Channel 7 Ethiopia

Channel 7 Ethiopia ቻናል 7 ኢትዮጵያ ዲጂታል የመርጃ አውታር ነው ፡፡
ለአስተያየ

ከመስከረም ጀምሮ ለሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወሰነ ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡ 📌 ዝቅተኛ...
18/08/2025

ከመስከረም ጀምሮ ለሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወሰነ

ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡

📌 ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ 6 ሺህ ብር
📌 ፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ 39 ሺህ ብር
📌የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ 11 ሺህ 500 ብር

የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ፤ መንግሥት የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሀገር ዐቅም የሚፈቅደውን ርምጃ እየወሰደ ነው ብሏል፡፡

በዚህም ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት መወሰኑን አስታውቋል፡፡

በማሻሻያው ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4 ሺህ 760 ወደ ብር 6 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ነው ያለው።

ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21 ሺህ 492 ወደ ብር 39 ሺህ እንዲያድግ ይደረጋል ብሏል።

የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6 ሺህ 940 ወደ ብር 11 ሺህ 500 የሚሻሻል መሆኑን ገልጿል።

ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ እንደሚደረግበት አስታውቋል።

ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት ጠይቋል ያለው ኮሚሽኑ፤ ይሄም ለደመወዝ የሚወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል ብሏል።

ዘገባው የፋና ነው

አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።ተዋናይ ፣ኮሜዲያን፣ አዘጋጅ ሆኖ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል፡፡ በመድረክ ፣ በሬዲዩ፣ በቴሌቪዥን፣ በፊልም ስራ እና በጋዜጠኝነት ሙ...
17/08/2025

አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

ተዋናይ ፣ኮሜዲያን፣ አዘጋጅ ሆኖ ለረዥም ዓመታት አገልግሏል፡፡ በመድረክ ፣ በሬዲዩ፣ በቴሌቪዥን፣ በፊልም ስራ እና በጋዜጠኝነት ሙያ ሠርቷል ። በአፍሪካ የመድረክ ሙያተኞች ማህበር በሊቀመንበርነት መርቷል ፣ በአትላንታ ጆርጂያ በበረከተው የሙያው ሥራ ኖቬምበር 24 ቀን በስሙ ተሰይሞለታል። (ጋሽ ደቤ) በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በህይወት ካሉት አርቲስቶች ግንባር ቀደሙና አንጋፋው ነው።

ጋሽ ደቤ ጋደኛም ሚስትም ከሆነችው ከአልማዝ ደጀኔ ጋር 4 ልጆች እና 6 የልጅ ልጆች አሉት።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም አውሮፕላን ተጠግኖ ዳግም ለአገልግሎት በቃ ከአገልግሎት ውጪ የነበረውን የኢትዮጵያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አውሮፕላን ተጠግኖ ዳግ...
16/04/2025

የቀድሞው ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለማርያም አውሮፕላን ተጠግኖ ዳግም ለአገልግሎት በቃ

ከአገልግሎት ውጪ የነበረውን የኢትዮጵያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም አውሮፕላን ተጠግኖ ዳግም ጥቅም ላይ ማዋል መቻሉ ተገለፀ።

አውሮፕላኑን ከተጣለበት ጥሻ በማንሳት አፕግሬድና ኦቨር ሆል በማድረግ ከ37 ዓመት በኋላ የበረራ አገልግሎት እንዲሠጥ ማድረግ መቻሉን የመከላከያ ሠራዊት ገልጿል።

ኤ.ቲ.ኤም ማሽን ያለባቸው ቦታዎች ላይ በመገኘት ገንዘብ ሊያወጡ የሚመጡ ግለሰቦችን የሚረዳ መስሎ ሚስጥር ቁጥራቸውን በማየትና ሌላ ካርድ  በመቀየር  የማጭበርበር ወንጀል ይፈፅም የነበረን ተ...
16/04/2025

ኤ.ቲ.ኤም ማሽን ያለባቸው ቦታዎች ላይ በመገኘት ገንዘብ ሊያወጡ የሚመጡ ግለሰቦችን የሚረዳ መስሎ ሚስጥር ቁጥራቸውን በማየትና ሌላ ካርድ በመቀየር የማጭበርበር ወንጀል ይፈፅም የነበረን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 08 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ተጠርጣሪው አለማየሁ የስጋት ይባላል፡፡ የወንጀል ድርጊቱን የሚፈፅመው ኤ.ቲ. ኤም ያለባቸው ቦታዎች በመገኘት ገንዘብ ሊያወጡ የሚመጡ በተለይም ደጋግመው የሚሞክሩ ሰዎችን ሲያይ የካርዳቸውን የሚስጥር ቁጥር በማየትና የሚረዳ በመምሰል ካርዳቸውን ወዲያው በሌላ በመቀየር እና ከአካባቢው በፍጥነት በመሰወር ከሌላ ማሽን ገንዘባቸውን አውጥቶ የሚሰወር ነው፡፡

