
22/07/2025
16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት !!
የእግር ኳስ ተጫዋች በነበረው አለልኝ አዘነ ግድያ የተከሰሱት ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው።
በአለልኝ አዘነ ጉዳይ የመጨረሻ ፍርድ ለመስጠት ዛሬ የተሰየመዉ የጋሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተከሳሽ የአለልኝ ባለቤት አደይ ጌታቸዉና በእህቷ ባል ላይ የ16 እና 15 ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶባቸዋል።
ፍርድ ቤቱ ይህንን ዉሳኔ ያስተላለፈው መጋቢት 17/2016 ዓ/ም በተጋቡ በ15ኛ ቀን አለልኝ አዘነን ባለቤቱና የባለቤቱ እህት ባል መግደላቸውን በሰዉና በሰነድ ማስረጃዎች ካረጋገጠ በኋላ መሆኑን የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል መረጃውን ከአርባ ምንጭ ልኳል።
Tirita Sport / ትርታ ስፖርት