Ethio Info Page 2

Ethio Info Page 2 Provides information as much as a fastest source.

ተወዳጇ ድምፃዊት ራሄል ጌቱ  ★ ዘመድ የለኝም ብለው ለሚያስቡ     ድንግል ማርያም እናት ትሁናችሁ።    መድኃኒዓለም አባት ይሁናችሁ።    አይዟችሁ ! ጠንክሩ ነው የምላችሁ።★ ብዙ ጊዜ ...
05/07/2026

ተወዳጇ ድምፃዊት ራሄል ጌቱ

★ ዘመድ የለኝም ብለው ለሚያስቡ
ድንግል ማርያም እናት ትሁናችሁ።
መድኃኒዓለም አባት ይሁናችሁ።
አይዟችሁ ! ጠንክሩ ነው የምላችሁ።

★ ብዙ ጊዜ ቤት ነው የምውለው።

★ በቅርቡ ለንደን ላይ ከጎሳዬ ተስፋዬ ጋር
ኮንሠርት አቀርባለሁ።

★ እኔ ዕድለኛ ነኝ። ከትላልቅ ድምፃዊያኖች ጋር
በመስራቴ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ።

★ ከተዋናይ ሄኖክ ወንድሙ ጋር አንድ ሰፈር ነን።
ሄኖክ አመስጋኝ ስለሆነ እንጂ የተለየ ምንም
ነገር አድርጌለት አይደለም።
ፊልሙን ስለጨረሰውም ደስ ብሎኛል።

★ ብዙም ደስ የሚል የልጅነት ጊዜ የለኝም።
እናትና አባቴ በልጅነቴ ነው የሞቱብኝ።
እዚህም እዚያም ክርትት እያልኩኝ ነው ያደኩት።

★ የበለጠ የማስታውሰው የብቸኝነት ጊዜዬን ነው።

★ ህይወትን ለማሸነፍ የታገልኩባቸው ጊዜያቶች
ናቸው ትዝ የሚሉኝ።

★ ህይወት ብዙ ነገር አስተምራኛለች።
ህይወት አብዝታ ያስተማረችኝ ፤ በማንም
አለመፍረድ ነው።

★ በልጅነቴ ት/ቤት መግባት አቅቶኝ ከፈረንሳይ
ሀገር የመጡ ፈረንጆች እየከፈሉ አስተምረውኛል።

★ እግዚአብሔር ቢያሳካልኝ ትልቁ ህልሜ ልጆች
የሚማሩበት ት/ቤት መክፈት ነው።
ህልሜን ከእግዚአብሔር ጋር አሳካዋለሁ።

★ በልጅነቴ ብቸኛ ሆኜ ነው ያደግሁት። ጠንካራ
አድርጎኛል። በፈተና ያለፈ ሰው ጠንካራ ይሆናል።
ደግ ሩህሩህ ይሆናል። ነገር ሁሉ ለበጎ ነው።

★ ማንም ሰው ጻድቅም ፤ ንፁህም አይደለም
ብዬ ነው የማስበው።

★ ሰዎች ገድገድ ሲሉ ማገዝ ያስፈልጋል።

★ በተቻለን መጠን ጥሩ ነገር ሰርተን ማለፍ ያስፈልጋል።

★ ህፃናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት በ10 ዓመቴ ገባሁ።
በቴአትር ቤቱ ብዙ ትዝታ አለብኝ።
ብዙ ነገር ተምሬበታለሁ።

★ ልጄ አሁን ትልቅ ልጅ ሆናለች። እግዚአብሔር
ይመስገን። ልጄ በረከቴ ነች።
የምጠነክረው እሷ ስላለች ነው።
የመኖሬ ምክንያት ነች።
ጨዋና አስተዋይ ልጅ ናት።

