Shewa Media

Shewa Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Shewa Media, Media/News Company, Unated State, Addis Ababa.

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !! የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተ...
22/01/2025

ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ የሐዘን መግለጫ
ታጋይ ይሰዋል ትግል ይቀጥላል !!

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው እና አሁን ላይ በአማራ ፋኖ በጎጃም የሁለተኛ (ተፈራ ) ክፍለጦር ሰብሳቢ የነበረው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በክብር ተሰዋ።

የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህሎና አደጋ ለመቀልበስ ያለ እረፍት ከአባልነት እስከ ከፍተኛ አመራርነት ግንባር ቀደም ትግል ሲያደርግ የነበረው ጀግናው ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ ጥር 12 ቀን ሌሊት ለጥር 13 አጥቢያ ዋሸራ በተባለ ቦታ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት ተናንቆ የክብር መስዕዋትነትን ተቀብሏል ።

ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በጎንጅ ቆለላ ወረዳ ጎንጅ ወ እንዘግድም በተባለ ቦታ የተወለደ ሲሆን የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ከማጠናቀቁ በፊት "በአማራ ተማሪዎች ማህበር አተማ " ከፍተኛ አመራር በመሆን ወቅቱ የጠየቀውን ትግል አድርጓል ።
ከዚያም አብይ አህመድ አማራን መውረሩን ተከትሎ ወደ ትውልድ ቀዬው እንዘግድም በመሔድ ቀደም ሲል የነበረውን " ጎንጅ ወ እንዘግድም ብርጌድን" የአሁኑን "ንስር ብርጌድን" ከሌሎች ጓዶቹ ጋር በመመስረት አይተኬ የትግል አሻራ ያሳረፈ ጀግና ነበር።

ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ በሞጣ : በአዴት : በምላጭበር : በፈረስ ቤት በቋሪት ከትግል ጓዶቹ ጋር በመሆን ከባድ ውጊያ ያደረገ ልበ ቆራጥ አርዓያ ፋኖ ነበር።

የአማራ ፋኖ በጎጃም ከተመሰረተ ዕለት ጀምሮ በአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኘነት ሀላፊ በመሆን ሰለቸኝ ታከተኝ ሳይል ያገለገለ ሲሆን ከቅንነት የመነጨ ልበ ቆራጥነትን ያስመሰከረ እና ታታሪነትን እና ለህዝብ ዋጋ መክፈልን መርህ ያደረገ ጀግና የፋኖ አመራር ነበር።

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ በነበረበት ጊዜ ያለፈውን ፈታኝ ጊዜ በመረዳት የመምራት እና ችግርን የመፍታት ትልቅ አቅሙ ታምኖበት የሁለተኛ ( ተፈራ) ክፍለጦር ሰብሳቢ በመሆን ትልቅ የመንፈስ መነቃቃትን የፈጠረ ታጋያችን ነበር።

ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ሌሊት ለጥር 13 አጥቢያ ጠላት ወደ ዋሸራ ከተማ ለመግባት በመገስገስ ላይ እያለ ባደረገው የፊት ለፊት ውጊያ አብሪ የጠላት ሐይሎችን በመደምሰስ የክብር መስዕዋትነትን ተቀብሏል ።

ፋኖ ዮሐንስ አለማየሁ ፅናትን : መታመንን : ቁርጠኝነትን እና መስዕዋትነትን ከታላላቅ ሰማዕታት ፋኖዎች በመውረስ ለቀሪው የአማራ ትውልድ ዕውነትን አስተምሮ ያለፈ ጀግና ነው።

ድርጅታችን የአማራ ፋኖ በጎጃም የፋኖ ዮሐንስ አለማየሁን ክብር የሚመጥን ዝግጅት እንደሚያደርግ እየገለፀ ለትግል ጓዶቹ እና ለቤተሰቦቹ መፅናናትን ይመኛል ።

