
28/12/2024
ከድንግል እወለዳለሁ እንዳለ የተፈጥሮን ልማድ ሰብሮ ተወለደ:: ስለ ሰው ልጆች መከራ ከተቀበለ ቡሃላ እሞታለሁ እንዳለ ሞተ:: እነሳለሁ እንዳለ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለም በሐይል ተነሳ:: ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁ እንዳለ የወጉት አይኖች እያዩት ወደ ሰማይ አረገ::ከተናገረው ያልተፈፀመ የለምና እመለሳለሁ ያለ ጌታ ደግሞ ይመለሳል:: ይህንን ቀን ስናስብ በዚህ እውነት ላይ መቆምና መፅናት ይሁንልን::በተስፋ ደስ ይበላችሁ በመከራም ታገሱ:: ፀጋ ይብዛ:: ቡርካን ናችሁ::
ፓስተር ተከስተ ጌትነት