ሙሳ ማቲ በሚክሲንግ ሰለምን ሃ/ማርያም፣አቤል ጳውሎስና አብርሃም ኪዳኔ በማስተሪንግ ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል፡፡

ሙያዊ ውይይት “ ” ሁሉም እንዲታደም ተጋብዟል!  #ቅዳሜ፣  ፣ 2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ይጀምራልአወያይ÷ ሔኖክ አየለ አቅራቢዎች÷•  ቤዛ ኃይሉ•  ሙሴ አበባየሁ ጌትነትአዘጋጅ:- የኢት...
17/03/2025

ሙያዊ ውይይት “ ”

ሁሉም እንዲታደም ተጋብዟል!

#ቅዳሜ፣ ፣ 2017 ዓ.ም
8፡00 ሰዓት ይጀምራል

አወያይ÷ ሔኖክ አየለ

አቅራቢዎች÷
• ቤዛ ኃይሉ
• ሙሴ አበባየሁ ጌትነት

አዘጋጅ:- የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነ ጥበባት ማዕከል

አድራሻ፦ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ (በንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል ገባ ብሎ)፡፡

ትራንስፖርት፡ ከፒያሳ/ማስታወቂያ አካባቢ 7፡30 ላይ የሚነሳ ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል፡፡-

ለበለጠ መረጃ እና መገኘትዎን ለማረጋገጥ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
https://t.me/+VZQIhKm-NoAwYjM0

በራሳችሁ ለምትመጡ አድራሻው፤ Ethiopian Academy of Sciences
ጎግል ማፕ፡ https://maps.app.goo.gl/GwKfjcwg1jmqsfG76
በፒያሳ በኩል ከመጡ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ እንዳሉ ወደ ቀኝ የሚታጠፈውን ሁለተኛውን ቀጭን የአስፓልት መንገድ ይዘው 500 ገባ ይላሉ፤ በውንጌት በኩል የሚመጡ ከሆነ መድሐኒያለም ትምህርት ቤትን እንዳለፉ በሚያገኙት የመጀመሪያው ቀጭን የአስፓልት መንገድ ወደ ግራ ታጥፈው 500 ሜትር ገባ ይላሉ፡፡

አዝናኙ ሲዝናና ሚዲያ ካፕ የ13 ዓመታ ጉዞ
10/03/2025

አዝናኙ ሲዝናና ሚዲያ ካፕ የ13 ዓመታ ጉዞ

"ከትዳር በላይ"100 ዓመት ያለፈው የቲአትር ታሪካችን ዛሬ ያለበት ሁኔታ ያሳስባል።"ከትዳር በላይ"የተቀዛቀዘውን ቲአትር በእጅጉ ሊያነቃቃ መምጣቱን ሰሞኑን ያለው የጥበብ ቤተሰቦች ርብርብ ያ...
28/02/2025

"ከትዳር በላይ"
100 ዓመት ያለፈው የቲአትር ታሪካችን ዛሬ ያለበት ሁኔታ ያሳስባል።
"ከትዳር በላይ"የተቀዛቀዘውን ቲአትር በእጅጉ ሊያነቃቃ መምጣቱን ሰሞኑን ያለው የጥበብ ቤተሰቦች ርብርብ ያሳየናል።
እየተዝናናን( እየሳቅን) ልናየው የተዘጋጀው ይህ ኮሜዲ ቲአትር በርካታ ባለሙያዎችን አሳትፏል።
በነገራችን ላይ ጸሐፊ ተውኔቱ፣ አዘጋጁ ፣ፕሮዲዩሰሯ መርጠው የሚሠሩና የሚሳካላቸው ባለሙያዎች ናቸው።

በከፍተኛ ዝግጅት የተሰናዳው ይህ ኮሜዲ ቲአትር በግል የሚሠሩ እና በቲአትር ቤት ቅጥር ሆነው የሚሠሩ ተዋናያን ተጣምረውበታል።


በተለያዩ የመድረክ፣ የፊልም እና የቴሌቭዥን ምርጥ ሥራዎቿ የምትታወቀው ተዋናይት መስከረም አበራ ፕሮዲዩስ አድርገዋለች። ጸሐፊ ተውኔት ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ተጽፎ በዳግማዊ ዓመለወርቅ ፈይሳ የተዘጋጀው "ከትዳር በላይ" የተሰኘው ኮሜዲ ቴያትር ዝነኞቹ ተዋንያን ሽዋፈራው ደሳለኝ ፣መስከረም አበራ ፣ ቸርነት ፍቃዱ ፣መዓዛ ገ/ሕይወት ፣ የማታወርቅ ታደሰ ተሳትፈውበታል።

