Gulale Media Network

Gulale Media Network The page will work on oromo's culture , politics and social issues. also we will work harldy to connect omoia with the world by all ways we can all.

oromia shall be free !

26/06/2025

Namni kun eenyu?

(GMN_ ዜና) ኢራን በኳታር በሚገኘው አል-ኡደይድ የአየር ጦር ሰፈር ላይ የሰነዘረችውን የሚሳይል ጥቃት አጥብቃ በማውገዝ ከኳታር ጎን እንደምትቆም ይፋ አደረገች። ይህ የባህሬን አቋም የባህ...
23/06/2025

(GMN_ ዜና) ኢራን በኳታር በሚገኘው አል-ኡደይድ የአየር ጦር ሰፈር ላይ የሰነዘረችውን የሚሳይል ጥቃት አጥብቃ በማውገዝ ከኳታር ጎን እንደምትቆም ይፋ አደረገች። ይህ የባህሬን አቋም የባህረ ሰላጤው ሀገራት በኢራን ድርጊት ላይ ያላቸውን ስጋት በግልጽ ያሳያል።

የባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ、 የኢራንን ጥቃት "የኳታርን ሉዓላዊነትና የአየር ክልል፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ህግንና የተባበሩት መንግስታት ቻርተርን በግልጽ የጣሰ ነው" ሲል ፈርጆታል።

መግለጫው አክሎም ባህሬን በዚህ "ክልሉ በሚገኝበት አስቸጋሪ ሁኔታ" ውስጥ ለኳታር ሙሉ ድጋፏንና ወገንተኝነቷን እንደምትገልጽ አረጋግጧል።

ባህሬን ይህን መግለጫ ያወጣቸው ኳታር እራሷ ጥቃቱን ካወገዘች በኋላ ሲሆን፣ ይህም የባህረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት (GCC) አባል ሀገራት በኢራን ድርጊት ላይ ተመሳሳይ አቋም ሊይዙ እንደሚችሉ አመላካች ነው ተብሏል።

አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት "ይህ ክስተት ኢራን ምንም እንኳን ጥቃቱ በአሜሪካ ጦር ላይ ያነጣጠረ ነው ብትልም፣ ድርጊቱ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮችን ያስተናገዱትን የባህረ ሰላጤው ሀገራት ከባድ የዲፕሎማሲ እና የጸጥታ አጣብቂኝ ውስጥ እየከተታቸው መሆኑን ያሳያል።"

  USA'n haleellaa xiyyaaraa milka'aa buufataalee nukleeraa Iraan sadii irratti raawwachuu Pirizidaanti Tiraamp beeksisan...
22/06/2025

USA'n haleellaa xiyyaaraa milka'aa buufataalee nukleeraa Iraan sadii irratti raawwachuu Pirizidaanti Tiraamp beeksisan.

Tiraampi karaa miidiyaa dhuunfaa isaanii Tiruuz akka ibsanitti xiyyaaronni waraanaa USA erga buufataalee gabbisa Niwukilara Iraan Isfaan, Furdow fi Natnaaz barbadeessanii booda nagaan qilleensa Iraan gadi lakkisaniiruu jedhan.

Tiraamp itti dabaluun gabbisu Niwukilaraa Iraan Fardow amma hin jiru , kana booda yeroon akan nageenyaati jedhaniiru.

Aab Taayee Danda'aa Gaaffii fi deebii miidiyaan Horn conversation Obbo Taayyee Danda'aa waliin taasisan kutaa 6 (jechuun...
21/06/2025

Aab Taayee Danda'aa

Gaaffii fi deebii miidiyaan Horn conversation Obbo Taayyee Danda'aa waliin taasisan kutaa 6 (jechuun kan Afaan Oromoo sadanii fi kan afaan Amaaraa sadanuu ) daawwadheera. Gaariidhas. Garuu----

1, Aab Taayyeen ammayyuu taanaan balleessaa kanaan dura raawwateef ykn raawwachiiseef dhiifama gaafachuu hin barbaanne. Yoo xinnaate bara 2019 garee maqa balleessaa ijaaruun Oromoo kutaan qoodee , sanuu warra nu malee jechuun balaan beelaa fi waraanaa waggaa lamaa oliif akka irratti raawwatuuf haala mijeesseera. Jechootni Jawwaar D3-dhaan ibse sunis ka'umsi isaa kanuma.

2, Cichoominni aab Taayyeen waan amane irratti mul'isu waan ajaa'ibaati. Ammayyuu taanaan bilxiginnaa deggaruu,faarsuu fi dhaabuu isaaf cichoomina qaba. Kun waan gaariidha.dhiirri ciniinnattuu wayya kan jedhanuufis kanumaafi.

3, Aab Taayeen gaaffiiwwan taasise hundaa keessatti badii Abiyyi raawwate hundasaa kan hubate booda ta'uu amaneera. Waan hunduma Abbichuun balleesse erga turee naaf gale jedheera. Gaariidha akkuma boombiin jette turanii uruun mataan isaayyuu dansaadha. Garuu immoo kan beekamuu qabu obbo Taayyeen miseensa paartii siyaasaati malee miseensa dhaaba amantii ykn hafuuraa miti. Dabi akka raawwatamu, sobni akka jiraatu, shiirri akka xaxamu , shakkuu ykn tilmaamuutu irra ture. Waan hundaa amma reefuun bare jechuun daree siyaasaan ala dubbatama .

Waggota shan dura yoon doggoruu baadhe miidiyaa LTV irratti intalli lakkoofsa tokkoo sun (Beetii Taaffasaa) "ati waan hundumaa fuuldurratti waan ilaaltuuf shirri siyaasa keessatti dalagamu balaaf sin saaxiluu ?" Jetteenii turte. Intalloon sirriitti tamalakkatteetti jechuudha.

4, Aab Taayyeen nama sirni diimokiraasii sirriin akka jiraatuuf hawwu ta'uu isaa hubadheera. Dhugumatti sirni ummataan ijaaramu otoo uumame Taayyichoon akka hawwu argera. Garuu xoobiyaatti hin yaadamu.

Kan biraa barreeffama Taayyee akka mixii nama ciniinu sanuummoo ganama ganama garaa duwwwatti otoon dubbisuu dhibeen garaachaa na mudatus , cichoomina isaa ilaalee aab Taayyeef dhiifama godheera.

Akka hiikamuuf waaqa kadhachaafii, gaafa bahe immoo paartii( haa gaabbinu ! ) jedhu akka waliin hundeessinu abdiin qaba.

19/06/2025

(GMN)ኢራን የኒውክሌር ቦምብ ለመስራት እየሞከረች ለመሆኑ ምንም አይነት ማስረጃ አላገኘሁም - አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ

የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ራፋኤል ግሮሲ ኢራን ወደ ኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመሸጋገር እየተቃረበች ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ምንም አይነት ማስረጃ የለም በማለት ተናገሩ።

ይህ የሆነው እስራኤል ብሄራዊ ስጋት ፈጥሮብኛል በማለት የኢራንን የጦር መሳሪያ መርሃ ግብር ለማስቆም በሚል በኢራን ኒውክሌር ጣቢያዎች ላይ የአየር ጥቃት እየሰነዘረች ባለበት ወቅት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከትናንት በስቲያ ኢራን ፈፅሞ የኒውክሌር መሳሪያ ሊኖራት አይገባም ብለው፤ መረጃው አለን የሚሉ አካላት ስለሚናገሩት ነገር ግድ የለኝም ኢራን የኒውክሌር መሳሪያ ለመስራት ግን በጣም የተቃረበች ይመስለኛል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ ነው እንግዲህ ዋና ፀሀፊው ኢራን የኒውክሊየር መሳሪያ ለመስራት ተቃርባለች የሚባለውን የእስራኤልና የአሜሪካን ውንጀላ የሚቃረን መግለጫ የሰጡት።