ግለሰቡ በተመሳሳይ የወንጀል አፈፃፀም ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ/ም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ፈረንሳይ ማዞሪያ አካባቢ ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከቀኑ7:30 ሠዓት በመገኘት አንዲት ግለሰብ ገንዘብ ለማውጣት ሲሞክሩ ከኋላቸው ሆኖ የካርዱን ሚስጥር ቁጥር ካየ በኋላ የሚረዳ መስሎ በመቅረብ ማሽኑ እምቢ ብሏል እስኪ በሌላ ይሞክሩ በማለት ካርዳቸውን ይዞ ይሄዳል፡፡ ግለሰቧም እውነት መስሏቸው ካርዱን ተቀብለው ደጋግመው ሲሞክሩ የተመለከታቸው የባንኩ ማናጀር ካርዳቸውን ተቀብሎ ሲያረጋግጥ የግል ተበዳይ አለመሆኑን በማወቁ ተከሳሹ ከአካባቢው ሳይርቅ በፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል።

ተከሳሹ ኪሱ ሲፈተሽም 4 የንግድ ባንክና 3 የአቢሲኒያ ባንኮች ኤ.ቲ.ኤም ካርዶች ከኪሱ የተገኘ ሲሆን ተጠርጣሪው ከ6 ወራት በፊት መርካቶ አካባቢ ከሚገኝ አንድ ባንክ በተመሳሳይ የማጭበርበር ወንጀል 7ሺህ ብር እንዳወጣም በምርመራ የተረጋገጠ ሲሆን ምርመራውም ቀጥሏል።

በተለያዩ ቦታዎች ተመሳሳይ ወንጀል የተፈፀመባቸው ግለሰቦች ካሉ የካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመቅረብ ለፖሊስ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡ እያሳሰበ ህብረተሰቡ ገንዘብ ለማውጣት በተለይም በባንኮችና የገንዘብ ማውጫ ማሽኖች በሚገኙባቸው ቦታዎች ሲገኝ የሚረዱ ወይም የባንክ ሠራተኛ በመምሰል የሰዎችን የኤ.ቲ.ኤም ካርድ የሚስጥር ቁጥራቸውን በማየት የማጭበርበር ወንጀል በሚፈጽሙ ግለሰቦች ሠለባ እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግና አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙም በአቅራቢያ ለሚገኝ ፖሊስ መረጃ በመስጠት ተባባሪ መሆን እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

የትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአስተማሪዎች የ17 ወራት ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈል ወሰነየትግራይ ክልል አስተማሪዎች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ያልተከፈላቸው ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈላቸው  ጉዳያቸውን...
15/04/2025

የትግራይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአስተማሪዎች የ17 ወራት ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈል ወሰነ

የትግራይ ክልል አስተማሪዎች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ያልተከፈላቸው ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈላቸው ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት ወስደው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፤ ጉዳዩን ተከሳሾቹ የትግራይ ትምህርት ቢሮ፣ የፋይናንስ ቢሮና ጊዜያዊ አስተዳደሩ በሌሉበት ሲከታተል የቆየው የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ ሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ውሳኔ መስጠቱን ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል፡፡

ፍርድ ቤቱ በውሳኔውም ተከሳሾች የአስተማሪዎችን ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፍሉ በመወሰን የክስ መዝገቡ እንዲዘጋ ወስኗል። የፍርድ ሂደቱ 1ኛ ተከሳሽ የትግራይ ትምህርት ቢሮ፣ 2ኛ ተከሳሽ የትግራይ ፋይናንስ ቢሮ፣ 3ኛ ተከሳሽ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርና 4ኛ ተከሳሽ የገንዘብ ሚኒስቴር ባልተገኙበት የተደረገ ነው ተብሏል።

በ3 ሚሊዮን ብር ማሳጅ፣እኛ ጋር ልብስ አይወለቅም!
06/07/2024

በ3 ሚሊዮን ብር ማሳጅ፣
እኛ ጋር ልብስ አይወለቅም!

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

በኢትዮጵያዊ ወጣት የተሰራችው ፈጣኗን መኪና ተመልከቱ
03/07/2024

በኢትዮጵያዊ ወጣት የተሰራችው ፈጣኗን መኪና ተመልከቱ

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

አቡነ ማትያስ ከአሜሪካ ህክምና ላይ ሆነው የላኩት መልዕክት
22/09/2023

አቡነ ማትያስ ከአሜሪካ ህክምና ላይ ሆነው የላኩት መልዕክት

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

ተመልከቱ ዛሬ በአራት ኪሎ
21/09/2023

ተመልከቱ ዛሬ በአራት ኪሎ

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ! በ2016 ዓ.ም ቻናል 7 ኢትዮጵያ የተለያዩ አዳዲስ ፕሮግራሞችን እና የማህበረሰብ ችግር ፈቺ የሆኑ ልዩ ልዩ መረጃዎችን ከFastM...
11/09/2023

ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ!

