Corki Tube

Corki Tube All activities which are necessary for our audience.

ቅኔ የሆነ ህዝብደጀንነት በተግባር
04/09/2022

ቅኔ የሆነ ህዝብ
ደጀንነት በተግባር

  ኮሜዲያን እሸቱ መለሰን አመስግኑልኝ። በውነቱ የሥራህው ሥራ ድንቅና አርአያ የሚሆን ነው። እሸቱ በቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ስም ለተቋቋመ ገዳም የእርሻ ትራክተር አበርክቷል። ይህ ገዳም  አዊ...
04/09/2022

ኮሜዲያን እሸቱ መለሰን አመስግኑልኝ። በውነቱ የሥራህው ሥራ ድንቅና አርአያ የሚሆን ነው። እሸቱ በቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ስም ለተቋቋመ ገዳም የእርሻ ትራክተር አበርክቷል። ይህ ገዳም አዊ ዞን ከዳንግላ ከተማ ምዕራብ አቅጣጫ 18 ኪ.ሜ ጉዞ በኋላ ወንደፋይ ቀበሌ ውስጥ ይገኛል። ወለተ ጴጥሮስ አንድነት ገዳም በዐፄ ሱስንዮስ ዘመነ መንግስት በጻዲቋ ወለተ ጴጥሮስ የተመሰረተች ጥንታዊትና ታሪካዊት ገዳም ናት፡፡ እሸቱ ላደረግህው መልካም ሥራ እናመሰግናለን🙏

የአቶ ውብሸት አያሌው ስርአተ ቀብር በሸዋሮቢት ከተማ ደብረ ኃይል ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተክርስቲያን ተፈጸመ ፡፡አቶ ውብሸት አያሌው ከአባታቸው ከአቶ አያሌው ባዩ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ...
03/09/2022

የአቶ ውብሸት አያሌው ስርአተ ቀብር በሸዋሮቢት ከተማ ደብረ ኃይል ቅዱስ ቴዎድሮስ ቤተክርስቲያን ተፈጸመ ፡፡

አቶ ውብሸት አያሌው ከአባታቸው ከአቶ አያሌው ባዩ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙነሽ ይመር ተወልደው፡፡ ትዳር በመመስረትም የእንድ ሴትና የአንድ ወንድ አባት መሆናቸውና በቀወት ወረዳና በሸዋሮቢት ከተማ በተለያዪ ተቋማት በባለሙያነትና በስራ ኃላፊነት አገልግለው ነበር በ37 ዓመታቸው ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት አካባቢ በመኖሪያ ቤታቸው ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በጥይት ተመተው ህይወታቸው ማለፉን በህይወት ታሪካቸው ለማወቅ ተችሏል፡

03/09/2022

በመጀመሪያው ወረራ በትሪሊየን የሚገመት ዝርፊያና በመቶ ሺህዎች የሚቆጠር እልቂት የፈጸሙ ወራሪዎች የለመዱትን ነውር ሊፈጽሙ ሲመጡ በጀግኖች ክንድ ላይ ኃይሉን ያስቀመጠ አምላክ መዓቱን አወረደባቸው።

28/08/2022

ከደባርቅ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተላለፈ ወቅታዊ መልዕክት።

የደባርቅ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ የፀጥታ ስጋት አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል።

1ኛ= በከተማችን የሚገኘው የተፈናቃይ መጠለያ ነዋሪ ከ12:00 በሗላ ወደ ውስጥም ሆነ ወደ ከተማ መግት ከልክሏል።

2ኛ= የከተማችን ባጃጅ ተሽከርካሪ ከምሽቱ 1:00 በሗላ መንቀሳቀስ አይችልም ይህን ሲያደርግ የተገኘ ባለባጃጅ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል።

3ኛ=መላው የከተማችን ማህበረሰብ በአደረጃጀቶች አካባቢውን ሌትና ቀን ከሰርጎገብ በንቃት እንዲጠብቅ።

4ኛ=ፀጉረ ልውጥ ሲያጋጥም በፍጥንት ለህግ አካል ጥቆማ በመስጠት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረግ።

5ኛ=የከተማችን ባለሆቴሎች እና ባለአልጋ ቤቶች ማንነቱ ያልታወቀ አንጋች በድርጅታችሁ ሲጋጥማችሁ ለህግ አካላት ጥቆማ እንድትሰጡ።

6ኛ=በከተማችን ያላችሁ የቤት አከራይዎች ያከራያችሁትን ግለሰብ ማንነትቱን ለይታችሁ እንድታከራዩ የተከራየውንም በመረጃ ፎርም ሞልታችሁ ለፀጥታ ጽ/ቤት እንድታሳውቁ።
እነዚን የውሳኔ ሀሳቦች በማጥስ ማንኛውም አካል ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ በጥብቅ መልዕክቱን ያስተላልፋል።
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮምንኬሽን።
ነሀሴ22/2014ዓ/ም
#ደባርቅ።

Address

AA
Addis Ababa
1000

Telephone

+251904567368

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Corki Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Corki Tube:

Share

Category