Gitsawe ግጻዌ

Gitsawe ግጻዌ ግጻዌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የየዕለ?

ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኡል ፡ ታኅሣሥ 19ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘን...
28/12/2021

ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኡል ፡ ታኅሣሥ 19

ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ምክንያቱም ያዘኑትን ለማፅናናት የምስራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ያላካልና፡፡

ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔርን ልጅ የሚመስል ጌታና አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ሰማዕታት ገድላቸውን እንዲፈፅሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደ ኋላ እንዳይመለሱ ይረዳቸዋል፡፡

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን የቅዱሳን መላዕክትን ወርሃዊና ዓመታዊ በዓላቸውን በፀሎትና በምስጋና ታከብራለች፤ በተለይ ታህሳስ 19 ቀን የሚከበርበት ምክንያት ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ከዕቶን እሳት ያዳነበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡

በጣዖት ፍቅር እጅግ ያለመጠን ልቡ ተቃጥሎ የነበረው የባቢሎን መሪ ነቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ወርዱ ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቅ ምስል አሰርቶ መኳንንቱን ሰብስቦ ሕዝቡ በሙሉ ለጣዖቱ እንዲሰግድ አዋጅ አወጀ፡፡ ያ ዘመን ለእግዚአብሔር ወዳጆች የፈተና ዘመን ነበር፡፡ አስመሳዮች ለጣዖት ሰገዱ፤ ተረበረቡ፡፡ እውነተኛ አማኞች ግን በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት ‹‹ ንጉስ የወደደው፣ ጊዜ የወለደው›› በሚል አስተሳስብ አይለወጥም፡፡ በዚያ ፈታኝ ዘመን ነበር ሶስት ታማኝ የእግዚአብሔር ባለሟሎች የተገኙት፡፡
ንጉሱ ላቆመው ጣኦት ያልሰገደ ወደ እቶን እሳት ተጥሎ እንደሚሞት ቁርጥ ውሳኔው መሆኑን ወጣቶቹ በሚገባ ያውቁታል ግን ይህንን አልፈሩም፡፡ ንጉስ ሆይ አምላካችንን ክደን አንተ ላቆምከው ጣዖት አንሰግድም አሉት፡፡ ሶስቱ ወጣቶች የወሰዱት ይህ አቋም ለንጉሱ ታላቅ ራስ ምታትን ፈጠረ፤ ንጉሱም አገልጋዮቹን ጠርቶ እሳቱ ሰባት እጥፍ እንዲነድ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

እሳቱም ሰባት እጥፍ ነደደ፡፡ ወዲያውኑ የንጉሱ አገልጋዮች አናንያ ፣ አዛርያን እና ሚሳኤልን እያንከበከቡ ወደ ዕቶን እሳቱ ወረወሯቸው፡፡ በእሳቱ ሀይል የተነሳ አገልጋዮቹም በእሳቱ እየተጠለፉ እንደ ማገዶ ነደዱ፡፡ ሠልስቱ ደቂቅ ግን ከየት እንደመጣ ከማይታወቅ እንግዳ ጋር በመሆን በዕቶን እሳት ውስት ይንሸራሸሩ ጀመር፡፡ ይህ ተዓማራት ንጉሱንና መኳንንቱን አስገረመ፡፡ ንጉሱም በዚህ ወቅት
‹‹ እነሆ እኔ በእሳቱ መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ እሳቱ ምንም አላቆሰላቸውም አራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል ፡፡ ›› አለ፡፡
ንጉስ ናብከደነፆር በግልፅ ተመልክቶ እንደመሰከረው የነደደውን እሳት በማብረድ ለሠልስቱ ደቂቅ ቤዛ የሆናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በግዕዙ ‹‹ ወገፁ ለራብዓይ ወልደ እግዚአብኤር ይመስል›› አራተኛውም ፊቱ የእግዚአብሔርን ልጅ ይመስላል ይላል፡፡

አዎን፤ ከዚህ በላይ እንደተገለፀው ሊቀመላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ስለ ሀይማኖታቸው መከራ የተቀበሉትን ወጣቶች የነደደውን እሳት አብርዶ በሃይማኖታቸው እንደአፀናቸው ተመልክተናል፡፡
የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት እኮ ጥንት የነበረ ብቻ ሳይሆን እስከ አለንብት ዘመን ደርሶ የመልአኩን አማላጅነት በዓይን የተመለከትነው ተጨባጭ ድርጊት ነው፡፡

የነደደ እሳት ውስጥ ገብቶ ከመውጣት ባልተናነሰ መከራ ውስጥ ገብተው በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ከሞተ ስጋ ነፍስ ድነው እውነተኛ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ብዙዎች ናቸው፡፡ በመልዓኩ ስም በፈለቀው ፀበል ተጠምቀው ደዌ የራቀላቸው እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ በየዓመቱ በቁልቢና በቅዱስ ገብርኤል ስም በታነፁአብያተ ክርስቲያናት የሚሰባሰበው ምዕመን ስዕለቱ የሰመረለት ልመናው የተሰማለት እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ ስለዚህ ለመላዕክት አለቃ ለቅዱስ ገብርኤል የተሰጠውን ፀጋ ተረድተን መልአኩን ልናከብረውና ልናመሰግነው ይገባል፡፡

መለከት ፡ ታህሳስ 1986 ዓ.ም

ቤተ መቅደስ ናብ ቤተ መቅደስ ኣትያ - ‘በአታ ለማርያም’‘በአታ ለማርያም’ ፦ ማለት ምእታው ናይ ቅድስት ድንግል ማርያም ናብ ቤተ መቅደስ ማለት እዩ። ቅድስት ድንግል ማርያም ካብ ዘርኢ እሴ...
12/12/2021

ቤተ መቅደስ ናብ ቤተ መቅደስ ኣትያ - ‘በአታ ለማርያም’

‘በአታ ለማርያም’ ፦ ማለት ምእታው ናይ ቅድስት ድንግል ማርያም ናብ ቤተ መቅደስ ማለት እዩ። ቅድስት ድንግል ማርያም ካብ ዘርኢ እሴይ፡ ካብ ቤት ዳዊት ካብ ዝኾኑ ኢያቄምን ሓናን ሕጋዊ ብዝኾነ ሩካቤ ዝተረኽበት ጓል መብጽዓ እያ። ምስ ተወልደት ኣብ ሠለስተ ዓመት ዕድመኣ ወሲዶም ንቤተ መቅደስ ሃብዋ። ውሉድካ ንቤተ እግዚአብሔር ምሃብን ኣብኡ እናኣገልገሉ ከምዝዓበዩ ምግባርን ኣብቶም ቅዱሳን ወለዲ ልሙድ እዩ። ከም በዓል ነቢይ ሳሙኤል ኣብ ቤተ መቅደስ ዓብዮም ምሉእ ሕይወቶም ንእግዚአብሔር ዝተወፈዩ እዮም ነይሮም።

ቅድስት ድንግል ማርያም ግና ቅድመ ዓለም ኣብ ሕልና ኣምላኽ ተሓሲባ ዝነበረት እያ’ሞ ገና ኣፋ እኽሊ፡ ከብዳ ድማ ዘመድ ከይለመደ ካብ ሕቍፊ ኣደኣ ሓና ተወሲዳ፣ ንሥላሴ ከም ኣቦን ኣደን፡ ንመላእኽት ድማ ከም ኃውን ኃፍትን ገይራ ኣብ ቤተ መቅደስ ንክትዓቢ ብ3 ታኅሣሥ ተዋህበት።

ናብ ቤተ መቅደስ ምስ ኣምጽእዋ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ ንካህናት ኣኪቡ ብዛዕባ መግባ ኽመክር ከሎ ቅዱስ ፋኑኤል መልኣኽ ኅብስት ሰማያውን ጽዋዕ ሰማያውን ኂዙ ተራእየ።

