Kid's clothes store

Kid's clothes store its all about ethiopia
ስለ ኢትዬጺያ ብቻ

29/11/2025
29/11/2025
24/03/2024
24/03/2024
20/03/2024

‼️

ይህ ወንድማችን ወደ ቡልቡላ አካባቢ መንገድ ላይ ከወደቀ 3ቀን ሆኖታል!ምንም አይናገርም!ምግብ አይበላም😭አካባቢው ላይ ያሉ ደጋጎች የቻሉትን እያደረጉለት ለፖሊሶችም ስለሁኔታው ነግረዋቸው መጥተው አይተውት"ወደ ጤናጣቢያ እንድንወስደው አንድ ሀላፊነት የሚወስድ ሰው ያስፈልጋል" ብለው ተመልሰዋል!
እናንተ ልበደጎች ምንአልባት ቤተሰብ የሆናችሁ ወይም የምታውቁት ካላችሁ የከፋ አደጋ ላይ ከመውደቁ በፊት እንድረስለት🙏 #ሼር በማድረግ እንተባበረው🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

0909245824-liya

20/03/2024

#ይገርማል‼️ ለካ እንዲህም አይነት ሰው አለ!!

" "
ብላችኋለች!! ነገሩ እንዲህ ነው:-

ከ10ዓመት በፊት አንዲት ምስኪን ሴት ዱባይ ሀገር ሰው ቤት እየሰራች ሳለ ያጠራቀመችውን ገንዘብ እንዳይጠፋባትና ያለችበት ሁኔታ አመቺ ስላልነበር በአይን ለምታውቃት ሴት በአደራ መልክ "አንቺ ጋር ይቀመጥልኝ"ብላ ትሰጣታለች!!

አደራዋን የተቀበለችው ሴትም መኖሪያ ፍቃድ ስላልነበራት ጊዜውም ጥሩ ስላልነበር ድንገት እንኳ ከተያዝኩ የሷን ገንዘብ ላትርፍ ብላ ሌላ ለምታውቃት ኢትዮጵያዊ ሰጠቻት!!

ይህችም ኢትዮጵያዊ "ገንዘቡ እኔ ጋር ከሆነ ይጠፋል፣ አንቺ ጋር ይቀመጥ ስትፈልገው እንሰጣታለን"ብላ ለጓደኛዋ(ለ4ተኛ ሰው)አስተላልፋ ሰጠቻት!!

ከጊዜ በኋላ ባለገንዘቧን የምታውቃት ሴት ምንም ሳትናገር ድንገት አድራሻዋ ጠፋ!!የት እንዳለች ምን እንደገጠማት የሚያውቅ አልተገኘም!!

ገንዘቡን በአደራ መልክ ያስቀመጠችው ሴት በጣም ተጨነቀች!የማን እንደሆነ ምንም የምታውቀው ነገር ስለሌለ ግራ ገባት!እንቅልፍ ነሳት!ምንም ሳትነካው ብታስቀምጠውም ሰላም አጣች!!

"ይህች ሴት እኮ አረብ ሀገር ለዓመታት ለፍታ የሰው ቤት ሰርታ ይሄኔ ችግር ላይ ነች፣ምን አልባት ታማ መታከሚያ አጥታ አልጋ ላይ ነች፣ወይም ስራ ፈትታ ተቀምጣለች "እያለች በየቀኑ በሀሳብ ትብከነከናለች!

ከ10ዓመት በኋላ ታህሳስ ወር ላይ 2016ዓ.ም አንድ ተስፋ አገኘች!

ከዋናዋ ባለጉዳይ መጀመሪያ ላይ ብሩን በአደራ መልክ የተቀበለቻትን ሴት በimo አገኟት!"እረ የት ነው ያለሽው? የሰው ብር ይዤ ሰላም አጣሁ!ማናት ልጅቷ?"ብለው ጠየቋት!!
በሚያሳዝን ሁኔታ እንደማታውቃትና "ስሟ ጠይባ መሆኑን የያኔ ፎቶዋም ይህነው"ብላ ብቻ ነገረቻቸው!

ሰው የጓደኛውን ገንዘብ ለመብላት በሚጣደፍበት ዘመን ይህች እህቴ 4ተኛ ተቀባይ ሆና የማታውቃትን ሴት ገንዘብ ለመመለስ 10ዓመት በትግስት መሞከሯና መፈለጓ የሚገርም ነው!!

ብዙ ሰዎች በቃ ለቤተክርስቲያን ስጪ፣እረ ለተቸገረ ለግሺ እያሉ ቢያስጨንቋትም "እሷ ያለችበትን ሁኔታ በምን ታውቃላችሁ?በስደት ለፍታ ያጠራቀመችው እኮ ነው"ብላ እንደምትመጣ አስባ በተስፋ እየጠበቀቻት ነው!! ???
#ሼር በማድረግ እንፈልጋት🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"

0912121942-ውብሸት
0913559189-ሄኖክ
0913557326-ሙሉቀን

08/03/2024

🗣️ "7 አመቴ ነበር።የአባቴ ስልክ ይጮሀል።ሮዛሪዮ ሴንትራል እኔን ለወጣት ቡድኑ ማስፈረም እንደሚፈልግ ለአባቴ ነገሩት።አባቴ የኒው ኦልድ ቦይስ የልብ ደጋፊ ሲሆን እናቴ ደግሞ የሮዛሪዮ ሴንትራል ደጋፊ ነበረች።"

🗣️"አባቴም ጥያቄያቸውን ውድቅ አደረገው። ምክንያቱም መኪና የለንም የሮዛሪዮ ሴንትራል ክለብ ልምምድ ቦታ እኛ ከምንኖርበት 9 ኪሎ ሜትር ይርቃል።እናቴ ግን እኔ ችግሩን እፈታለው በማለት አባቴ ውድቅ ያደረገውን የዝውውር ጥያቄ መቀበል አለብን አለች።."

🗣️"ቤታችን ውስጥ የነተበ፣አሮጌ እና ቢጫ ቀለም ብስክሌት ነበር።እናቴም ወደ ልምምድ ቦታ በዚህ ሳይክል ለማድረስ ወሰነች።አባቴም ሳይክሉ ላይ የነበረውን የእቃ መያዣ ቅርጫት በእንጨት በመስራት ታናሽ እህቴ ቤት የሚጠብቃት ስለሌሌ እኛ ጋር እንድትመላለስ አደረገ።"

🗣️"አስቡት እናቴ በየቀኑ ደርሶ መልስ 18 ኪሎ ሜትር በአሮጊ ሳይክል ትጓዝ ነበር።በዛ ላይ እኔ ከጀርባዋ፣እህቴ ፊትለፊት እንዲሁም ማልያ ፣ጫማ እና ምግባችን ከኃላ በአንድ ቅርጫት ይጫናል።ዝናብ እና ፀሀይ እንዲሁም ጨለማ እና ሌቦች ሳይበግሯት በየቀኑ ለአመታት ለእኔ የእግርኳስ ህይወት መሳካት ስትል ዋጋ ከፍላለች። በዚህ ትጋቷም ህልሜን እየኖርኩ ነው።" 🇦🇷

አንሄል ዲ ማሪያ

06/03/2024

Address

Merkato
Addis Ababa
09

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kid's clothes store posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share