ኢራን በበኩሏ፤ የኒውክሌር ኃይልን ለሰላማዊ አገልግሎት ብቻ ለመጠቀም እየሞከረች እንደሆነ በተደጋጋሚ መግለጿ ይታወሳል።

ይህ በዚህ እንዳለ የአለም አቀፉ አውቶሚክ ባለስልጣን ሁለቱ ሀገራት በሰላማዊ መንገድ እንዲነጋገሩና፤ ምንም እንኳን እስካሁን ኢራን ለስጋት የሚያደርስ የአውቶሚክ ሀይል እየሰራች ነው ብሎ ባያምንም ተጨማሪ ፍተሻ እንዲደረግ ጠይቋል።

19/06/2025

Soba guddaa bara kanaa sobame .

1. Shuguxii shan natti fixe, keessummaa Gammadaa Olaanaa

2. Obbleettii koo waggaa 16 Internet irra barbaade Raachee Tasfaayee

3. Ani namakeessi kiyya hojjatameedha Meerii Didhaa

4. Miidiyaa OBS guddisuuf jedhee gaa'ela osoo hin dhaabbatin hafe Margaa Hangaasuu

5. Abiyyi Elekooptara bira bula . Milkeessaa miidhagaa

6. Addaamii fi hawwaan gaafa wal fuudhan Gabreeltu jaarsummaa deeme , maammir Zanabee.

7. Waggoota 7 darban keessa namni tokko hin reebamne ykn hin dararamne .Abiyyi Ahmed .

Kan yaadattan itti dabalaa !

18/06/2025

የኢራን ጠቅላይ መሪ አሜሪካ ለምትፈጽመዉ ጥቃት የማይጠገን ጉዳት ይከተላታል ብለዋል፡፡

የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ መግለጫ እየሰጡ ይገኛል፡፡

በመግለጫቸዉማንኛውም አይነት የአሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃገብነት ሊስተካከል የማይችል ጉዳት እንደሚከተለዉ ጥርጥር የለውም ብለዋል።

የበላይ መሪዉ ኢራናውያን እጃቸውን የሚሰጡ አይደሉም ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ኢራንን እንዲሁም ህዝቦቿን እና ታሪኳን የሚያውቁ ብልሆች ይህንን ህዝብ በእንደዚህ ዓይነት የዛቻ ቋንቋ በጭራሽ አይናገሩም ምክንያቱም ኢራናውያን እጃቸውን የሚሰጡ ስላልሆኑ ብለዋል፡፡

እናም አሜሪካኖች ማንኛውም የአሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃገብነት የማይጠገኑ መዘዞችን ይዞ እንደሚመጣ ማወቅ አለባቸዉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡

የኢራን ጠቅላይ መሪ አሊ ኻሜኒ አሁን የሰጡትን መግለጫ በታሲም የዜና አገልግሎት ቴሌቭዥን እየተላለፈ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

18/06/2025

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት (IDF)፣ በኢራን ውስጥ በሚገኝ አንድ የአየር ኃይል ማዘዣ ጣቢያ ላይ ትክክለኛ ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት መሰንዘሩን የእስራኤል ምንጮች አስታወቁ። በጥቃቱ ወቅት እስከ አምስት የሚደርሱ AH-1J "ኮብራ" የተሰኙ ጥቃት ፈጻሚ ሄሊኮፕተሮች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገልጿል።

የወደሙት ሄሊኮፕተሮች፣ ኢራን በሻህ ዘመነ መንግስት በ1970ዎቹ ከዩናይትድ ስቴትስ የተረከበቻቸው ሲሆኑ፣ በዚህም እድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ መሆኑ ተገልጿል። እነዚህ ሄሊኮፕተሮች ከሳዳም ሁሴን ጦር ጋር በተደረገው የኢራን-ኢራቅ ጦርነት ወቅት በብዛት ቢወድሙም፣ የተወሰኑት ተርፈው ለአገልግሎት በቅተዋል።ጥቃቱ በሚፈጸምበት ወቅት የሄሊኮፕተሮቹ ትክክለኛ ቴክኒካዊ ሁኔታ ምን ይመስል እንደነበር ባይታወቅም፣ በይፋ ግን በአገልግሎት ላይ እንደነበሩ ተመዝግበው ነበር።

