Mehaleq Radio Show-መሃለቅ

Mehaleq Radio Show-መሃለቅ “Mehaleq” is a radio show focusing on economic, investment, and Business issues and brought to you through Arada FM 95.1 Radio.

It is produced by Kal Multimedia & Communication Plc.

30/06/2023
ተሽከርካሪዎች በመንገድ ላይ ችግር ሲገጥማቸው በፍጥነት እገዛ ለማግኘት የሚያስችላቸው አዲስ የሞባይል መተግበሪያ (Mobile Application) ይፋ ተደረገ፡፡ረብዑ መጋቢት 20 ቀን 2015...
29/03/2023

ተሽከርካሪዎች በመንገድ ላይ ችግር ሲገጥማቸው በፍጥነት እገዛ ለማግኘት የሚያስችላቸው አዲስ የሞባይል መተግበሪያ (Mobile Application) ይፋ ተደረገ፡፡
ረብዑ መጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ይፋ የተደረገው ይህ መፍትሔ ሰጪ መተግበሪያ ‹‹ኑሀ የመንገድ ዳር እርዳታ ሰጪ /Nuha Roadside Assistant/›› የተሰኘ መተግበሪያ ነው፡፡
‹‹የሰው ልጅ የጤና ችግር ሲገጥመው የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ተሸከርካሪዎችም በመንገድ ላይ እክል ሲገጥማቸው የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ያስፈልጋቸዋል›› ያሉት የአዲስ አበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ እና የትራፊክ ደህንነት የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ የሆኑት ኢንስፔክተር አሰፋ መዝገቡ ‹‹ኑሀ መተግበሪያ ለተሸከርካሪ የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ የሚሰጥ መፍትሔ ነው›› ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ የትራፊክ ሕግ አንድ ተሸከርካሪ በብልሽት ምክንያት በከተማ ውስጥ ከሁለት ሠዓታት በላይ ከከተማ ውጪ ደግሞ እንደመንገዱ ሁኔታ ከስምንት ሠዓታት በላይ መቆም እንደማይፈቀድለት ያወሱት ኢንስፔክተር አሰፋ ይሁንና አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መኪኖች በብልሽት ምክንያት ከህግ ውጪ ለቀናት ቆመው ይታያሉ ብለዋል፡፡ ‹‹በእዚህ ሳቢያ በከተማዋ ስለሚደርሰው የትራፊክ አደጋ እና መጨናነቅ ከእኔ በላይ አስረጂ ሊኖር አይችልም›› ያሉት ኢንስፔክተር አሰፋ ‹‹ኑሀ መተግበሪያ ለእዚህ ችግር ፍቱን መፍትሔ ነው›› ብለዋል፡፡
ኑሃ መተግበሪያ አሽከርካሪዎች በቀላሉ ከጉግል ፕሌይ ስቶር አውረደው በስልካቸው ላይ ሊጭኑት የሚችሉት መተግበሪያ ነው፡፡ ይህንን መተግበሪያ ጭነው የተመዘገቡ አሽከርካሪዎች በጉዞ ላይ የተሽከርካሪ ችግር በሚገጥማቸው ጊዜ ቢበዛ ከግማሽ ሠዓት ባልበለጠ ጊዜ ሙያተኛ ያሉበት ድረስ መጥቶ እገዛ እንዲያገኙ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡ የተሽከርካሪው እክል በስፍራው በተገኘው የቴክኒክ ሙያተኛ ወዲያው የሚፈታ ካልሆነ ደግሞ መኪናውን አስጭኖ ጥገና የሚያገኝበት ቦታ ድረስ በነፃ የማድረስ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
በእዚህ መተግበሪያ ወይም በአጭር የስልክ ቁጥር 6516 ላይ ተመዝግበው የኑሀን አገልግሎት ለሶስት ወራት ለማግኘት 825 ብር የሚከፈል ሲሆን ለስድስት ወራት አገልግሎት 1,500 ብር ለአንድ ዓመት አገልግሎት ደግሞ 3,000 ብር ይከፈላል፡፡
የደንበኝነት ክፍያን በቴሌ ብር ለመክፈል እንዲቻል በኑሀ የመኪና ብልሽት እርዳታ ሰጪ ድርጅትና በቴሌ ብር እልፍ ጉዳይ መተግበሪያ መካከል ስምምነት ተደርጓል፡፡
በኑሀ መተግበሪያው ይፋ ማድረጊያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የኢትዮ ቴሌኮም የቴሌ ብር ዳይሬክተር አቶ ሞሃመድ አብዱልሠመድ በኢትዮ ቴሌኮም ብቻ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ እንደማይቻል አስታውሰው ‹‹ዛሬ በተለይ በትራንስፖርቱ ዘርፍ ከፍተኛ መነቃቃት አለ፡፡ ይህ የኑሀ ተግባር ያንን መነቃቃት የበለጠ የሚያጠናክር እመርታ ነው›› ብለዋል፡፡
በኑሀ መተግበሪያ ለመገልገል የተመዘገበ አሽከርካሪ በጉዞ ላይ የጎማ ብልሸት፣ የነዳጅ ማለቅ፣ የመኪና በጭቃ ወይም በጉድጓድ መያዝ ቢያጋጥመው እንዲሁም ባትሪ ቢደክምበት እና የመኪናውን ቁልፍ ከውስጥ ሳያወጣ በሩ ቢቆለፍበት በፍጥትነት የእገዛ አገልግሎት እንደሚያገኝ ታውቋል፡፡ ፊውዝ መቀየርን ጨምሮ በአጠቃላይ ለሚያጋጥሙ ቀላል ብልሽቶች በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለእዚሁ ተግባር በተመደቡና በተጠነቀቅ በሚጠባበቁ የድርጅቱ ሙያተኞች እገዛ የሚሰጥ መሆኑንም የድርጅቱ መሥራች የሆኑት ወንድማማቾቹ ፍፁም እና ነቢዩ ዘካሪያስ ገለፀዋል፡፡