ሊቀ ካህናት ዘካርያስ ንኣይ ዝመጸ እዩ ኢሉ ክቕበል እንተ ተንሥኦ ንላዕሊ ረኃቐ፣ ቀጺሉ ናቱ ሰዓቢ ስምዖን’ውን ኽቅበል ደልዩ እንተ ቐረበ ንእኡ ኸኣ ረኃቖ። ጥበብ እግዚአብሔር ኣይፍለጥን’ዩ፡ ምናልባት ናብዛ ሕፃን ዝመጸ ሃብቲ ከይከውን ኢሎም ንበይና ገዲፎማ ድኅር እንተበሉ፣ ንሳ ድማ ደድኅሪ ኣደኣ ክትስዕብ ከላ፡ ብፍጥነት እቲ መልኣኽ ወሪዱ ሓደ ክንፉ ኣንጺፉ ንሓደ ክንፉ ጋሪዱ ክንዲ ቁመት ሰብኣይ ዝኣክል ካብ ምድሪ ክብ ኣቢሉ መጊብዋ ዓረገ። እምበኣር እዚ ፍቓድ እግዚኣብሔር እዩ ኢሎም ብ 3 ታኅሣሥ ናብ ቤተ መቅደስ ኣእተዉዋ። (ቅዳሴ ማርያም ቍ. 38-44) ነዚ ንምኽባር ዓመት መጸ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና፡ ኣማናዊት ታቦት ቅድስት ድንግል ማርያም ኣብ ቤት ኣቦኣን ኣደኣን ሠለስተ ዓመት ጸኒሓ ናብ ቤተ መቅደስ ዝኣተወትሉ 3 ታኅሣሥ ‘በአታ ለማርያም’ እናበለት ብዓቢይ መንፈሳዊ ክብሪ ተብዕሎ።

ቅድስት ድንግል ማርያም ካብ ሠለስተ ዓመት ዕድመኣ ጀሚራ ኣብ ቤተ መቅደስ መላእኽቲ ዘምጽኡላ ሰማያዊ ኅብስት እናተመገበት፡ ሰማያዊ መስተ እናሰተየት፡ ሓርን ወርቅን ኣሰማሚዓ እናፈተለት ብሞግዚትነት መላእኽቲ ዓበየት፣ እምበር ንጽሕተ ንጹሓን ድንግል ማርያም ከምተን ቅድሜኣን ድኅሬኣን ዝኾና ሕፃናትን ኣዋልድን ብስሓቅን ጸወታን ዝዓበየት ኣይኮነትን። ቅዱስ ያሬድ፡ ‘ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ፡ ከመዝ ነበርኪ ዓሠርተ ወክልኤተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት’ (ኣንቀጸ ብርሃን) ኢሉ ከምዝጠቐሶ፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ብቅድስናን ብንጽሕናን እናኣገልገለት ኣብ ቤተ መቅደስ ዓሠርተ ክልተ ዓመት ምስ ተቐመጠት፡ ልማድ ኣንስቲ ዘይብላ ንጽሕተ ንጹሓን ክነሳ ኣይሁድ ብመንቀኝነት ተላዒሎም ‘ንቤተ መቅደስና ከይተርክሰልና ትውፃእ’ በሉ።

ካህን ዘካርያስ ንእግዚኣብሔር ብጸሎት ሓቲቱ ብዝረኸቦ ጥበብ መሠረት ብሠለስተ መሰኻኽር እቲ ዘመዳ ዝኾነ ኣረጋዊ ዮሴፍ ምእንቲ ክሕልዋ ብሓደራ ተዋህበት። ሀብተ ንጽሕና ዝነበሮ ዮሴፍ ሓላዊኣ ኮይኑ ምስኣ እንተነበረ፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ግና ኣብ ሕልና ኣምላኽ ሰለዝነበረት፡ ንሓደ ኣካል ካብ ቅድስት ሥላሴ ንኣካላዊ ቃል እግዚኣብሔር ወልድ ብድንግልና ፀኒሳ ብድንግልና ከም እትወልዶ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ኣበሠራ፣ ንሳ ድማ ብእምነት ስለዝተቐበለቶ ኣደ ኣምላኽ ክትከውን በቕዐት። (ሉቃ. 1፡26-28)

ቅድስት ድንግል ማርያም ንእግዚአብሔር እምንቲ መዝገብ ምሥጢር ኮነት፣ ነቲ ኣብ ደቂ ሰባት ሠልጢኑ ዝነበረ ገዛኢ ጸልማት ዲያብሎስ ዝስዕር ኣማናዊ ብርሃን ፀሓየ ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ዝተረኽበላ ኣማናዊት ምሥራቅ ምኽንያት ድኅነትና ብምዃና ኣብ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፍሉይ ሥፍራ ኣለዋ። ድኅሪ ስም ሥላሴ ቀጺልና ናታ ስም ምጽዋዕ፡ ድኅሪ ንፈጣሪ ዝቐርብ ምስጋና ኣስዒብና ንኣና ምምስጋን፣ ናይ ወዳን ፈጣሪኣን ለውሃትን ተኣምርን ድኅሪ ምዝራብ ናታ ፍቕርን ተኣምርን ምዝራብ ልሙድ እዩ።

ስለዚ ነዛ እግዚኣብሔር ዘኽበራን ዝኃረያን (መዝ. 132፡13-14) ቅድስት ድንግል ማርያም፡ ንሕና ደቂ ሰባት ነቲ በዓላ (በአታ ማርያም 3 ታኅሣሥ) እንተኣኽበርናን ብስማ እንተ ተማኅፀንናን ሰማያዊ ዓስቢ፡ በረከተ ሥጋ ወነፍስ ዘውህብ እዩ’ሞ ናይዚ በረከት ተሳተፍቲ ክንከውን ቅዱስ ፍቓዱ ይኹነልና።

ጸሎታን በረከታን ምሕረት ፍቁር ወልዳን ምስ ኵልና ሕዝበ ክርስቲያን ይኹን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡ ኣሜን።

በአታ ለማርያም ውስተ ቤተ መቅደስ #በየቀኑ የሚለጠፉ ጽሑፎችን ለማግኘት ገጻችንን   ያድርጉ ።እንኳን አደረሰን ። ሰይጣን በእባብ አካል ተሰውሮ ሔዋንን፤ በእርሱዋም አዳምን በማሳት በእነርሱ...
12/12/2021

በአታ ለማርያም ውስተ ቤተ መቅደስ

#በየቀኑ የሚለጠፉ ጽሑፎችን ለማግኘት ገጻችንን ያድርጉ ።

እንኳን አደረሰን ።

ሰይጣን በእባብ አካል ተሰውሮ ሔዋንን፤ በእርሱዋም አዳምን በማሳት በእነርሱ ላይ ሞት እንዲሠለጥንባቸው ስላደረገ “በአንተና በሴቲቱ መካከል፣ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደረጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኮናውን ትነድፋለህ” በማለት የፍቅር አምላክ እግዚአብሔር ፈረደበት፡፡ “በአንተ” የተባለው ሰይጣን ሲሆን፣ “በሴቲቱ” የተባለችው ቅድስት ድንግል ማርያም ናት (ገላ.4፡4)፣ “በዘርህ” ሲል የዲያብሎስ የግብር ልጆችን ሲሆን(ዮሐ.8፡49)፣ “በዘርዋ” የተባለው ክርስቶስ ነው(ገላ.3፡16)፡፡ ትርጉሙ እንዲህ አንደሆነም ወንጌላዊው ዮሐንስ “ዘንዶው በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የጠበቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ”አለን፡፡(ራእ.12፡17) እባብ የተባለው ሰይጣን ስለመሆኑም “ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ”(ራእ.12፡9) ብሎ ጻፈልን፡፡

አዳም በዚህ ፍርድ ቃል ምክንያት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ምን እንደሆነ ተረዳ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር አምላክ በሔዋንና በእርሱ ላይ የፈረደው ፍርድ እነርሱን ከማዳን አንጻር የርኅራኄ ፍርድ እንደሆነ፤ እርሱና ሔዋን በክፉ ምርጫቸው ምክንያት ያጎሳቆሉትን ተፈጥሮአቸውን ወደ ቀደሞው ክብሩ ይመልሰው ዘንድ ንጽሕት ዘር ከሆነች ታናሽ ብላቴና እንደሚወለድና በመስቀሉ ሞት በእነርሱ ላይ የተላለፈውን የሞት ፍርድ እንደሚሽረው፣ አዳምና ሔዋን የተመኙትን የአምላክነት ስፍራ በክርስቶስ በኩል እንደሚያገኙት እንዲሁም በእርሱ የማዳን ሥራ የመለኮቱ ተካፋዮች እንዲሆኑ አስተዋለ፡፡ ይህም እውን እንደሚሆንም “አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ” በሚለው አምላካዊ ቃሉ አረጋገጠ፡፡ ስለዚህም ለመሰናከሉ ምክንያት የሆነችው ሴት ለትንሣኤውም ምክንያት እንደሆነች ተረዳ፡፡ በዚህም ምክንያት አስቀድሞ ከሥጋዬ ሥጋ ከአጥንቴ አጥንት የተገኘሽ ክፋዬ ነሽ ሲል “ሴት” ብሎ የሰየማትን ሚስቱን “ሔዋን” ብሎ ስም አወጣላት፡፡ ትርጓሜውም የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው፡፡ እንዲያ ባይሆንና አባታችን አዳም ይህንን የእግዚአብሔርን አሳብ ባይረዳ ኖሮ እንዴት በሰው ዘር ላይ ሞት እንዲሠለጥን ምክንያት ለሆነችው ሚስቱ ሔዋን የሚል ስምን ያወጣላት ነበር? ነገር ግን በእርሱዋ ሰብእና ውስጥ እርሱንና ወገኖቹን ከሞት ፍርድ ነጻ የሚያወጣቸውንና ወደ ቀደመው ክብራቸው የሚመልሳቸውን ጌታ በሥጋ የምትወልድ፣ የሕያዋን ሁሉ እናት የሆነች ንጽሕት ዘር እንዳለች ከእግዚአብሔር የፍርድ ቃል አስተዋለ፡፡

አዳም ይህን ሲረዳ ክፋዩ ለሆነች ሚስቱ ያለው ፍቅርና አክብሮት ከፊት ይልቅ ጨመረ፡፡ ከእርሱም በኋላ ለሚነሡ ወገኖቹም ለመዳናቸውና ለመክበራቸው ምክንያት ከሴት ወገን የሆነች ቅድስት ድንግል ማርያም እንደሆነ አስተውለው ወንዶች ለእናቶቻቸውና ለእኅቶቻቸው እንዲሁም ለሴት ልጆቻቸው ተገቢውን አክብሮትና ፍቅር እንዲያሳዩ ለማሳሰብ ሲልም ሚስቱን ሔዋን ብሎ መሰየሙንም መረዳት እንችላለን፡፡ እንዲህም ስለሆነ ነቢዩ ኢያሳይያስ “ዐይኖችን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሟቸዋል”(ኢሳ.60፡4)ብሎ ትንቢት ተናገረ፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ራሱዋን የጌታ ቤተክርስቲያን በማድረግ፤ ቤተክርስቲያን በልጁዋ ክቡር ደም ተዋጅታ እንድትመሠረት ምክንያት ሆናለች፡፡ ስለዚህም አባታችን አዳም እንዳደረገው ነቢዩም እንደተናገረው ለእርሱዋ ያለንን ፍቅርና አክብሮት በጾታ ለሚመስሎአት እናቶቻችን፤ እኅቶቻችን፣ እንዲሁም ሴቶች ልጆቻችን በማሳየት እንገልጠዋለን፡፡

ከአዳም በኋላ የተነሡ ቅዱሳን አበው በአዳምና በሔዋን መተላለፍ ምክንያት በእነርሱ ላይ የሠለጠነባቸው ሞት የሚወገድላቸውና ወደ ገነት የሚገቡት እግዚአብሔር አምላክ ከቅድስት ድንግል ማርያም በመወለድ እንደሆነ ከአዳም አባታቸው ተምረው ነበር፡፡ ስለዚህም ከክርስቶስ የማዳን ሥራ ተካፋይ ለመሆን እሾኽና አሜካላ በምታበቅለውና ሰይጣን በሠለጠነባት በዚህ ምድር የመዳን ተስፋቸው የሆነችውን የቅድስት ድንግል ማርያምን መወለድ በተስፋ እየተጠባበቁ ቅዱስ ጳውሎስ “ማቅ፣ ምንጠፍና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ተጨነቁ፣ ተቸገሩ፣ መከራ ተቀበሉ፣ ተራቡ፣ ተጠሙም፣ ዓለም የማይገባቸው እነዚህ ናቸው፤ዱር ለዱርና ፍርኩታ ለፍርኩታም ዞሩ”(ዕብ.11፡33-38) በጽድቅ ተጉ፡፡ ጌታችንም እንደተስፋ ቃሉ ከንጽሕት ቅድስት እናቱ ተወልዶ በመስቀል ላይ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ በመቅረብ ወደ ገነት አፈለሳቸው፡፡ ስለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዳ ጌታችንን መድኀኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እስክትወልድ ድረስ የተስፋ ቃሉ እንዳልተፈጸመ ለማስዳት ሲል ጨምሮ “እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙም፡፡ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ አግዚአብሔር ስለ እኛ የምትበልጠውን አስቀድሞ በይኖአልና፡፡” ማለቱ(ዕብ.11፡39-40)

አባቶቻችን ከሐዋርያት በትውፊት አግኝተው እንደጻፉልን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልክ እንደ ይስሐቅ፣ ነቢዩ ሳሙኤል እና መጥምቁ ዮሐንስ፣ መካን ከነበሩ ወላጆች የተገኘች ናት፡፡ እናቱዋ ሐና በአባቱዋ በኩል ከአሮን ቤት ስትሆን በእናቷ በኩል ከይሁዳ ወገን ነበረች፡፡ አባቱዋ ኢያቄም ግን ከይሁዳ ወገን ነበር፡፡ እነዚህ ወላጆች በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ ነገር ግን ልክ እንደ አብርሃምና እንደ ሣራ እስከ እርጅናቸው ድረስ ልጅ አልወለዱም ነበር፡፡ በአይሁድ ዘንድ መካንነት የእርግማን ምልክት ተደርጎ ይወሰድ ስለነበር ኢያቄምና ሐና እግዚአብሔር አምላክ ልጅ በመስጠት ይህን ስድብ ያርቅላቸው ዘንድ በቅድስናና በንጽሕና በመጽናት ምጽዋትንም በማብዛት በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ ጸሎታቸውንና ምጽዋታቸውን እግዚአብሔር ስለተቀበለላቸው አምላክን በሥጋ በመውለድ ለዓለም መድኅን የሆነቸውን ቅድስት ድንግል ማርያምን በእርጅና ዘመናቸው ግንቦት አንድ ቀን ወለዷት፡፡ ማርያም ማለት የእግዚብሔር ስጦታ ማለት ነው፡፡ ሐናም እግዚአብሔር አምላክ ስድቤን ከእኔ አርቆልኛልና ከእግዚአብሔር እንዳገኘዋት ለእግዚአብሔር መልሼ እሰጣታለሁ ብላ የተሳለቸውን ስለት አሰበች፡፡ ሦስት ዓመት ሲሞላትም ስለቷን ትፈጽም ዘንድ ከኢያቄም ጋር ልጇን ቅድስት ድንግል ማርያም ይዛ ወደ ቤተመቅደስ አመራች፡፡ በጊዜው ሊቀ ካህናት የነበረው ካህኑ ዘካርያስም ሕዝቡን ሰብስቦ በታላቅ ደስታ ተቀበላቸው፡፡ ነገር ግን ካህኑን ዘካርያስን የምግብናዋ ነገር አሳስቦት ነበረና ሲጨነቅ ሳለ ነቢዩ ኤልያስን ይመግበው ዘንድ መልአኩን የላከ እግዚአብሔር አምላክ(1ነገሥ.19፡6) እናቱ የምትሆነውን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይመግባት ዘንድ ሊቀ መላእክትን ቅዱስ ፋኑኤልን አዘዘላት፡፡ ካህኑ ዘካርያስም የምግቡዋ ነገር እንደተያዘለት ሲረዳ በቤተ መቅደስ ውስጥ እንድታድግ አደረጋት፡፡ ይህ እለት በሁሉም ኦሬንታልና የሐዋርያት የሥልጣን ተዋረድ(Apostolic succession) በተቀበሉ የሚታወቅና የሚከበር ክብረ በዓል ሲሆን በአታ ለማርያም ወይም የቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተመቅደስ መግባት በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህም “ልጄ ሆይ ስሚ፣ ጆሮሽንም አዘንቢዪ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤ ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፤ እርሱ ጌታሽ ነውና፡፡”(መዝ.44፡10) የሚለው ቃል መፈጸሙን እናስተውላለን፡፡