ከታማኝ ምንጮች እንደተገኘው መረጃ፣ አሁን ያለው ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ኢራን ከእነዚህ አይነቶች ሄሊኮፕተሮች ጥቂቶቹ ብቻ ነበሯት። በመሆኑም የአምስት ሄሊኮፕተሮች መውደም በኢራን አቅም ላይ የተወሰነ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ይገመታል።

በተያያዘ ዜና፡ የኢራን የአየር መከላከያ ኃይል በእስራኤል የተሰራ 'ሄርሜስ 900' የተባለ ጥቃት ፈጻሚ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) በኢስፋሃን ግዛት ሰማይ ላይ መትቶ መጣሉን አስታወቀ። ድሮኑ ሲወድቅ የተቀረጸ የቪዲዮ ምስል መውጣቱ፣ ጥቃቱ የተሳካ መሆኑን በምስል ያረጋገጠ ሆኗል።

ይህ ክስተት ላለፉት ስድስት ቀናት በዘለቀው የእስራኤልና የኢራን ውጥረት ውስጥ ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ አረጋግጣ የጣለችው የአየር ላይ ኢላማ ነው።

በተጨማሪም ድሮኑ የወደቀው በራሷ የኢራን ግዛት ውስጥ መሆኑ፣ ሀገሪቱ የአየር ክልሏን የመከላከል አቅሟን ያሳየችበት ክስተት ተደርጎ ተወስዷል።

18/06/2025

(GMN - አጭር ትንታኔ) በኢራን እና እስራኤል መካከል በተፈጠረው ግጭት አሜሪካ ምን ዓይነት ሚና እንደምትጫወትእስካሁን ግልጽ አይደለም። ነገር ግን ዛሬ ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ የተለያየ የሚያወዛግብ መልዕክት ሲያስተላልፉ በመዋላቸው "የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሀገሪቱ ወደ ውጊያ እንድትገባ የመወሰን ምን ያህል ስልጣን አላቸው?" የሚለውን ጥያቄ አስነስቷል።

በአሜሪካ ሕግ መሰረት፣ ፕሬዝዳንቱ በሌላ ሀገር ላይ በይፋ ጦርነት የማወጅ ስልጣን የላቸውም። ይህን ማድረግ የሚችለው ኮንግረስ - ማለትም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በሴኔት ውስጥ የተመረጡ ህግ አውጪዎች - ብቻ ነው።

ነገር ግን ህጉ ፕሬዝዳንቱ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ መሆናቸውን ይደነግጋል። ይህም ማለት ፕሬዝዳንቱ በይፋ ጦርነት ሳያውጁ ወታደሮችን ማሰማራት እና ወታደራዊ ዘመቻዎችን ማካሄድ ይችላሉ ማለት ነው።

ለምሳሌ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በ2017 በሶሪያ የአል-አሳድ አስተዳደር የአየር ጥቃት ለመፈጸም የወሰኑት ውሳኔ የኮንግረስን ይሁንታ አላስፈለገውም። በምትኩ፣ ፕሬዝዳንቱ የብሔራዊ ደህንነት እና የሰብአዊነት ጉዳዮችን በመጥቀስ በራሳቸው ውሳኔ እርምጃ ወስደዋል።

አሁን ላይ፣ ከተለያዩ ፓርቲዎች የተውጣጡ አንዳንድ ህግ አውጪዎች የፕሬዝዳንቱን በኢራን ላይ የአየር ጥቃት የማዘዝ ስልጣን ለመገደብ እየሞከሩ እንደሆነ ተሰምቷል። የኬንታኪው ሪፐብሊካን ተወካይ ቶማስ ማሲ ዛሬ ማክሰኞ "ትራምፕ እንዲህ ዓይነት እርምጃ ያለ ኮንግረስ ይሁንታ እንዳይወሰዱ የሚከለክል" ረቂቅ ህግ አቅርበዋል።

