
31/01/2025
ጥር 23-2017 - የእስራኤል ምርኮኞች ቤተሰቦች ኔታንያሁ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ማበላሸት የለባቸውም ሲሉ ተናገሩ
በጋዛ የታገቱ ቤተሰብ ያላቸው እስራኤላውያን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የተኩስ አቁም ስምምነቱን እንዳያበላሹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡በ+972 መጽሔት ላይ የእስራኤል መንግስትን የሚተቸዉ ዩዳ ኮሄን የተባለዉ ግለሰብ የእስራኤል ወታደር የሆነዉ ልጁ ናምሩድ በጥቅምት 7 የተማረከ ሲሆን እስራኤል በጋዛ ፍልስጤማውያን ላይ የጦር ወንጀል እየፈፀመች ብቻ አይደለም "በእስራኤል ወታደሮች ላይ ወንጀል እየፈፀመች ነው"ሲል ተደምጧል፡፡
"ሁሉም ታጋቾች እንዲመለሱ እፈልጋለሁ" ሲልም አክሏል፡፡ከፍልስጤማውያን ጋር ይበልጥ የተረጋጋ እና ዘላቂ መፍትሄ ላይ መድረስ ተገቢ ነው። ሌላውን ጎን ማየት አለብን። አንዱ ወገን ሲያድግ ሌላኛው ሲሰቃይ ሊሆን አይችልም ። በሌላ በኩል ሐሙስ ዕለት በጋዛ ደቡባዊ ካን ዮኒስ የእስራኤል ምርኮኞችን በርካታ የፍልስጤም ታጠቂ ቡድኖች አሳልፈዉ ለሃማስ መስጠታቸዉ በአካባቢው ባሉ የተቃውሞ ቡድኖች መካከል ያለውን ትብብር እና ግንኙነት ቀጣይነት ያለው መሆኑን የጦርነት ተቆጣጣሪዎች ተናግረዋል ።
የጦርነት ጥናት ኢንስቲትዩት እና Critical Threats ፕሮጀክት (CTP)፣ መቀመጫቸውን አሜሪካ ያደረጉ ሁለት የመከላከያ ትንታኔ ተቋማት፣ የሃማስ ተዋጊዎች፣ የፍልስጤም ተቃዋሚ ኮሚቴ እና የፍልስጤም ሙጃሂዲን ንቅናቄ ሃይሎችን አብረዋቸው እንደነበሩ ያሳያል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ከእስራኤል ጋር ከ 15 ወራት ጦርነት በኋላ "በተዳከመ ተቋማዊ የማስተባበር ዘዴ ምክንያት ተግዳሮቶች" ሊያጋጥሟቸው በሚችሉበት በዚህ ወቅት በታጠቁት ቡድኖች መካከል ያለው አንድነት አስገራሚ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የእስራኤል ማአሪቭ ጋዜጣ በበኩሉ በጋዛ ጦርነት ላይ የእስራኤልን የህዝብ አስተያየት የሚገመግም የዳሰሳ ጥናት አውጥቷል።በአላዛር ምርምር በተካሄደው የሕዝብ አስተያየት መሠረት 57 በመቶ የሚሆኑ እስራኤላውያን የሀገሪቱ የጦርነት ዓላማዎች "ሙሉ በሙሉ አልተሳካም" ሲሉ 32 በመቶ የሚሆኑት "ምንም አልተሳካም" ብለው ያምናሉ፡፡ምላሽ ከሰጡት ሰዎች መካከል አራት በመቶው ብቻ የእስራኤል የጦርነት ኢላማዉን በጋዛ "ሙሉ በሙሉ አሳክቷል" ብለዋል።
በስምኦን ደረጄ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…
Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/