የጌታን መወለድ በተስፋ ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን አበው ይህች ቀን እጅግ ታላቅ እለት ነበረች፤ ምክንያቱም የመዳናቸው ቀን መቃረቧን የምታበሥር ቀን ነበረችና፡፡ ለእኛም ለክርስቲያኖች ይህች ቀን ታላቅ የሆነ በረከት ያላት ናት፡፡ ሙሴ የመገናኛ ድንኳኗንና በውስጡ ያሉትን ነዋያተ ቅዱሳት የጥጃና የፍየሎች ደምን ከውኃ ጋር በመቀላቅል በቀይ የበግ ጠጉርና በሂሶጵ በመንከር ረጭቶ ቀድሶአት ነበር፡፡(ዘጸ.24፡7-8፤ዕብ.9፡18-22) ንጉሥ ሰሎሞንም እርሱ ያሠራውን ቤተመቅደስ እርሱና ሕዝቡ ባቀረቡት የእንስሳት መሥዋዕት ቀደሷት ነበር፡፡(1ነገሥ.8፡23) እነዚህ ሥርዐታት ግን ክርስቶስ በደሙ ለሚዋጃት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነበሩ፡፡

በዚህች ቀን ቅድስት እናታችን ራሱዋን የጌታ ቤተ መቅደስ በማድረግ የብሉዩዋ ቤተመቅደስ ክርስቶስ በደሙ በዋጃት ቤተክርስቲያን ልትተካ መቃረቡዋን ለማብሠር ወደ ቤተ መቅደስ ያመራችበት ቀን ነው፡፡ ጌታችንም ከእርሱዋ የነሳውን ሥጋና ነፍስ በተዋሕዶ የራሱ ቤተመቅደስ በማድረግና እኛንም በጥምቀት የአካሉ ሕዋሳት እንድንሆን በማብቃት ሥጋችንን የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ስለዚህም እኛ ክርስቲያኖች የቅድስት ድንግል ማርያምን ወደ ቤተመቅደስ መግባት ባሰብን ቁጥር እግዚአብሔር ቃል ከእርሱዋ በሥጋ በመወለዱ ያገኘነውን ድኅነትና ብዙ ጸጋዎችን እናስባለን፡፡ አሁን እኛ ክርስቲያኖች በጥምቀት ከእርሱዋ የተወለደውን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለብሰነዋል፤ (ገላ.3፡27) ከእርሱዋ በነሣው ተፈጥሮ በኩል ሞትን በመስቀሉ ገድሎ ሲያስወግደው፣ እኛም በጥምቀት ከእርሱ ሞት ጋር በመተባበራችን ሞትን ድል የምንነሣበትን ኃይልን ታጥቀናል፡፡ በጥምቀት ያገኘነውን ጸጋ ሠርተንበትና አብዝተነው ብንገኝ ከትንሣኤው ተካፋዮች መሆንን እናገኛለን፡፡ ይህ ሁሉ የተፈጸመልን እግዚአብሔር ቃል ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ በመወለዱ ምክንያት ነው፡፡

ቅድስት ድንግል ማርያም ብሉይን ከአዲስ ያገኛኘች መንፈሳዊት ድልድይ ናት፡፡ በብሉይ ያሉት ቅዱሳን በሐዲስ ኪዳን ካለነው ጋር አንድ ማኅበር የፈጠሩትና ከቅዱሳን መላእክትም ጋር እርቅ የወረደው ከእርሱዋ በነሳው ሰውነት በኩል ነው፡፡ ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እንግዲህስ ወዲህ እናንተ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም”(ኤፌ.2፡19) ብሎ አስተማረ፡፡ ራሷን የጌታ ቤተ መቅደስ በማድረግ እኛንም በልጁዋ በኩል የመንፈሱ ቤተ መቅደስ እንድንሆን ምክንያት ሆናልናለችና የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተመቅደስ መግባት ለእኛ ክርስቲያኖች ልዩ ትርጉም አለው፤ ስለዚህም ይህቺን እለት በታላቅ ድምቀት እናከብራታለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም
ረድኤትና በረከት ያሳትፈን
ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

02/12/2021

††† እንኳን ለቅዱሳን ቆርኔሌዎስ ሐዋርያዊ እና አብድዩ ነቢይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ቆርኔሌዎስ †††

††† ዛሬ የምንመለከተው የዚህ ቅዱስ ዜና ሕይወት በአብዛኛው የተወሰደው ከሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 10 ላይ ነው:: በቤተ ክርስቲያን የሐዲስ ኪዳን ታሪክ ወሳኝ ከሚባሉ ክዋኔዎች የዚህ ቅዱስ አምኖ መጠመቅ ነውና በታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ላይ በስፋት ተመዝግቧል::

ምንም እንኩዋ ከእርሱ አስቀድሞ ኢትዮዽያዊው ባኮስ እንዳመነና እንደ ተጠመቀ ቢታወቅም (ሐዋ. 8:26) ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ከአሕዛብ ወገን አምኖ ሐዋርያትን የተቀላቀለ የመጀመሪያው ሰው ነው:: ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
የሮም መንግሥት በቄሣሮች ሥር በ1ኛው መቶ ክ/ዘመን ዓለምን እንደ ሰም አቅልጦ: እንደ ገል ቀጥቅጦ ይገዛ ነበር:: በየ አሕጉሩም እስከ መንደርተኛ ሹሞች ድረስ ተሹመው ግብርን ለቄሣር ይሰበስቡ: ሕዝቡን ለቄሣር ያስገዙ ነበር::

ከእነዚህ መካከልም አንዱ የሆነው ቆርኔሌዎስ በቂሣርያ ዘፍልስጥኤም (ሌላ ቂሣርያ ስላለች ነው) የመቶ አለቃ (ሃቤ ምዕት): የሠራዊት መሪ (ሊቀ ሐራ) ሆኖ ተሹሞ ነበር:: የሠራዊቱን ስምም "ኢጣሊቄ" ይሉታል::

ቆርኔሌዎስ እግዚአብሔርን አያውቅም:: እንደ አረሚ (ግሪካውያን) የከዋክብት አምላኪ ነበር እንጂ:: ያም ሆኖ ክፋትን የሚጠላ: ደግነትን የሚያበዛ: ምጽዋትን የሚያዘወትርና በሐቲት (በምርምር) የሚኖር ሰው ነበር::

ታዲያ በዚያ ሰሞን ክርስቶስ ኢየሱስ መድኃኒታችን የማዳን ሥራውን ፈጽሞ: አበው ሐዋርያት ለትምሕርተ ወንጌል እንደ ሠጋር በቅሎ ይፋጠኑ ነበር:: ሹም (አለቃ) ነውና ቆርኔሌዎስ የሐዋርያት ዜና ፈጥኖ ነበር የደረሰው::

ቅዱሳኑ በስመ ክርስቶስ ድውያንን እንደሚፈውሱ: ሙታንን እንደሚያነሱ: በኃይለ መንፈስ ቅዱስም ብዙ ምልክቶችን (ተአምራትን) እንደሚያደርጉ ሰምቶ ተገረመ:: እርሱ የሚያመልከው ዙሐል (የኮከብ ስም ነው) አቅመ ቢስ ፍጡር መሆኑን ተረዳና እርግፍ አድርጐ ተወው::

ምንም የሠራዊት አለቃ ሹም ቢሆንም ዘወትር በመዓልትና በሌሊት ይጾምና ይጸልይ ገባ:: ጸሎቱም "የእውነት አምላክ ተገለጥ" ነበር:: ጾምና ጸሎት ያለ ምጽዋት ቁም ነገር አይሠሩምና ቤቱን ቤተ-ርሑባን: ቤተ-ነዳያን አደረገው::

ይሕ ተወዳጅ ጾም: ጸሎትና ምጽዋት ደግሞ ያለ ከልካይ ወደ ሰማያት: ቅድመ እግዚአብሔር ደረሰ:: ምንም አሕዛባዊ (ኢ-ጥሙቅ) ቢሆንም ጌታ ግን ቅዱስ መልአኩን ላከለት::

አንድ ቀን እንዳስለመደ ሲጸልይ ዘጠኝ ሰዓት (በሠርክ) አካባቢ መልአኩ ብሩህ ልብስ ተጐናጽፎ ተገለጠለት:: "ቆርኔሌዎስ ሆይ! ጸሎትህና ምጽዋትህ ወደ እግዚአብሔር ደረሰልህ:: እግዚአብሔርም አሰበህ" አለው::