Tonight!!
29/03/2023

Tonight!!

10/03/2023
ጋዜጣዊ መግለጫአራዳ ኤፍኤም 95.1 ስርጭቱን በመጪው ሰኞ በይፋ ይጀምራል::በሰላም መልቲሚዲያ ኃ.ተ.የግ. ማኅበር ሥር የተቋቋመው አራዳ ኤፍኤም 95.1 የሬዲዮ ጣቢያ በመጪው ሰኞ መጋቢት 4...
10/03/2023

ጋዜጣዊ መግለጫ
አራዳ ኤፍኤም 95.1 ስርጭቱን በመጪው ሰኞ በይፋ ይጀምራል::
በሰላም መልቲሚዲያ ኃ.ተ.የግ. ማኅበር ሥር የተቋቋመው አራዳ ኤፍኤም 95.1 የሬዲዮ ጣቢያ በመጪው ሰኞ መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ሥርጭቱን በይፋ ይጀምራል፡፡
በሚዲያው ዘርፍ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ትብብር የተቋቋመው አራዳ ኤፍኤም 95.1፤ በመዝናኛ፣ ስፖርትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ የሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡
ጣቢያው ከሰኞ እስከ እሁድ በቀን ለ18 ሰዓታት በተለያዩ ዝግጅቶች በአዲስ አበባና አካባቢዋ በሚገኙ ከተሞች የሚደርስ ሲሆን፤ እስካሁን አየር ላይ በቆየባቸው የሙከራ ግዜያት በጣቢያውና በተባባሪ ፕሮግራም አዘጋጆቹ በመዝናኛና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡
ከመጪው ሰኞ ከመጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በተሟላ አቅም ስራውን ይጀምራል፡፡
አራዳ ኤፍኤም 95.1 ዘመኑ የደረሰባቸው ዘመናዊ የማሰራጫና የስቱዲዮ መሳሪያዎችን የረዥም ጊዜ ልምድ ካላቸው ባለሙያዎች ጋር አጣምሮ በስቱዲዮዎቹ በተገጠሙት ካሜራዎች አማካኝነት በራዲዮ-ቪዥን ዘዴ የተመረጡ ፕሮግራሞቹን ያሰራጫል፡፡
ጣቢያው በአበይት የማኅበራዊ ሚዲያዎች ተደራሽ ሲሆን በድረገፁ www.aradafm.com በቀጥታ ስርጭት በመላው ዓለም ለሚገኙ አድማጮች ይደርሳል፡፡
አራዳ ኤፍኤም 95.1 መደበኛ ስርጭቱን በሚጀምርበት ዕለት የጣቢያው ሰራተኞች ፤ተባባሪ ፕሮግራም አዘጋጆቸ እና በጎ ፈቃደኛ የሆኑ አድማጮችን አስተባብሮ የደም ልገሳ ያደርጋል፡፡

“አራዳ ኤፍኤም 95.1 ውለው የሚያመሹበት”