የሪፐብሊካን ተወካዩ በኤክስ ገጻቸው ላይ፣ "ይህ የእኛ ጦርነት አይደለም። ቢሆንም እንኳ፣ በህገ መንግስታችን መሠረት በእንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ላይ መወሰን ያለበት ኮንግረስ ነው" ብለዋል።

14/06/2025
10/04/2025

Waaqi kan isin haa oolchu

ጉለሌ ሚዲያ ኔትዎርክ /GMN_የሲዳማ ክልል መንግሥት በበህብረተሰቡ የተነሳበትን ከፍተኛ ተቃውሞ  ለመሸፋፈን ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ  ገንዘብ ከመንግስት ካዝና ወጪ ማድረጉ ታወቀ ።*...
06/04/2025

ጉለሌ ሚዲያ ኔትዎርክ /GMN_የሲዳማ ክልል መንግሥት በበህብረተሰቡ የተነሳበትን ከፍተኛ ተቃውሞ ለመሸፋፈን ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ከመንግስት ካዝና ወጪ ማድረጉ ታወቀ ።
**********
አርቲስት ቶክቻው በክልሉ የተንሰራፋውን የመልካም አስተዳደር ኦጦት እና የሙስና ቅሌት በመቃወም በክልሉ መንግስት ላይ በተከታታይ ትችት እየሰነዘረ መሆኑ ይታወቃል ። ለዚህም ትችት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደሰታ ሌዳሞ ሚዲያዎችን ጋብዘው ትዝብት ላይ የጣላቸውን ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል ።

በአሁን ወቅት በክልሉ የሚገኙ ሌሎች አርቲስቶች ፣ መምህራን እና መላው ህብረተሰብ ትግሉን በመቀላቀል በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ በማጋለጥ ላይ ይገኛሉ። ። በዚህም አርቲስት ኢትዮጵያ በቀለችን ጨምሮ በርካቶች ታስረዋል።

በተጨማሪም በአቶ ደሰታ ሌዳሞ የሚመራው የክልሉ መንግስት አርቲስቱ የተቃውሞ ትችት ማሰማት ከጀምረ ቀን አንስቶ የተከፈተበትን የሙስናና የብልሹ አሰራር ክስ ለመከላከልና ለገጽታ ግምባታ ሥራ ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ ብቻ ወደ ሁለት መቶ ሚሊዮን ብር የመንግስትና የህዝብ ገንዘብ እንዲባክን ማድረጉን የርዕሰ መስተዳድሩ የፋይናንስ ምንጮቻችን ነግረውናል።

ገንዘቡ በፕሬዝዳንቱ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ወጭ ተደርጎ ለገፅታ ግንባታ ሰብሰባዎች፣ በጉብኝት፣ ለተካፋይ አክቲቪስቶች እና ሚድያዎች እንዲሁም ለሎቢስቶች መከፈሉን እና እስካሁንም እየተከፈለ እንደሆነ ተነግሯል።

ፕረዝዳንቱ የተለያዩ ነቢያት ነን የሚሉ ሰዎችን ቤተመንግሥት በመጋበዝ ከመንግሥት ወጪ ድግስ ደግሰው "ትንቢት" እያስነገሩ እንደሚገኝ የነገሩን ምንጫችን ከአርቲስት ቶክቻው በተጨማሪ በፌደራል ስልጣንና በአምባሳደርነት ሹመት ላይ የሚገኙ የብሔሩ ተወላጆች ላይ ጥርስ እንደነከሱባቸው የመረጃ ምንጫችን አክለው ነግረውናል።

ጉለሌ ሚዲያ ኔትዎርክ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gulale Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gulale Media Network:

Share