"አሁንም ትድን ዘንድ በሰፋዪ ስምዖን ቤት: በሃገረ ኢዮዼ: ዼጥሮስ የሚሉት ስምዖን አለና እርሱን ጥራው:: እርሱ የምትድንበትን ይነግርሃል" ብሎት: የምሥራቹንም ነግሮት ተሰወረው:: ወዲያውም ከራዕዩ የተነሳ እያደነቀ ብላቴኖቹን ጠርቶ ወደ ኢዮዼ ላካቸው::

በዚያች ዕለትም የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ዼጥሮስ በቤተ ስምዖን ሰፋዪ ሳለ ይጸልይ ዘንድ ወደ ደርቡ (ፎቅ) ወጣ:: በዚያም በጸሎት ላይ ሳለ ተደሞ መጣበት:: ግሩም ራዕይንም ተመለከተ:: "ሞጣሕት ስፍሕት" ይላታል:: ከሰማይ በ4 ማዐዝን የተያዘች መጋረጃ: በውስጧ የእንስሳት: የአራዊት: የአዕዋፍ ስዕል ተስሎባት ስትወርድ ተመለከተ::

አንዲት እጅም ወደ እሪያው (አሳማ) እያመለከተች "ተንስእ ኦ ዼጥሮስ ኅርድ ዘንተ ወብላእ . . . - ዼጥሮስ ሆይ! ተነስ: ይህንንም አርደህ ብላ" ስትለው:: እርሱ ግን "ግሙራ ኢቦአ ርኩስ ውስተ አፉየ-የረከሰ ነገር ከአፌ ገብቶ አያውቅም" ብሎ መለሰ::

መልሶም "ዘእግዚአብሔር አንጽሐ አንተ ኢታስተራኩስ- እግዚአብሔር ያነጻውን አንተ አታርክሰው" ሲለው:: ይሕም ራዕይ 3 ጊዜ ሲደጋገም ተመለከተ:: ወዲያውም ያቺ መጋረጃም ወደ ላይ ተመለሰች::

የራዕዩ ምሥጢር ለጊዜው እግዚአብሔር ከፈጠረው "ርኩስ" የሚባል እንደ ሌለ ያጠይቃል:: ለፍጻሜው ግን ያቺ ሞጣሕት የወንጌል (የክርስትና) አንድም የእመ ብርሃን ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት::

እሪያው ደግሞ የቅዱስ ቆርኔሌዎስ ምሳሌ ነውና "አትጸየፈው: አጥምቀው" ሲለው ነበር:: ቅዱስ ዼጥሮስ ስለዚህ ነገር ሲያሰላስል የቅዱስ ቆርኔሌዎስ ብላቴኖች ደርሰው ጠሩት:: መንፈስ ቅዱስ "አብረሃቸው ሒድ" ብሎታልና አብሯቸው ሔደ::

ወደ ቆርኔሌዎስ ዘንድ ደርሶም 2ቱ ራዕያቸውን ተጨዋወቱ:: ቆርኔሌዎስም በግንባሩ ተደፍቶ ለሊቀ ሐዋርያት ሰገደለት:: ቅዱስ ዼጥሮስ ግን ስለ ትሕትና "አትስገድልኝ" አለው:: ከዚያም አፉን ከፍቶ ለእርሱና ለቤተሰቡ ከቅዱስ ቃሉ መገባቸው:: አጥምቆም እጁን ሲጭንባቸው ከቅዱስ መንፈሱ ተካፈሉ::

ከዚህች ዕለት በሁዋላም ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ሃብቱን: ንብረቱን: ሹመቱንና ክብሩን ንቆ ሐዋርያትን ተከተላቸው:: ለስብከተ ወንጌል አገልግሎትም አንዲት በትር ብቻ ይዞ ወደ ምድረ ግብጽ ወረደ:: በዚያም ብዙዎችን ወደ ክርስትና ስቦ: ለዓመታት ተጋድሎ በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† ቅዱስ አብድዩ ነቢይ †††

††† "አብድዩ" ማለት "የእግዚአብሔር አገልጋይ" ማለት ነው:: ቁጥሩ ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን የቅዱስ ኤልያስ ታላቁም ደቀ መዝሙር ነው:: ቅዱሳን ነቢያት ዮናስና ኤልሳዕም ባልንጀሮቹ ነበሩ::

ቅዱስ አብድዩ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ800 ዓመት አካባቢ የከሃዲው ንጉሥ የጦር መሪ ሆኖ በሃምሳ አለቃነት አገልግሏል:: ግፈኛዋ ኤልዛቤል ነቢያተ እሥራኤልን ስታስፈጅ 50ውን በአንድ ዋሻ 50ውን ደግሞ በሌላ ዋሻ አድርጐ አትርፏቸዋል:: 900ው ግን ተጨፍጭፈዋል::

ያተረፋቸውንም ክፉ ዘመን እስኪያልፍ ድረስ መግቧቸዋል:: አክአብና ኤልዛቤል ከሞቱ በሁዋላም ቅዱስ ኤልያስን ተከትሎ ሹመቱን ትቷል:: እግዚአብሔር ገልጾለትም ትንቢት ሲናገር: ሕዝቡንም ሲገሥጽ ኑሯል::

በብሉይ ኪዳን ካሉ የትንቢት መጻሕፍትም በጣም አጭሩን የጻፈው ይሕ ነቢይ ነው:: ትንቢተ አብድዩ ባለ አንድ ምዕራፍ ብቻ ናትና:: ቅዱሱ በዚህች ቀን ዐርፎ ወገኖቹ ቀብረውታል::

††† አምላከ ነቢያት ወሐዋርያት የበረከትና የሰላም ዘመንን ያምጣልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ኅዳር 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ቆርኔሌዎስ (ሐዋርያዊ ጻድቅ)
2.ቅዱስ አብድዩ ነቢይ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል

††† "በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር: ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ: በልብህም:- 'ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው?' የምትል አንተ ሆይ! የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል:: እንደ ንስር መጥቀህ ብትወጣ: ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን: 'ከዚያ አወርድሃለሁ' ይላል እግዚአብሔር::" †††
(አብድዩ 1:3)

የቴሌግራም ቻናላችን አባል ይሁኑ ።
https://t.me/+ZJ_WnwHdV4JkMzg0
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

30/11/2021

We are going to launch Gitsawe ግጻዌ in four languages.






and our Page!

 ኅዳር ሃያ አንድ በዚህች ቀን የእመቤታችን   የበዓልዋ ነው፣ ከሮሜ አገር የሆነ   አረፈ፣ ሊቀ ጳጳሳት   አረፈ፣   ዘአስዩጥ አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ ኅዳር ሃያ አ...
30/11/2021



ኅዳር ሃያ አንድ በዚህች ቀን የእመቤታችን የበዓልዋ ነው፣ ከሮሜ አገር የሆነ አረፈ፣ ሊቀ ጳጳሳት አረፈ፣ ዘአስዩጥ አረፈ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞



ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው።

"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።

እግዚአብሔር ከዘመነ አበው በሁዋላ በጊዜው ለእሥራኤላውያን ክብር፣ ሞገስ፣ አምባ የምትሆናቸውን ታቦተ ጽዮንን በቅዱስ ሙሴ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል። (ዘጸ. 31፥18) ከዚያም ለ500 ዓመታት ከእነሱ ጋር በመሆኗ በፈጣሪና በእነሱ መካከል ድልድይ ሆና ኖራለች።

ከዚያም ባለቤቱ ሲፈቅድ በዘመነ ሳባ በቀዳማዊ ምኒልክ (እብነ መለክ-እብነ ሐኪም) አማካኝነት ወደ ኢትዮዽያ መጥታለች። እነሆ በሃገራችን የ3ሺ ዓመት ቆይታዋን ልትደፍን የቀራት ጥቂት ዓመታት ብቻ ናቸው። ጌታ እንደ ፈቀደ ቅዱስ መስቀሉንና ታቦተ ጽዮንን ይዘን ይሔው በቸርነቱ እንኖራለን።

ያም ሆኖ ታቦተ ጽዮንን መስረቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀሳጢዎች እንዳሉ እናውቃለን። ግን አንጨነቅም። ምክንያቱም የመጣችውም የምትጠበቀውም በፈቃደ እግዚአብሔር ነውና እንጸልያለን እንጂ አንጨነቅም። በተለያየ ወሬም ራሳችንን አናማጥንም። ባለቤቱ እንድትሔድ ከፈቀደ ደግሞ ማንም ጉልበተኛ አያስቀራትም።