28/01/2023

መሃለቅ የሬዲዮ መርሃ-ግብር ነገ እሁድ ቀትር ከ6፡00-7፡00 ሠዓት በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1
በእዚህ ሣምንት መርሃ-ግብራችን፡-
-በሣምንቱ የተከናወኑ አንኳር ምጣኔ ኃብታዊ ዜናዎች በ‹‹መሠንበቻ›› ክፍለ ጊዜ፣
-ለአንድ አገር የምጣኔ ኃብት እድገት ወሳኝ የሆነውን የውጪ ቀጥታ መዋዕለ-ንዋይ (Foreign Direct Investment/FDI) ለመሳብ ወሳኝ (Determinants) ከሆኑ ስምንት ነጥቦች ውስጥ አንዱ ስለሆነው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ መረጋጋት (Political, Economy and Social Stability) በ‹‹ሲራራ›› ክፍለ-ጊዜያቸን፣
-በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብታዊ ስሪት ምን መልክ ነበረው የሚለው ታሪክ በ‹‹ብራና›› ክፍለ-ጊዜያችን ይደመጣሉ፡፡
ዝግጅታችንን ያዳምጡ፣ ይጠቀሙበታል!!
በሬዲዮ ሲተላለፍ ያመለጥዎን ዝግጅቶቻችንን በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ያገኟቸዋል!!! https://t.me/mehaleqradioshow
የኢንስታግራምና የፌስቡክ ገፆቻችንንም ይወዳጁ፡፡
https://www.instagram.com/mehaleqradioshow/
https://www.facebook.com/mehaleqradio
አስተያየትዎን፡-በ [email protected]
ወይንም በሞባይል ሥልክ ቁጥራችን፡-+251 925 003348 በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ይላኩልን!!!
መልካም ዕለተ-ሠንበት ይሁንልዎ!!
ነገ ረፋድ አራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ሬዲዮ ላይ እንገናኝ!!!

መሃለቅ የሬዲዮ መርሃ-ግብር ነገ እሁድ ቀትር ከ6፡00-7፡00 ሠዓት በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ላይ ይደመጣል!!በእዚህ ሣምንት መርሃ-ግብራችን፡--በሣምንቱ የተከናወኑ አንኳር ምጣኔ ኃብታዊ ዜ...
21/01/2023

መሃለቅ የሬዲዮ መርሃ-ግብር ነገ እሁድ ቀትር ከ6፡00-7፡00 ሠዓት በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ላይ ይደመጣል!!
በእዚህ ሣምንት መርሃ-ግብራችን፡-
-በሣምንቱ የተከናወኑ አንኳር ምጣኔ ኃብታዊ ዜናዎች በ‹‹መሠንበቻ›› ክፍለ ጊዜያችን ይቀርባሉ፣
-ለአንድ አገር የምጣኔ ኃብት እድገት ወሳኝ የሆነውን የውጪ ቀጥታ መዋዕለ-ንዋይ (Foreign Direct Investment/FDI) ለመሳብ ወሳኝ (Determinants) ከሆኑ ስምንት ነጥቦች ውስጥ አንዱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ መረጋጋት (Political, Economy and Social Stability) ነው፡፡ በእዚህ ረግድ ኢትዮጵያ ምን ላይ ትገኛለች? ምን ማድረግስ ይጠበቅበታል በሚለው ጉዳይ ላይ ከሙያተኛ ጋር የተደረገ ውይይት በ‹‹ሲራራ›› ክፍለ-ጊዜያቸን ይቀርባል፡፡
-በ19ኛው እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብታዊ ስሪት ምን መልክ ነበረው የሚለው ታሪክ በ‹‹ብራና›› ክፍለ-ጊዜያችን ይደመጣል፡፡
ዝግጅታችንን ያዳምጡ፣ ይጠቀሙበታል!!
በሬዲዮ ሲተላለፍ ያመለጥዎን ዝግጅቶቻችንን በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ያገኟቸዋል!!! https://t.me/mehaleqradioshow
የኢንስታግራምና የፌስቡክ ገፆቻችንንም ይወዳጁ፡፡
https://www.instagram.com/mehaleqradioshow/
https://www.facebook.com/mehaleqradio
አስተያየትዎን፡-በ [email protected]
ወይንም በሞባይል ሥልክ ቁጥራችን፡-+251 925 003348 በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ይላኩልን!!!
መልካም ዕለተ-ሠንበት ይሁንልዎ!!
ነገ በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ሬዲዮ አየር ላይ እንገናኝ!!!