በመግለጫው እንደተገለጸው ከትዳር በላይ ኮሜዲ ቲአትርየ ለሙያው መደረግ የሚገባውን ሥነ ምግባር በመከተል የተሠራ በመሆኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ደፍረው ሂስ እንዲሠሩበት ተጋብዝዋል። ቲአትሩ በአዲስ መልክና በተሻለ መልኩ በመሠራቱ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶበታል።

በተጨማሪም የትያትሩ ጽሑፍ በተደጋጋሚ ታርሞ ለ2 ወር የተጻፈና በአዲስ አበባ የባህል ማዕከልና ዓለም ሲኒማ 3ወር ልምምድ እንደተደረገበትም ተገልጿል።

ከትዳር በላይ ኮሜዲ ቴያትር የኮሜዲ ዘውግ ያለው ሲሆን ሳቅ የሚያስጭር ብቻ ሳይሆን ቁምነገርም የሚጨበጥበት እንደሆነ ተነግሯል።

የትያትሩ መግቢያ 1000 ብር ሲሆን ይህ ዋጋ ግን ለምርቃቱ ጊዜ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

በተጨማሪም ትያትሩን በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ለማሳየት እቅድ ተይዟል።
በቅርብም ሚያዚያ ላይ እስራኤል ሀገር እንደሚታይ ተነግሯል።
ቲኬቱ ሁሉ በእጄ መተግበሪያ የሚገኝ ሲሆን VIP ከ5000 ብር በላይ መግዛት እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን ከ50 ወንበሮች መካከል የተወሰኑት መሸጣቸውን እየተመለከትን ነው።
እናም VIP ካርዱን ለማግኘት +251 922 541776 እና +251 713 927054 ላይ በመደወል መግዛት ይቻላል።
ለሁሉም ባለሙያዎች ከፍተኛ ክብር ይገባቸዋል።

አባይ ቴሌቭዥን መቅደስ ደበሳይን አሰፈረመ!ተወዳጇ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ መቅደስ ደበሳይ ዓባይ ቴሌቪዥንን በይፋ ተቀላቀለች፡፡በመዝናኛው ዘርፍ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በኢትዮጵያ ውስጥ ተወ...
24/02/2025

አባይ ቴሌቭዥን መቅደስ ደበሳይን አሰፈረመ!

ተወዳጇ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ መቅደስ ደበሳይ ዓባይ ቴሌቪዥንን በይፋ ተቀላቀለች፡፡

በመዝናኛው ዘርፍ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በኢትዮጵያ ውስጥ ተወዳጅነትን ካተረፉ የመዝናኛ ዝግጅት አቅራቢዎች መካከል ስሟ የሚጠራው መቅደስ ደበሳይ ዓባይ ቲቪ በይፋ ተቀላቅላለች፡፡

በቴሌቪዥን የመዝናኛ መሰናዶ የተመልካቾችን ቀልብ በሚስብ ድንቅ አቀራረብ ላለፉት ዓመታት አድናቆት የተቸራት መቅደስ ዓባይ ቴሌቪዥንን በመቀላቀሏ የተሰማትን ደስታ ገልጻለች፡፡

ዝነኛዋ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ መቅደስ ዓባይ ቴሌቪዥንን መቀላቀሏን ይፋ ስታደርግ ከቴሌቪዥን ጣቢያው ስራ አስኪያጅ አቶ ግሩም ይልማ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርማለች፡፡

በስምምነት ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረገጉት የዓባይ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅ አቶ ግሩም ይልማ ‹‹ስርጭት ከጀመረ ሶስት ዓመታትን ያስቆጠረው ዓባይ ቴሌቪዥን በእነዚህ ጥቂት ዓመታት ሰፊ ህዝብ ጋር በመድረስ ተወዳጅነትን በማትረፍ ትልቅ ስኬት ላይ ደርሷል›› ብለዋል፡፡

‹‹ዓባይ ቴሌቪዥን አሁንም በተጨማሪ ከፍታ ለመምጣት በርካታ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ከመቅደስ ጋር በመገናኘታችን እጅግ በጣም ደስተኛ ነን›› ሲሉም አቶ ግሩም አክለዋል፡፡

ዝነኛዋ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢ መቅደስ ደበሳይ በበኩሏ ‹‹ተወዳጁ ዓባይ ቴሌቪዥን በቤተሰባዊነት ስሜት ስለተቀበለኝና ይህንን ስምምነት ስላደረግኩ በጣም ደስ ብሎኛል፡ ስለተማመናችሁብኝ ከልቤ አመሰግናለሁ›› ብላለች፡፡
Abbay TV

Pandora Dubai 🇦🇪VIP ትኬት በ400,000ብር!በፈረንጆቹ አቆጣጠር በጃንዋሪ 16 በፖንዶራ ዱባይ የሚዘጋጀው የስመጥሩ ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ የሙዚቃ ዝግጅት የVIP ቦታ 24 ሰዓት ባ...
11/01/2025

Pandora Dubai 🇦🇪
VIP ትኬት በ400,000ብር!