ታቦተ ጽዮን ብዙ ጊዜ "ጽላተ ኪዳን፣ ታቦተ ሕጉ" እየተባለች ትጠራለች። "ጽሌ" ማለት "ሰሌዳ" እንደ ማለት ሲሆን "ጽላት" ደግሞ በብዙ ቁጥር ነው። "ኪዳን" ደግሞ በፈጣሪና በሰው ልጆች መካከል ያለ "ውል - ስምምነት" ነው።

"ታቦት" ማለት "ማሕደር-ማደሪያ" እንደ ማለት ነው። ሕጉ የተጻፈባቸውን ሰላድው "ጽላት" ስንላቸው የጽላቱ ማደሪያ ደግሞ "ታቦት" ይባላል። ጽላት (ታቦትን) ያመጣ ፈጣሪ ነው። በሐዲስ ኪዳንም ምሥጢርና ሐተታ ቢኖረውም 2 ቦታ ላይ ስለ ታቦት ተጠቅሶ እናገኛለን። (2ቆሮ.6፥16 ፣ ራዕይ.11፥19)

በመጨረሻም ኅዳር ሃያ አንድ ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች እንመለከታለን።

:-
✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።

✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።

✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።

✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤

✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤

በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞



በዚህችም ዕለት ከሮሜ አገር የሆነ ተአምራትን የሚያደርግ ቅዱስ ጎርጎርዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት የቀናች ሃይማኖትንም ተምሮ እውነተኛ ክርስቲያን ሆነ። ከዚህም በኋላ የዚህን ዓለም ኃላፊነት የማታልፍ የመንግሥተ ሰማያትንም ኑሮ አሰበ ኀሳቡንም ሁሉ ስለ ነፍሱ ድኅነት አደረገ።

የዚያቺም አገር ኤጲስቆጶስ በኤጲስቆጶስነቱ ሥራ ይራዳው ዘንድ ለመነው እርሱ ግን አልፈቀደም ከውዳሴ ከንቱ የሚሸሽ ሁኗልና ወደ ገዳምም ገብቶ ጽኑዕ የሆነ ተጋድሎንም መጋደል ጀመረ።

የዚያቺም አገር ኤጲስቆጶስ በአረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶስ የሚያደርጉት ፈልገው አጡ ስለዚህም ተሰብስበው ሳሉ የመለኮትንም ነገር የሚናገር ጎርጎርዮስ ከእሳቸው ጋር ሳለ ገዳማዊ ጎርጎርዮስን ፈልጋችሁ በእናንተ ላይ ሹሙት የሚል ቃል ከሰማይ ወደ እነርሱ መጣ ።

በበረሀውም ውስጥ በፈለጉት ጊዜ አላገኙትም እየፈለጉትም ብዙ ቀን ኖሩ እርሱ ግን በአቅራቢያቸው ይኖር ነበር። ባለገኙትም ጊዜ በአንድ ምክር ተስማምተው በሌለበት ወንጌል ይዘው በላያቸው ኤጲስቆጶስነት ሾሙት ስሙንም የመለኮትን ነገር በሚናገር በጎርጎርዮስ ስም ጎርጎርዮስ ብለው ሰየሙት።

ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ተገልጦ ተነሥተህ ወደ እነርሱ ሒድ እነሆ በላያቸው ኤጲስቆጶስነት ሹመውልሃልና ይህም ከእግዚአብሔር የሆነ ነው አለው። ያን ጊዜም ወደ እነርሱ ወረደ የአምላክን ትእዛዝ መተላለፍ ፈርቷልና በአዩትም ጊዜ ወጥተው በታላቅ ክብር ተቀበሉት የሹመቱንም ሥርዓት ፈጸሙ።

እግዚአብሔርም ቊጥር የሌላቸው ብዙዎች ተአምራትን በእጆቹ ገለጠ ስለዚህም ገባሬ መንክራት ጎርጎርዮስ ተብሎ ተጠራ ። ከብዙዎች ተአምራቱም አንዲቱ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ ከእርሷም ብዙ ዓሣዎችን የሚያጠምዱበት ታናሽ ባሕር ነበረቻቸው አንዱም አንዱ የኔ ናት በማለት እርስበርሳቸው ተጣሉ ስለዚችም ባሕር በመካከላቸው ይፈርድ ዘንድ ወደ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ለመሔድ ተስማሙ እርሱም ከሁለት ተካፍሉ ብሎ አዘዛቸው እንዳዘዛቸውም ባልተስማሙ ጊዜ ስለዚያች ባሕር እግዚአብሔርን ለመነው በዚያንም ጊዜ ባሕሪቱ ደርቃ የምትታረስ ምድር ሆነች በመካከላቸውም ሰላም ሆነ በእጆቹ ስለሚደረጉ ድንቆች ተአምራት ዜናው በሁሉ አገር ተሰማ በጎ አገልግሎቱንም ከፈጸመ በኋላ በሰላም አረፈ ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞



በዚህችም ቀን የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ቆዝሞስ አረፈ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሃምሳ አራተኛ ነው። ይህም አባት ብዙ መከራና ኀዘን ደረሰበት በዘመኑም በክርስቲያን ወገኖች ሁሉ ላይ መከራና ችግር ደረሰባቸው በእነዚያም ወራት የክርስቲያን ወገኖችና አይሁዳውያን ልብሳቸውን በሰማያዊ ቀለም እንዲያቀልሙት እንጂ ነጭ ልብስ እንዳይለብሱ የእስላሞች ንጉሥ ጋዕፊር አዝዞ ነበርና።

በዚህም አባት ዘመን ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ በአስቄጥስ ገዳም በቅዱስ ሳዊሮስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ነበረች ጐኗም ተገልጦ ከእርሷ ብዙ ደም ፈሰሰ በግብጽ አገር ከአሉ ከሌሎች ሥዕሎችም ከዐይኖቻቸው ብዙ ዕንባ ፈሰሰ ይህም የሆነው በሊቀ ጳጳሳቱና በክርስቲያን ወገኖች ላይ ስለ ደረሰው መከራ እንደ ሆነ በመራቀቅ የሚያስተውሉ አወቁ።

ከዚህም በኋላ ስለእነዚያ የከፉ ወራቶች ፈንታ በጎ የሆኑ ወራቶችን እግዚአብሔር ሰጠው ሁል ጊዜም ምእመናንን የሚያስተምራቸውና የሚያጽናናቸው በቀናች ሃይማኖትም የሚያበረታታቸው ሆነ ። በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበርም ላይ ሰባት ዓመት ከአምስት ወር ከኖረ በኋላ በአምስት መቶ ሰባ አምስት ዓመተ ሰማዕታት ኅዳር ሃያ አንድ ቀን አረፈ ይንሶር በሚባል ዋሻውም ተቀበረ።

✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞



በዚችም ቀን ደግሞ የብርሌ የብርጭቆ ሠሪዎች ልጅ የሆነ ከአስዮጥ አገር ቅዱስ አባት አባ ዮሐንስ አረፈ ። ይህንንም ቅዱስ በወለዱት ጊዜ በበጎ ተግሣጽ አሳድገውታል የጥርብ ሥራንም አስተማሩት ከጥቂት ዘመናትም በኋላ አባቱና እናቱ አረፉ። ያን ጊዜ ወደ ቅዱስ አባ ኢስድሮስና ወደ አባ ባይሞን ዘንድ ሒዶ መነኰሰ በጾምና በጸሎት በገድል ሁሉ ተጠምዶ ተጋደለ ዜናውም በራቁ ገዳማት ሁሉ ተሰማ ።

ከዚህም በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጠለት ወደ ሀገሩ ሒዶ ወገኖቹን የጽድቅን ጎዳና ይመራቸው ዘንድ አዘዘው። ቅዱስ ቊርባንንም ሳይቀበል ከበዓቱ የማይወጣ ሆነ። በአንዲት ዕለትም ሁለት ቅዱሳን አረጋውያን አባ አብዢልና አባ ብሶይ ወደርሱ መጡ ገና ወደርሱ ሳይቀርቡ ከሩቅ ሳሉ ስማቸውን በመጥራት ሳያውቃቸው አባቶቼ ለመምጣታችሁ ሰላምታ ይገባል ብሎ ተናገረ እጅግም አደነቁት አባ ሲኖዳም ከግብጽ አገር እየመጣ ብዙ ጊዜ ይጎበኘው ነበር።

የከዳተኞችም ጠብ በግብጽ አገር ላይ በተነሣ ጊዜ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ የላከው የጦር መኰንን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጣ። በጸሎቱም ይራዳው ዘንድ ለመነው ቅዱስ ዮሐንስም መስቀሉን አንሥቶ መኰንኑን አይዞህ አትዘን አንተ ጠላቶችህን ድል ታደርጋለህና አለው እንደ ቃሉም ሆነ።

ዳግመኛም በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ላይ ጠላት በተነሣበት ጊዜ ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ላከ እርሱም አትዘን አንተ ጠላትህን ታሸንፋለህ አለው ያን ጊዜም ጠላቶቹን አሸነፈ ።

ከዚህም በኋላ በእነዚያ ወራት ንጉሥ ቴዊዶስዮስ የርኲሰትን ሥራ ስለ ሠሩ የአስዮጥን ሰዎች እንዲገድሏቸው ሀገራቸውንም እንዲአጠፉ አዘዘ። ንጉሡም የላከው መኰንን ሳይደርስ የእግዚአብሔር መልአክ ይህን ነገር ለአባ ዮሐንስ አሳወቀው የሀገርም ሰዎች የንጉሡን ትእዛዝ በሰሙ ጊዜ ወደ አባ ዮሐንስ ገዳም ወጥተው ስለ መጥፋታቸው በፊቱ አለቀሱ አባ ዮሐንስም አትጨነቁ አይዟችሁ እግዚአብሔር ያድናችኋልና አላቸው።

መኰንኑም በመጣ ጊዜ ከእርሱ በረከትን ይቀበል ዘንድ ወደ አባ ዮሐንስ ደረሰ አባ ዮሐንስም ንጉሡ ያዘዘውን ሁሉ ነገረው መኰንኑም ሰምቶ ደነገጠ ለቅድስናውም ተገዢ ሆነ ለመኰንኑም ርኩስ መንፈስ ያደረበት የዐሥራ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረው ያድንለት ዘንድ ቅዱስ ዮሐንስን ለመነው በዚያንም ጊዜ ዘይትን ቀብቶ አዳነው።

ከዚህም በኋላ የአስዩጥ ሰዎችን መገደላቸውን እንዲተው ወደ ንጉሥ ይጽፍለት ዘንድ መኰንኑን አባ ዮሐንስ ለመነው መኰንኑም ጽፎ ለአባ ዮሐንስ ሰጠው አባ ዮሐንስም ተቀብሎ ወደ ዋሻው ገባ ወደ ጌታችንም ጸለየ ብርህት ደመናም መጣች ተሸክማም ወደ ንጉሡ አደረሰችው ያን ጊዜም ንጉሥ ከማዕድ ላይ ነበረ ያንንም ደብዳቤ ከወደላይ ጣለለት ንጉሡም አንሥቶ በአነበበው ጊዜ ከመኰንኑ የተጻፈ እንደሆነ በመካከላቸው በአለ ምልክት ተጽፎ አገኘው የተጻፈውም ቃል ስለ አባ ዮሐንስ ልመና ሀገሪቱን ማጥፋትን እንዲተው የሚል ነበር ቀና ባለ ጊዜም ደመና አየ ንጉሡም አደነቀ።

ከዚህም በኋላ ሀገሪቱን ማጥፋትን ስለ አባ ዮሐንስ ይተው ዘንድ መልሱን ለመኰንኑ ንጉሡ ጽፎ ደብዳቤዋን ወደ ደመናው ወረወራት የተሰበሰቡትም እያዩ እጅ ተቀበለችውና ወደ ደመናው ገባች ወዲያውኑ አባ ዮሐንስ በዚያች ደመና ወደበዓቱ ተመለሰና በማግሥቱ ያቺን ደብዳቤ ለመኰንኑ ሰጠው በላይዋም የንጉሡ ፊርማውና ማኅተሙ አለ በአያትና በአነበባት ጊዜ ደነገጠ አደነቀም ስለ ሀገሪቱ ድኅነትም እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደአገሩ ተመለሰ።

የንጉሥ ዘመድ የሆነች የከበረች ሴት ዜናውን በሰማች ጊዜ ከደዌዋ ይፈውሳት ዘንድ ወደርሱ መጣች በጸሎቱም ተፈወሰች። ከዚህም በኋላ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ በሞተ ጊዜ መናፍቁ መርቅያን ነገሠ ። ቅዱስ አባ ዲዮስቆሮስንም አሠቃየው ። የቀናች ሃይማኖትን ስለመለወጡ አባ ዮሐንስ እየዘለፈና እየረገመው ወደ ርሱ ደብዳቤ ላከ ከጥቂት ወራትም በኋላ እግዚአብሔር ቀሠፈው።

ለእርሱም ዕድሜው መቶ ሃያ አምስት ዓመት ሲሆነው ዕረፍቱ እንደ ደረሰ አወቀ እየጸለየም ግምባሩን ምድር አስነክቶ ሰገደ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ ከመቃብሩም ቁጥር የሌላቸው ድንቆች የሆኑ ብዙዎች ተአምራት ተገለጡ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ይኑር። በቅዱሳኑም ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

    ተኣምር ኣዴና ቅድስቲ ድንግል ማርያም ኣብ ዝነግር መጽሓፍ ‘ተኣምረ ማርያም’ ከምዝገልጾ፡ ነቶም ዝኽበሩ 33 በዓላት ኣዴና ቅድስቲ ድንግል ማርያም ክንፈቅድ ከሎና ኅዳር 21 ንቘጽር። ...
30/11/2021





ተኣምር ኣዴና ቅድስቲ ድንግል ማርያም ኣብ ዝነግር መጽሓፍ ‘ተኣምረ ማርያም’ ከምዝገልጾ፡ ነቶም ዝኽበሩ 33 በዓላት ኣዴና ቅድስቲ ድንግል ማርያም ክንፈቅድ ከሎና ኅዳር 21 ንቘጽር። ዓመት ዓመት 21 ኅዳር ድማ ብስም ቅድስቲ ድንግል ማርያም ኣብ ዝተሓንፁ ኣብያተ ክርስቲያን ‘ኅዳር ጽዮን’፡ ‘ኅዳር ማርያም’ ተባሂሉ መንፈሳዊ በዓል ይኽበር። እዚ በዓል'ዚ ኣቦታትና ካብ ቀደም እናኽበርዎ ዝመጽኡ ዓቢይ በዓል እዩ።

ምኽንያት ኣበዓዕላኡ ድማ ፦

• መጽሓፍ ‘ተኣምረ ማርያም’ ኣብ መቅድሙ ከረድእ ከሎ፡- “ኣብዚ ወርኂ’ዚ ኣብ መበል 21 መዓልቲ ነቢይ ዘካርያስ ናይ ቀንዴል ፋና ኬበርህ ዝረኣየሉ መዓልቲ እዩ” (ዘካ. 2፥2)

• ታቦተ ጽዮን ኣብ ምርኮ፦ ብተኣምራ ንዳጎን ሰባቢራ፡ ንዝደፈሩ ኣረማውያን ብመቕሠፍቲ ገሪፋ ናብ ሃገራ ዝተመለሰትሉ ወርኂ ኅዳር ምዃኑ እዩ። 1ይ ሳሙ. 2፥12፤ 7፥2። ‘ታቦተ ጽዮን’ ዝብል ስያመ’ ትርጕሙ ኣብ ጽዮን ዘላ ታቦት ማለት እዩ።

• ‘ታቦተ ጽዮን’ ኣብ ደብተራ ኦሪት (ኣብ ድንኳን) ንኣሽሓት ዓመታት ድኅሪ ምቕማጣ ንጉሥ ሰሎሞን ዓቢይ ቤተ መቅደስ ሓኒፁ ናብ ቤተ መቅደስ ዝኣተወትሉ በዓል ኮይኑ ዝኸበረሉ ወርኂ ኅዳር ምዃኑ ተፈሊጡ እዩ። (1ይ ነገ. 8፥1-67)