17/12/2022

መሃለቅ የሬዲዮ መርሃ-ግብር ነገ እሁድ ቀትር ከ6፡00-7፡00 ሠዓት በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ላይ ይደመጣል!!
በእዚህ ሣምንት መርሃ-ግብራችን፡-
-በሣምንቱ የተከናወኑ አንኳር ምጣኔ ኃብታዊ ዜናዎች በ‹‹መሰንበቻ›› ክፍለ ጊዜያችን ይቀርባሉ፣
-በኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት ውስጥ የጥቃቅን አነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች (Micro, Small and Medium Enterprises) ያላቸውን ድርሻና ያሉበትን ደረጃ የሚዳስሰው ውይይት ሦስተኛው ክፍል በ‹‹ሲራራ›› ዝግጅታችን ይደመጣል፣
-በ‹‹ወጌሻ›› ዝግጅታችን ደግሞ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞቸ ስለሚቋቋሙበትና ስለሚታዳደሩበት ሁኔታ የተደነገገውን የአገራችንን ሕግ ይዘት አዘጋጁ የሕግ ባለሙያ ያሠናዱትን ሙያዊ ገለፃ ታዳምጣላችሁ፡፡
በሬዲዮ ሲተላለፉ ያመለጧችሁን ዝግጅቶቻችንን በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ታገኟቸዋላችሁ!!! https://t.me/mehaleqradioshow
የኢንስታግራምና የፌስቡክ ገፆቻችንንም ተወዳጁ፡፡
https://www.instagram.com/mehaleqradioshow/
https://www.facebook.com/mehaleqradio
አስተያየታችሁን፡-በ [email protected]
ወይንም በሞባይል ሥልክ ቁጥራችን፡-+251 925 003348 በአጭር የጹሁፍ መልዕክት ላኩልን!!!
መልካም ዕለተ-ሠንበት ይሁንላችሁ!!
ነገ በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ሬዲዮ አየር ላይ እንገናኝ!!!

03/12/2022

መሃለቅ የሬዲዮ መርሃ-ግብር ነገ እሁድ ቀትር ከ6፡00-7፡00 ሠዓት በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ላይ ይደመጣል!!
በእዚህ ሳምንት መርሃ-ግብራችን፡-
-በሣምንቱ የተከናወኑ አንኳር ምጣኔ ኃብታዊ ዜናዎች በ‹‹መስንበቻ›› ዝግጅት ይቀርባሉ፣
-በኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት ውስጥ የጥቃቅን አነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች ያላቸው ድርሻና ያሉበት ደረጃ በ‹‹ሲራራ›› ዝግጅታችን ይደመጣል፣
-በ‹‹ብራና›› ዝግጅታችን የኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት በ19ኛው መቶ ዓመት የነበረበትን ሁኔታ የሚያስቃኝ ታሪክ ይቀርባል፡፡
በሬዲዮ ሲተላለፉ ያመለጧችሁን ዝግጅቶቻችንን በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ታገኟቸዋላችሁ!!! https://t.me/mehaleqradioshow
የኢንስታግራምና የፌስቡክ ገፆቻችንንም ተወዳጁ፡፡
https://www.instagram.com/mehaleqradioshow/
https://www.facebook.com/mehaleqradio
አስተያየታችሁን፡-በ [email protected]
ወይንም በሞባይል ሥልክ ቁጥራችን፡-+251 925 003348 በአጭር የጹሁፍ መልዕክት ላኩልን!!!
መልካም ዕለተ-ሠንበት ይሁንላችሁ!!
ነገ በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ሬዲዮ አየር ላይ እንገናኝ!!!

20/11/2022

“Mehaleq” is a radio show focusing on economic, investment, and Business issues and brought to y

20/11/2022

የመሃለቅ የሬዲዮ መርሃ-ግብር ዛሬ እሁድ ቀን ከ6፡00-7፡00 ሠዓት በአራዳ ኤፍ ኤም 95.1 ላይ ሲተላለፍ ሳያዳምጡ አልፎዎ ከሆነ ረበረዑ ምሽት ከ1፡00-2፡00 ይደገማልና ይከታተሉ!!
አልያም ከታች የሰፈረውን ማስፈንጠሪያ ተጭነው በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ያገኙታል፡፡
https://t.me/mehaleqradioshow
አዳምጠው አስተያየትዎን፡-በ [email protected] ወይንም በሞባይል ሥልክ ቁጥራችን፡-+251 925 003348 በአጭር የጹሁፍ መልዕክት ይላኩልን!!!
ደግሞም የማኅበራዊ መገናኛ ድረ-ገፆቻችን ወዳጅ/ባልንጀራ ይሁኑ!!
https://t.me/mehaleqradioshow
https://www.instagram.com/mehaleqradioshow/
https://www.facebook.com/mehaleqradio

“Mehaleq” is a radio show focusing on economic, investment, and Business issues and brought to y

Address

Kazanchis
Addis Ababa
1000

Telephone

+251925003348

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mehaleq Radio Show-መሃለቅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mehaleq Radio Show-መሃለቅ:

Videos

Share