በፈረንጆቹ አቆጣጠር በጃንዋሪ 16 በፖንዶራ ዱባይ የሚዘጋጀው የስመጥሩ ድምፃዊ ኤፍሬም ታምሩ የሙዚቃ ዝግጅት የVIP ቦታ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያውያን የሙዚቃ ዝግጅት ታሪክ በዱባይ ሪከርድ በሆነ ዋጋ ብር 400,000 ተሽጦ ማለቁ አነጋጋሪ ሆኗል::

አርቲስት መሀሙድ አህመድ  (  የክቡር ዶክተር)  ካሁን ቀደም ያልተሰሙ የህይወቱን ገጽታዎች አካቶ የተሰናዳው መጽሀፉ ትላንት ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም በማሪዮት ሆቴል ለምረቃ በቅቷል።ለዝግ...
11/01/2025

አርቲስት መሀሙድ አህመድ ( የክቡር ዶክተር) ካሁን ቀደም ያልተሰሙ የህይወቱን ገጽታዎች አካቶ የተሰናዳው መጽሀፉ ትላንት ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም በማሪዮት ሆቴል ለምረቃ በቅቷል።

ለዝግጀት 10 ዓምታትን የወሰደው መጽሐፉ፣ የክቡር ዶክተር አርቲስት መሀሙድ አህመድ ካሁን ቀደም ያልተሰሙ የህይወቱን ገጽታዎችን የያዘ ሆኖ የተሰናዳ ስለመሆኑ ደራሲው ወሰን ደበበ ማንደፍሮ ተናግሯል።

የክቡር ዶክተር አርቲስት መሀሙድ አህመድ ላለፉት 63 ዓመታት በሙዚቃው ዓለም ያሳለፋቸዉን ውጣ ውረዶች፣ የቤተሰብ የኋላ ታሪክና የወዳጅ ጓደኞቹን እንዲሁም የሙያ ባልደረባዎቹን ምስክርነት አካቶ የያዘው የሕይወት ታሪክ መፅሐፍ በጋዜጠኛና ደራሲ ወሰን ደበበ ማንደፍሮ ተዘጋጅቶ በንብ ኢንተርናሽናል ባንከ አማካኝነት ታትሞ ለንባብ ተዘጋጀቶዋል።

ንብ ባንክ በ3.5 ሚሊዮን ብር ሕትመቱን ስፖንሰር ማደርጉ ተገልጿል።

ኢንጂነር ቢጃናይ እና ዶ/ር ሐውለት አሕመድ 500 መጽሐፍትን በ2.5 በሚሊዮን ብር ገዝተዋል፣ የሰንሻይን ሪል ስቴት ባለቤት አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በበኩላቸው በ500 ሺ ብር 100 መጽሐፍትን ገዝተዋል።

ታላቁ የፊልም ሰው. . .EBS ቅዳሜ መዝናኛ ከሚሶ ነጋያ ጀምሮ በርካታ የሙዚቃ ክሊፖችን ዳይሬክት በማድረግ የምናውቀውን ስንታየሁ ሲሳይን እንግዳ አድርጎ አቅርቦ ነበር ።በአሁን ጊዜ ያለበት...
06/10/2024

ታላቁ የፊልም ሰው. . .
EBS ቅዳሜ መዝናኛ ከሚሶ ነጋያ ጀምሮ በርካታ የሙዚቃ ክሊፖችን ዳይሬክት በማድረግ የምናውቀውን ስንታየሁ ሲሳይን እንግዳ አድርጎ አቅርቦ ነበር ።
በአሁን ጊዜ ያለበት አሳዛኝ የኑሮ ፈተናንም ለህዝብ አድርሷል ።
https://youtu.be/VuwCj7pCom8?si=1bomNf_L-F0FALjf

