16/09/2025
                                            የሞተ ቋንቋ ምን ማለት ነው ?! 
ዶክተር በድሉ ዋቅጅራን ለቀቅ አድርጉ :: በቋንቋ  ጥናት እና ምርምር አንድ ቋንቋ የሞተ ቋንቋ ነው የሚባለው ምን ሲሆን ነው የሚለውን ጠይቁ እና እወቁ ! ይህ የባህርዳር ዩንቨርስቲ የአማርኛ ትምህርት መማሪያ ነው ::
ግእዝን በተመለከተ እንዲህ ይላል 
ይህን ቋንቋ በአሁኑ ጊዜ በአፍ መፍቻነት የሚናገረው ወገን የለም ስለዚህም ግዕዝ የሞተ ቋንቋ ነው:: የግልጋሎት ክልሉም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ተወስኗል፡፡
ስለዚህ የሞተ ቋንቋ ማለት በአፍ መፍቻነት የሚጠቀምበት የለም ለማለት ነውንጅ ቋንቋውን ማጥላላት አይደለም ::
ዶክተሩም ያሉት በዩንቨርስቲ ደረጃ ይሰጥ ለህፃናት ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ መሰጠቱ አስፈላጊ አይደለም ነው ያሉት ::
እኛም ያልነው ይኼንኑ ነው !