17/11/2025
የኦፓል ማዕድን ዋሻ የተናደባቸው ማዕድን አውጭዎች አፅም ስርዓተ ቀበራቸው ተፈፀመ።
ሮሃ ቴቪ ኅዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ ባሳለፍነው ዓመት ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ኦፓል በማውጣት ላይ ሳሉ ዋሻ ተንዶባቸው ሊገኙ ያልቻሉት ስመንት ወጣቶች ከ 20 ወራት በኋላ በዋሻ ውስጥ አፅማቸው መገኘቱን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለትም ስርዓተ ቀበራቸው ተፈፅሟል።
በደላንታ ወረዳ በተለምዶ ቆቅ ውኃ እየተባለ በሚጠራ አካባቢ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት የኦፓል ማዕድን በቁፋሮ ለማውጣት ሲሞክሩ የነበሩ በርካታ ወጣቶች የቆፈሩት አለት ተንዶ ህወታቸውን ማትረፍ እና 8ቱ ደግሞ ሳይገኙ መቅረታቸው የሚታወስ ነው።
ከአመት በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት ህዳር 4 ቀን 2018 ዓ/ም በአካባቢው ኦፖል በማውጣት ላይ የነበሩ ወጣቶች አፅማቸው በዋሻ ውስጥ ማግኘታቸውን ቢቢሲን ዋቢ አድርገን መዘጋባችን የሚታወስ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ህዳር 4 ቀን ከማለዳው 12:00 ጀምሮ የአፀም ማውጣት ስራው ተጀምሮ የ8 ወጣቶች አፅም ወጥቶ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በወገልጤና ርዕሰ አድባራት ሐመረኖህ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን የፍትሃተ ፀሎት ተደርጎ ስርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል ተብሏል።
ላለፉት 13 አመታት የኦፓል ማዕድን ቁፋሮ ሲደረግበት የቆየው ዋሻ ከ750 ሜትር በላይ ርዝመት ያለው ሲሆን በደረሰበት የመናድ አደጋ በውስጡ የቀሩ ሰዎችን ለማውጣት በወቅቱ ከ80 ሜትር በላይ ቁፋሮ መደረጉ ይታወሳል። ከ20 ወራት በኋላ አጽማቸው ሲገኝም ሰራተኞቹ ቁፋሮ እያደረጉ በነበሩበት የዋሻ ክፍል ተዘግቶባቸው በህይወት ለቀናት እንደቆዩና እሚደርስላቸው በማጣታቸው አሟሟታቸውም በረሀብ ምክንያት እንደሆነም ምንጮች ተገኝተዋል። አፅማቸውም በአንድ አንድ ሜትር ርቀት እንደተገዘ ሆኖ ተዘጋጅተው እንደተገኙም ተገልጿል። መጨረሻ የሞተው ብቻ ገለል ብሎ በዛው ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል። በሥነ ሥርዓት በአንድ አንድ ሜትር ርቀት አስቀምጧቸዋል። በረሃብ ነው የሞቱት" ይላሉ። የማኅበሩ ሊቀ መንበር አቶ ተስፋዬ "እነሱ ያሉበት እና የሚቆፍሩበት ቦታ ውስጥ አልተናደም፤ ከእነሱ ወደታች ያለው ክፍል ነው የተናደው እና የተዘጋው መውጫ አጥተው ነው፤ አቅጣጫው በጣም ከባድ ስለሆነ ነው መውጣት ይችሉ ነበር። የተገኙበት ሁኔታ ልጆቹ ውሃ እየጠጡ እንደቆዩ የሚያስረዳ ነው። ዋሻው ውስጥ ውሃ ስላለ ውሃ ለማግኘት የቆፈሩትን ሁሉ አግኝተነዋል" ሲሉ ተናግረዋል።።