Wasihune Tesfaye ተከታዩን ፅሁፍ ስለ ስንታየሁ አጋርቷል ።

ታላቁ የፊልም ሰው. . ...
ከጥቂት ጊዜያት በፊት ፡ ቦሌ ላይ ፡ በዘመናዊ ካሜራዎችና ፡ የስቱዲዮ እቃዎች የተሞላ የትልቅ ስቱዲዮ ባለቤት የነበረ ፡ ልጆቹን ዘመናዊ ትምህርት ቤት ያስተምር የነበረ. . በኢትዮጵያ ውስጥ ቁጥር አንድ የፊልም ዳይሬክተር ..ስንታየሁ ሲሳይን የሚያክል ሰው . ህይወት ጋደል ብላበት የቤት ኪራይ የሚከፍለው አጥቶ ሲቸገር አስባችሁታል ?....
መኪናውን ሽጦ ፡ ከሰው ተበድሮ ፡ እንደምንም ብሎ ልጆቹን ለማስተማር ሞክሮ በመጨረሻ ግን አቅቶት የዚህ ጎበዝ ልጅ. ልጆቹ የትምህርት ቤት የሚከፍሉት አጥተው. .. በዚህ ዘመን እቤት ለመዋል ሲገደዱ. .ማሰብ ይከብዳል ።
...ግን ምን ይደረግ ህይወት አንዳንዴ ፊቷን ታዞር የለ ፡ ስንታየሁንም የገጠመው ይሄ ነገር ነው ።
ስንታየሁ ሲሳይን የሚያክል ታላቅ ባለሙያ በዚህ መልኩ ህይወት ከብዶት ሰው ፊት ሲቆም ያሳዝናል ። .....
ይህ ታላቅ የጥበብ ሰው በውጭ ሀገር ቢሆን ፡ ቪዲዮዎቹን የሚቀርፀው በራሱ ሄሊኮፕተር ይሆን ነበር ። አልሆነም ። ስንታየው ፡ ዛሬ የኛን ድጋፍ የሚፈልግበት ጊዜ ላይ ነው ። ይህ ጎበዝ ሰው ዳግም በእግሩ ቆሞ የተለመዱ ስራዎችን እንዲያበረክት የወገን እገዛ ይፈልጋል ። ...
ለተባበረ ወገን ስንታየሁን ወደቀድሞ ከፍታው ላይ እንዲሆን ማገዝ ቀላል ነው ። አለሁ እንበለው ፡ አነሰ በዛ ሳንል ተባብረን የምንጥላት እያንዳንዷ ጠጠር ፡ ይህንን ታላቅ ባለሙያ ዳግም ወደካሜራው መመለስ ይችላል ።
1000351511285 - ስንታየሁ ሲሳይ CBE...
ከጥቂት ጊዜያት በፊት ፡ ቦሌ ላይ ፡ በዘመናዊ ካሜራዎችና ፡ የስቱዲዮ እቃዎች የተሞላ የትልቅ ስቱዲዮ ባለቤት የነበረ ፡ ልጆቹን ዘመናዊ ትምህርት ቤት ያስተምር የነበረ. . በኢትዮጵያ ውስጥ ቁጥር አንድ የፊልም ዳይሬክተር ..ስንታየሁ ሲሳይን የሚያክል ሰው . ህይወት ጋደል ብላበት የቤት ኪራይ የሚከፍለው አጥቶ ሲቸገር አስባችሁታል ?....
መኪናውን ሽጦ ፡ ከሰው ተበድሮ ፡ እንደምንም ብሎ ልጆቹን ለማስተማር ሞክሮ በመጨረሻ ግን አቅቶት የዚህ ጎበዝ ልጅ. ልጆቹ የትምህርት ቤት የሚከፍሉት አጥተው. .. በዚህ ዘመን እቤት ለመዋል ሲገደዱ. .ማሰብ ይከብዳል ።
...ግን ምን ይደረግ ህይወት አንዳንዴ ፊቷን ታዞር የለ ፡ ስንታየሁንም የገጠመው ይሄ ነገር ነው ።
ስንታየሁ ሲሳይን የሚያክል ታላቅ ባለሙያ በዚህ መልኩ ህይወት ከብዶት ሰው ፊት ሲቆም ያሳዝናል ። .....
ይህ ታላቅ የጥበብ ሰው በውጭ ሀገር ቢሆን ፡ ቪዲዮዎቹን የሚቀርፀው በራሱ ሄሊኮፕተር ይሆን ነበር ። አልሆነም ። ስንታየው ፡ ዛሬ የኛን ድጋፍ የሚፈልግበት ጊዜ ላይ ነው ። ይህ ጎበዝ ሰው ዳግም በእግሩ ቆሞ የተለመዱ ስራዎችን እንዲያበረክት የወገን እገዛ ይፈልጋል ። ...
ለተባበረ ወገን ስንታየሁን ወደቀድሞ ከፍታው ላይ እንዲሆን ማገዝ ቀላል ነው ። አለሁ እንበለው ፡ አነሰ በዛ ሳንል ተባብረን የምንጥላት እያንዳንዷ ጠጠር ፡ ይህንን ታላቅ ባለሙያ ዳግም ወደካሜራው መመለስ ይችላል ።
1000351511285 - ስንታየሁ ሲሳይ CBE

Saturday afternoon infotainment show with magazine format; lifestyle, tea time guests, book review, music, cooking segment, and many more…, every Saturday at...

Address

Kirkos
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Biruh Entertainment posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share