በ2016 ዓ.ም ቻናል 7 ኢትዮጵያ የተለያዩ አዳዲስ ፕሮግራሞችን እና የማህበረሰብ ችግር ፈቺ የሆኑ ልዩ ልዩ መረጃዎችን ከFastMereja ጋር በጋራ አብረን እንደምንሰራ ለመግለፅ እንወዳለን።

ቻናል 7 ኢትዮጵያ
Channel 7 Ethiopia

ጎቤ እና ሺኖዬ ጭፈራ በአዲስ አበባ ቄሮ እና ቀሬ ተገናኝቷል! እንድትመለከቱት ጋበዝን!
07/09/2023

ጎቤ እና ሺኖዬ ጭፈራ በአዲስ አበባ ቄሮ እና ቀሬ ተገናኝቷል! እንድትመለከቱት ጋበዝን!

ቻናላችንን ስለጎበኙልን እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ የመዝናኛ እና የመረጃ ቪዲዮዎች እንዳያመልጦት ቻናላችንን Subscribe በማድረግ ቤተሰባችን ይሁኑ!! ለቻናል 7 ሃሳብ አስተያየት ካላችሁ 09517...

ለዉርስ ብሎ ወንድሙ ላይ የግድያ ሙከራ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራት መቀጣቱን የዳዉሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ ።ተከሳሽ  በተላ ባቴ ላይ የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንበት የቻለው በዳ...
10/08/2023

ለዉርስ ብሎ ወንድሙ ላይ የግድያ ሙከራ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራት መቀጣቱን የዳዉሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ ።

ተከሳሽ በተላ ባቴ ላይ የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንበት የቻለው በዳዉሮ ዞን በሎማ ባሶ ወረዳ ቤሮ ያማል ቀበሌ ልዩ ስሙ ፊናት ተብሎ በሚጠራበት መንደር ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም የግል ተበዳይ ወንድሙን በእርሻ መሬት ዉርስ በመካከላቸዉ በተፈጠረ አለመግባባት በፈፀመዉ የግድያ ሙከራ ወንጀል ክስ ጥፋተኝነቱ በመረጋገጡ ነዉ።

የወረዳ ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚያስረዳዉ ተከሳሹ እና የግል ተበዳይ ወላጆቻቸዉን በሞት በመለየታቸዉ የእርሻ መሬትና ሌሎች ንብረቶች ላይ ክፍፍል ለማድረግ በታላቅና በታናሹ ወንድም መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ታናሽ ወንድም የግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ድረስ በመሄድ አልጋ ላይ ተኝቶ እያለ በመሳደብ ከአልጋ ጎትቶ በማዉረድ ሲደበድበዉ የግል ተበዳይ ሕይወቱን ለማትረፍ ሲታገል ተከሳሽ በእንጨት መፍለጫ መፍለጫ/ፋስ/ ግንባሩ ላይ በብረቱ በኩል በመምታት የሞተ መስሎት ጥሎ ከአንድ ግለሰብ ቤት ይሸሸጋል፡፡

የተሸሸገበት ግለሰብ ሁኔታን ሲነግረው ለማጣራት ሲመጣ ጉዳት ደርሶበትና በህይወት መኖሩን በማረጋገጡ ለፖሊስ ጉዳዩን በማሳወቅ ተጎጂውን ወደህክም ተቋም ተወስዶ ህይወቱን ማትረፉን ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል፡፡

የሎማ ቦሳ ወረዳ ፖሊስ ተከሳሽን በቁጥጥር ስር አድርጎ ምርመራ አጣርቶ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በህክምና ማስረጃ በማደራጀት ለዳዉሮ ዞን ዐቃቤ ህግ መዝገቡን ልኳል።

የዞኑ ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ የቀረበለትን የምርመራ መዝገብ መርምሮ ተከሳሹን በፈፀመው ከባድ የሰው ግድያ ሙከራ ወንጀል ክስ መስርቶበት ፍርድ ቤት አቅርቦታል፡፡

የዳዉሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ ግለሰቡን ከሶ ያቀረበውን የክስ መዝገብ ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ክስ ተከሳሹ ክሱን እዲያስተባብል ዕድል ቢሰጠውም ክሱን ማስተባበል ባለመቻሉ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።

በዚሁ መሰረት የዳዉሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ባስቻለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ በተላ ባቴ በ12 አመት እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ መተላለፉን ከዞኑ ፖሊስ የተገኘዉ መረጃ ያመለክታል።

የፍርድ ውሳኔውን እየተጠባበቀ የነበረው ተጎጂ ከወንድሙ ግድያ ቢተርፍም በወንዝ ሙላት ተወስዶ ህይወቱ ማለፉን ታውቋል፡፡

ዘገባዉ፦ክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ነው!

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Channel 7 Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Channel 7 Ethiopia:

Share