የ ግፍ ግፍ ወላጅ በተገኘበት ልጅን መረሸን😭ቪድዮከቴሌግራም ያግኙ።https:://t.me/showapress
18/01/2025

የ ግፍ ግፍ ወላጅ በተገኘበት ልጅን መረሸን😭

ቪድዮከቴሌግራም ያግኙ።
https:://t.me/showapress

16/01/2025

የ አማራ ፋኖ በጎጃም ዝናቡ አዘነበው።

22/12/2024

ይህ ጭቆናን የተጠየፈው የመኖር ህልውናው ለማረጋገጥ የሚታገለው አድሱ ትውልድ አማራ ፋኖ ነው።

19/12/2024

አስቸኳይ ትኩረት ይደረግበት🔴

ህጻናት በርሃብ እየሞቱ፣ እየተሰቃዩ ነው። የወገኖቻችን ስቃይ በዜና፣ ቀጥሎ በፎቶ፣ ዛሬ ደግሞ በቪዲዮ ተጋልጧል። ቪዲዮው የላስታ አሳምነው ኮር የሚዲያ ቡድን ነው!

https://t.me/showapress

19/12/2024

የ አማራ ፋኖ ኮማንዶ ይሄን ሀይል ከፈጣሪ በቀር ማንቻውም ሀይል ሊያስቆመው አይችልም ✊✊

ስማችን አማራ !
መጠሪያችን ፋኖ❤️❤️

በአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አንኮበር  አፄ ዘራያቆብ ክ/ጦር ጣይቱ ብርጌድ  በሚንቀሳቀስበት ቀጠና  በተለያየዩ ቀበሌዎች ህዝብ መንግስትና መከላከያን የሚቃወም ሰልፍ አድርገዋል።   ...
18/12/2024

በአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አንኮበር አፄ ዘራያቆብ ክ/ጦር ጣይቱ ብርጌድ በሚንቀሳቀስበት ቀጠና በተለያየዩ ቀበሌዎች ህዝብ መንግስትና መከላከያን የሚቃወም ሰልፍ አድርገዋል።

ተጨማሪ መረጃ ከቴሌግራም ያግኙ።
https://t.me/Showapress

ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት አስተላልፏል !       ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ሥርዓቱን ያሸነፍን መሆኑን ከብልግናው ቡድን በኩል ጥፍር ታክል ልቡ የሚጠራጠር ባተሌ ካድሬ ቢኖር የዛ...
18/12/2024

ራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ መልዕክት አስተላልፏል !
ታህሳስ 9 ቀን 2017 ዓ.ም

ሥርዓቱን ያሸነፍን መሆኑን ከብልግናው ቡድን በኩል ጥፍር ታክል ልቡ የሚጠራጠር ባተሌ ካድሬ ቢኖር የዛሬው ውሎ በህዝብ የተመታ ታሪካዊ ማህተም ሆኖ ይወሰድ። በአብዮቱም በኩል ካሸነፍን የሰነበትን መሆኑን ማመን ያልቻለ አንድ እንኳን ፋኖ ቢኖር የዛሬውን ቀን ድሉን ከህዝብ ጋር ከፍ አድርጎ ያበሰረበት ዕለት አድርጎ ይፃፈው።

ስርዓቱ ተሸንፏል። ለበሰበሰው ቡድኑ ሽታ አፍንጫችን ስንሸፍን አይናችንም በጋቢያችን ሸፍነነው ካልሆነ በስተቀር ሥርዓቱ ተሸንፏል። በትውልዱ የድል ዋንጫና በኛ መካከል የቀረውን ስንዝር እርቀት ለመጓዝ ግን ጉልበታችን ቄጤማ ሁኗል። ከራያ እስከ ጉበያ፣ ከመተማ እስከ ወንበርማ፣ ከምንጃር እስከ አቸፈር ያካለለ ብርቱ እግራችን ስንዝር ለመራመድ ስለምን አቃተው ካልን መልሱ ትግሉ በአንድ መዋቅር ማሰር ስላልቻልን ነው ይሆናል። የቀረን ነገር ቢኖር ሰኞ በአንድ ቁመን ማክሰኞ ዕለት የድሉን ዋንጫ ማንሳት ብቻ ነው። እዚህ ላይ እንበርታ ።

[ክፋት ለማንም፣ በጎነት ለሁሉም]
አዲስ ትውልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ !
አንድ አማራ !!!