• ኣብዚ 4ይ ክፍለ ዘመን ድኅሪ ልደተ ክርስቶስ ኣብ ዘመን ቅዱሳን ነገሥታት ኣብርሃ ወኣጽብሐ ድማ ‘ታቦተ ጽዮን’ ብስም ‘ጽዮን ማርያም’ ተሰይማ ሥርዓተ ቅዳሴ ቤታ ኣብ ወርኂ ኅዳር ተኸቢሩላ እዩ።

• . . . ወዘይመስሎ

ዓመት መጽአ፡ 21 ኅዳር ብኣምሳል ታቦተ ጽዮን፡ ናይታ ኣማናዊት ታቦተ ጽዮን ዝኾነት ኣዴና ቅድስት ድንግል ማርያም “ኅዳር ጽዮን” ብዝብል ስም ክብ ብዝበለ በዓል ምኽባርና መሠረቱ መጽሓፍ ቅዱሳውን ክርስቲያናዊ ትውፊትን እዩ።

• ኣብ ዘመን ቅዱስ ዳዊት፡ ታቦተ ጽዮን ካብ ቤት ኣሚናዳብ ሥርዓተ ንግሥ ተጌሩ ብዝደመቐ በዓል ብዜማ ንእግዚኣብሔር እናኣመስገኑ ብ 30 ሺሕ ዝኣኽሉ ሰባት ተዓጂባ ብኽብሪ ኣብ ቤት ኣቢዳራ ን3 ወርኂ ተቐሚጣ እያ። ብምኽንያት ታቦት፡ እግዚአብሔር እቲ ንቤት ኣቢዳራ ከም ዝባረኸ ዝሰመዐ ዘማሪ ዳዊት ናይቲ በረኸት ተሳታፊ ምእንቲ ኪኸውን ነታ ታቦት ብማኅሌትን ብዝማሬን ብዓቢይ ክብርን ኣብ ከረን ጽዮን ስለ ዘዕረፋ፡ ካብዚ ጊዜ እዚ ጀሚሩ ‘ታቦተ ጽዮን’ እናተባህለት ክትጽዋዕ በቕዐት (2ይ ሳሙ 6፥1-19)።

• ኣብ መጽሓፍ ቅዱስ “ጽዮን” ዝብል ከከም ኣገላልጻኡ ዝተፈላለየ ትርጕም ኣለዎ፦

• ኣብታ ኣብ ከረን ሞርያ ዝተሓንፀት ቤት መቅደስ “ጽላተ ሕግ” (ታቦት ሕጊ) ስለ ዝነበረ ንከረን ሞርያ ‘ጽዮን’ ይብሎ። (ኢሳ. 8፥18 ፥ 18፥7 ፥ 24፥23)።

• ‘ኢዮሩሳሌም’ ውን ጽዮን ትበሃል ነይራ እያ። (2ይ ነገ. 19፥21 ፥ መዝ. 48፥2 ፥ 69፥35)።

• “ጽዮን” ዝብል ስም ሕዝቢ ኣይሁድ ይጽውዑሉ ኔሮም እዮም (መዝ 126፥1 ፥ ዘካ 9፥9)።

• ሰማያዊት ኢየሩሳሌም ውን ከረን ጽዮን ተባሂላ ትፍለጥ እያ (ዕብ 12፥22፣ ራእ 14:1)።

• . . . ወዘይመስሎ

ኣብ ዘመነ ብሉይ ኪዳን ኵሉ’ቲ ዝተነግረ ትንቢትን ዝተመሰለ ምሳሌን ኣማናዊ ትርጕም ዝረኸበ ኣብ ሓዲስ ኪዳን ኣካላዊ ቃል መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ብዘደንቕን ብዘይምርመርን ምሥጢረ ተዋሕዶ ካብ ኣዴና ቅድስት ድንግል ማርያም ሰብ ኮይኑ ድኅሪ ምግላጹ እዩ። “ኣነ ንነቢያትን ሕግን ክፍጽም ደኣ እምበር ክስዕር ኣይመጻእኩን” ከም ዝበለ (ማቴ. 5፥17)። ድኅሪ ትንሣኤኡ ውን ጐይታናን መድኃኒናን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቶም ኣርድእቱ ኦሪትን ነቢያትን እናጠቐሰ ፍጻሜ ከምዝረኸበ ከም ዝመሃሮም ቅዱስ ሉቃስ መስኪሩ እዩ። ስለዚ እቲ ምሥጢራዊ ኣማናዊ ትርጕም ናይ ‘ጽዮን’፦ ነታ ኣደ ኣምላኽና ሓቀኛ ታቦተ ጽዮን ንድንግል ማርያም ዝምልከት እዩ።

ዘማሪ ዳዊት በመንፈሰ ትንቢት ‘እምነ ጽዮን ይብል ሰብእ/ ሰብ ኣዴና ጽዮን ይብል’ (መዝ. 87፥5) ከምዝበለ፡ ዋላ እኳ ብምሳሌያዊ ኣዘራርባ ብዛዕባ ኢየሩሳሌም፡ ናይ ኦሪት ቤት መቅደስ፡ ብዛዕባ ሕዝበ እስራኤልን ምስኣቶም ብሃይማኖት ዝምድና ብዛዕባ ዝነበሮም ኣኅጉራትን እንተገለጸ፡ እቲ ኣማናውን ምሥጢራውን ትርጕም ግና ብዛዕባ ናይ ሓዲስ ኪዳን ቤት መቅደስ (ቤተ ክርስቲያን)፡ ብዛዕባ እስራኤል ዘነፍስ ዝተባህሉ ክርስቲያን ክኸውን እንከሎ እቲ ዋና ምሥጢራዊ ትርጕሙ ኸኣ ብዛዕባ ኣዴና ቅድስት ድንግል ማርያም ዝገልጽ ኮይኑ ንረኽቦ።

‘ጽዮን’ ዝተባህለት ድንግል ማርያም ምዃና ንኣና ንኦርቶዶክሳውያን ሓድሽ ነገር ኣይኮነን። ኣብቲ ናይ ወትሩ ጸሎትና’ውን “እንተ ይእቲ ስምዕየ ማርያም ጽዮን ለዓለመ ዓለም/ እታ ናይ ዘለዓለም ምስክረይ ድማ ጽዮን ማርያም እያ” ክንብል ከለና ማርያም ጽዮን ከም እትበሃል ንፈልጥ። “ሰብ ኣዴና ጽዮን ይብል” ምባሉ ብወንጌል ኣሚኑ ዝተጠምቀ ክርስቲያን ናይ ሃይማኖቱ መንነትን ናይ ክርስትናኡ መረጋገጺትን ንዝኾነት ‘ጽዮን እምባ መጸግዒት ኣደይ ይብላ’ ንኽብል እዩ።

ኣዴና ቅድስት ድንግል ማርያም “ጸወነ ሥጋ ጸወነ ነፍስ” ኮይና ንሕዝበ ክርስቲያን ብነፍሶምን ሥጋኦምን ተስፋ ከይቈርጹ በቲ ዝተዋህባ ናይ ምሕረት ቃል ኪዳን፡ ብጸሎታን ኣማላድነታን መጸግዒት ኮይና ብረዲኤታን ብለውሃታን እትሕልዎም መንፈሳዊት ኣደ ምዃና ፈሊጦም “ከውልና፡ መጸግዒት ኣዴና” እናበሉ ከም ዝምኅጸንዋ ንኽገልጽ እዩ ክቡር ዳዊት “ሰብ ኣዴና ጽዮን ይብል” ኢሉ ዝመስከረ። ኣብ ጊዜ ሓጐሶምን ኃዘኖምን ቈልዑ ናብ ኣደኦም ከም ዝጽግዑ እሞ ንሳ ድማ ከም እተጸናንዖም ንኻልእ ዝተከወለ ኣይኮነን።

ከምኡ ድማ ቅድስት ድንግል ማርያም መንፈሳዊት ኣዴና ምዃና ብቓል ኪዳና ተማኅጺንና፡ ብኣማላድነታ ምስ ንኣምን ካብ መከራ ሥጋን ነፍስን ድኂንና ወረስቲ መንግሥቲ ወዳ ከምእንኸውን ዝተረጋገጸ እዩ።

ናይ ኣዴና ጽዮን ቅዱስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ኣማላድነት ኣይፈልየና፡ ኣሜን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር; አሜን!

ምንጭ: ልሣን ተዋሕዶ

30/11/2021
30/11/2021

Address

Addisu Gebeya
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gitsawe ግጻዌ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share