
05/01/2025
"መደበኛ ህዋስ ውይይት ለተሻለ ተቋም ግንባታ"
በወረዳችን የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ የሁሉም ማህበራዊ መሰረት የሚገኙ ህዋሳቶች ወርሀዊ መደበኛ የህዋስ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
በለሚ ኩራ ወረዳ 06 የብልጽግና ፓርቲ የመኖሪያ ፣የቢሮ ፣የጥቃቅን፣የትምህርት ቤት፣የወጣት ሊግ ፣የሴት ሊግ ፣ተቋማቶች በሚገኙበት ቀጠናና በተቋማቸው በየህዋሶቻቸው ወርሀዊ ውይይት በሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያና የኮር ሚና በሚል አጀንዳ በሳል ውይይቶች እየተደረጉ ይገኛል።
በውይይቱ ሚዲያ ህዝብ ጋር ለመድረስ ትልቅ በቀጣይ አቅም እንዳለውና ለበጎ ስራ ሚዲያን በመጠቀም ፓርቲያችን የሰራቸውን ስራዎች በሰፊው ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ተግባቦት መፍጠር ተችሏል።
ለሚ ኩራ ወረዳ 6 ፓርቲ ሚዲያ
ታህሳስ 26/2017 ዓ ም