★ የምኮራበት ሀብቴ ልጄ ናት።

★ ዝምተኛነቴ ባህሪዬ ይመስለኛል። ዝምታ ለሁሉም
ነገር መልስ ነው።

★ ሁሉም ነገር ማብራሪያ ፤ ሁሉም ነገር መልስ
ያስፈልገዋል ብዬ አላምንም።

#ውዴ የተሰኘው ዘፈኔን ከቅድስት ይልማ ጋር
ስንሰራው ብዙ ለፍተንበታል። 3 ሚሊዮን ብርም
ወጪ ወጥቶበታል።

★ ከእድለወርቅ ጣሰው ጋር የረጅም ጊዜ ወዳጆች
ነን።ዕድል የሰራችበትን #ታሽጓል የሚለውን ፊልም
እኔ ነኝ ፕሮዲውስ ያደረኩት።

★ #የኛ ትልቁ መሠረታችን ነው። መልካም ጊዜ
አሳልፈናል።

★ ጂም እሰራ ነበር። አሁን ግን አቁሜዋለሁ።

★ ከኢንስታግራም ውጪ ሶሻል ሚዲያ አልጠቀምም።

★ ድሮ ብዙ የሚያዝናኑኝ ነገሮች ነበሩ። አሁን ግን
ፀጥታ ያለበት ቦታ ያዝናናኛል።

★ ሰፈራችን በሚገኘው አምባሳደር ሲኒማ ቤት
ፊልም በጣም እመለከት ነበር።

★ የቴዲ ታደሰ #ዝምታ ፣ የአስቴር አወቀ #ካቡ
እና የቴዲ አፍሮ #ኢትዮጵያ አልበሞችን
በጣም እወዳቸዋለሁ።

★በየቀኑ ፀሎት ሳላደርግና ሙዚቃ ሳላዳምጥ
መዋል አልችልም።

★ ከማስታወቂያ ባለሙያው ዘላለም ኩራባቸው
ጋር የተነሳሁትን ፎቶ ሶሻል ሚዲያ ላይ ለጥፈውት
ባልና ሚስት ናቸው አሉን።

★ ወዳጅነት ለእኔ ትልቅ ቦታ አለው። በጣም
የምወዳቸው ብዙ ወዳጆች አሉኝ።
በወዳጅ የተባረኩኝ ነኝ።

★ ሴትነት የሁሉም ነገር ምንጭ ነው።
ሴት ለሁሉም ነገር ቅመም ነች።

★ ላይ ከትልልቅ አርቲስቶች ጋር
መሳተፌ ያበረታኛል።

★ ከሰው የተለየ የማደርገው ነገር የለም።

★ዋና መዋኘት አልችልም ልጄ ግን ጎበዝ ነች።

★ የምንም ነገር ሱስ የለብኝም።

★ ከጊዜ በኋላ የተማርኩት ህይወት አጭር
እንደሆነች ነው። በተቻለን መጠን መልካም
ነገር አድርገን ማለፍ ያስፈልጋል።

★ ከራሴ ህይወት የተቀዳ ሙዚቃ የለም።
አልበሜ ላይ ያለው #ትረፊ ግን ከእኔ
ህይወት ጋር ይቀራረባል።

★ የሰው ልጅ በምርቃት ያድጋል ብዬ አስባለሁ።

★ #ናና የተሰኘውን አዲሱ ነጠላ ዜማ
ለወዳጅ አድናቂዎቼ አንድ ሙዚቃ እናድርስ
በሚል ነው ከአልበሜ በፊት የሰራሁት።

★ አልበም እየሰራሁ ነው። ከወዳጆቼ አድናቂዎቼ
ጋር በቅርቡ እንገናኛለን።

በመጨረሻም ሁሉንም ወዳጆቼን ማመስገን እፈልጋለሁ።
ብዙ ከሚያግዙኝ ሰዎች ሚኪ አትላንታ የሚኖር
ወንድማችንን ማመስገን እፈልጋለሁ።
ናና ስራ ላይ የተሳተፉትን በሙሉ አመሰግናለሁ።
ሰይፉ አንተንም እጅግ በጣም አመሰግናለሁ።
እግዚአብሔር ያክብርልኝ።

Rahel Getu እጅግ ምርጥ ቆይታ ነበር። ብስለትሽና
እርጋታሽ እጅግ አስገራሚ ነበር።
።ናና። አዲሱ ነጠላ ዜማሽ ሁለተኛው አልበምሽን
በጉጉት እንድንጠብቀው ያደርጋል።

አክባሪሽና አድናቂሽ
ዘሪሁን ተዝናኑ
ሞቅ ካለ የሚነበብ ፊርማ ጋር !!!

28/03/2026

!!!

16/03/2026



"የመጀመሪያዋ ኢራናዊ ያልሆነች የነዳጅ ጫኝ መርከብ 'ካራቺ' (Karachi)፣ የመከታተያ ምልክቷን (tracking signal) በማብራት የሆርሙዝ ሰርጥን በሰላም አቋርጣለች።"

ባለፉት ሳምንታት በሰርጡ ላይ ያለው የትራፊክ እንቅስቃሴ እጅግ ጸጥተኛ የነበረ በመሆኑ፣ የዚህች መርከብ ጉዞ ልዩ ትኩረት ስቧል። የአቡ ዳቢን ድፍድፍ ነዳጅ የጫነችው ይህች መርከብ ሰርጥኑን አቋርጣ አሁን በኦማን ባሕረ ሰላጤ ላይ በመጓዝ ላይ ትገኛለች።

ይህች መርከብ በምን ምክንያት እንዲያልፍ እንደተፈቀደላት በይፋ የተገለጸ ነገር የለም። ነገር ግን አንዳንድ ጭነቶች "በድብቅ ደህንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ" (safe passage) እየተሰጣቸው እንደሆነ ይጠቁማል።

ምንጭ፦

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Info Page 2 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share