አርበኛ ዘመነ ካሴ

https://t.me/Showapress

17/12/2024

የ"ወለጋ ክፍለ ሀገር ፋኖ ዕዝ" ዛሬ በይፋ መመስረቱን አስታወቀ። ዕዙ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል መግለጫውን ያድምጡት።

የዛሬ ምኒሻ የነገ ፋኖዎች።
15/12/2024

የዛሬ ምኒሻ የነገ ፋኖዎች።

13/12/2024

ሲጀመር የባህር ሀይሉ ሸዋ ላይ አልቋል።

ስልክዎን ብቻ በመጠቀም ገንዘብ ይስሩ በቴሌግራም የሚደግፍ እና በቅርቡ list የሚሆን ፕሮጀክት ነው ብትሠሩት ተጠቃሚ  የምትሆኑበት አሪፍ Airdrop ነው ያልጀመራችሁ ተጠቀሙበት ለመጀመር ...
30/11/2024

ስልክዎን ብቻ በመጠቀም ገንዘብ ይስሩ በቴሌግራም የሚደግፍ እና በቅርቡ list የሚሆን ፕሮጀክት ነው ብትሠሩት ተጠቃሚ የምትሆኑበት አሪፍ Airdrop ነው ያልጀመራችሁ ተጠቀሙበት ለመጀመር ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ብላችሁ በመጀመር ታስኮቹን ስሩ👇👇

ስልክዎን ብቻ በመጠቀም ገንዘብ ይስሩ ከ Dog ጋር ተመሳሳይነት ያለው በቴሌግራም የሚደግፍ እና በቅርቡ list የሚሆን ፕሮጀክት ነው ብትሠሩት ተጠቃሚ  የምትሆኑበት አሪፍ Airdrop ነው ...
30/11/2024

ስልክዎን ብቻ በመጠቀም ገንዘብ ይስሩ ከ Dog ጋር ተመሳሳይነት ያለው በቴሌግራም የሚደግፍ እና በቅርቡ list የሚሆን ፕሮጀክት ነው ብትሠሩት ተጠቃሚ የምትሆኑበት አሪፍ Airdrop ነው Dog የሰሩ ጥሩ ተከፍሏቸዋል ያልጀመራችሁ ተጠቀሙበት ለመጀመር ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ብላችሁ ጀምሩ👇👇

"እስክንድር ዳዊት ይዞ ወደዛ ወደዚህ ሲል አምኜው ነበር" ሻለቃ መሳፍንት 😀😀😀
24/11/2024

"እስክንድር ዳዊት ይዞ ወደዛ ወደዚህ ሲል አምኜው ነበር"

ሻለቃ መሳፍንት 😀😀😀

ጠቃሚ ነገር ልጠቁማችሁ👉 በቴሌግራም የሚደግፍ እና በቅርቡ list የሚሆን ፕሮጀክት ነው ብትሠሩት ተጠቃሚ  የምትሆኑበት አሪፍ Airdrop ነው  ለመጀመር ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን   ብላ...
19/11/2024

ጠቃሚ ነገር ልጠቁማችሁ👉 በቴሌግራም የሚደግፍ እና በቅርቡ list የሚሆን ፕሮጀክት ነው ብትሠሩት ተጠቃሚ የምትሆኑበት አሪፍ Airdrop ነው ለመጀመር ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ብላችሁ ጀምሩ👇👇

16/11/2024

ባህርዳር የተመታዉ Helicopter አብራሪውን ጨምሮ ሁሉም ሞተዋል። ብርሀኑ ጁላ ሞቷል። የለም በህይወት
አለሁ አልሞትኩም ካለም። እያለ ዱብ ዱብ እያለ ካላየን አናምንም።

Address

Unated State
Addis Ababa

Website

https://youtube.com/channel/UC05y0-96PuPy2yRN0Sk4a3A

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shewa Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share