21/04/2026
🖊የሚመለከተው አካል አፋጣኝ እርምጃዎች እንድወስድ እና በትራንስፖርት ዙርያ ለህዝቡ ዘላቂ መብቴ እንድሰጥ አጥብቀን እንጠይቃለን።
ይህ በወላይታ ሶዶ እና አካባቢ ያለውን የትራንስፖርት አገልግሎት ከታሪፍ ወጪ ለምያስከፍሉና ናፍጣ ቀድቶ ስምርት ተሰጥቶ አልጭንም በማለት ህዝቡን ለእንግልት ለምዳረጉ ባለንብረቶች በወላይታ ሶዶ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ብሮ ክትትል በማድረግ በቂ እርምጃ በመዉሰድ የረዥም ጊዜ የህዝብ ስቃይ እንዲያቃልልን ነዉ።
በገጠመን ችግር መረዳዳት እና ህግና ሥራቱን ተከትሎ መስራት እንጅ እንዴ አጠቃላይ የመጣውን ችግር በመጠቀም የግል ሀብት ለማካበት የሚጠቀሙ ማንኛውም ግለሰቦች ሆነ ድርጅት ካለ መንግስት አፋጣኝ ክትትል እና እርምጃ እንድወስድ ለምመለከታ አካል ጥሪ እናቀርባለን።
ስለሆነም የወላይታ ሕዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት እንግልት እና ስቃይ በተላይ ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ወረዳዎች የሚጭኑ የህዝብ ማመላለሻ አዉቶብሶች ያልተገባ ከታሪፍ ዉጪ ዋጋ ጭማሪ፤ ከወንበር ዉጪ በእጥፍ መጫን እና አንዳድ ሰዉ ለምን የሚለውን ጥያቄ ካቀረቡ ሹፌሩ ሆነ ረዳት ጭምር ተሳፋሪ መስደብ እና ያለ ቦታዉ ማስወረድ እና ሌሎች መሰል ድርግቶች ከዚህ በኃላ መቆም እንዳለበት የሚመለከተው አካል በድጋሚ ትኩረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን።