Ethio Fam

Ethio Fam Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio Fam, Social Media Agency, Addis Ababa.

ማዕከላዊ  ኢትዮጵያ ክልል
22/08/2023

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል

11/08/2023
11/08/2023
09/08/2023

«በትግራይ የምግብ እርዳታ ከተቋረጠ ወዲህ 1411 ሰዎች በረሃብ ሞተዋል» የትግራይ አስተዳደር

የትግራይ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን ኮምሽነር ዶክተር ገብረሕይወት ገብረእግዚአብሔር "እስካሁን 1411 ሰዎች በረሃብ ምክንያት ሕይወታቸው እንዳለፈ፣ እነዚህ ሕይወታቸው ያለፈ ደግሞ ሽማግሌዎች፣ ሴቶች፣ ህፃናት መሆናቸው ፥ የምግብ እርዳታው ከቆመ በኃላ ከዞኖች፣ ወረዳዎች ሪፖርት ተደርጎልናል።ይህ የሟቾች ቁጥር ምዕራብ ትግራይ ዞን፣ የደቡብ ትግራይ ዞን 6 ወረዳዎች፣ የማእከላዊ ዞን 22 ወረዳዎች እንዲሁም የመቐለ 7 ክፍለከተሞች እንደማይጨምር የትግራይ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ኮምሽነር ዶክተር ገብረሕይወት ገብረእግዚአብሔር ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

ለተቸገሩ ዜጎች የሚቀርብ የምግብ እርዳታ ተዘርፏል በሚል ምክንያት ከአምስት ወራት በፊት በትግራይ ጨምሮ በአጠቃለይ በሀገሪቱ ለሚገኙ እርዳታ ፈላጊዎች ያቀርበው የነበረ የምግብ አቅርቦት ማቋረጡ የገለፀው የዓለም የምግብ ድርጅት ቀስበቀስ የምግብ እርዳታ ማቅረብ መጀመሩ በትላንትናው ዕለት የተዘገበ ቢሆንም እንደ የትግራይ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን ገለፃ ግን የተጀመረው፥ ለረዥም ግዜ በትግራይ ተቋርጦ የነበረ የሴፍትኔት ፕሮግራም እንጂ የአስቸኳይ ሕይወት አድን ሰብአዊ እርዳታ አለመሆኑ ተገልጿል።ኮምሽነሩ ዶክተር ገብረሕይወት፥ ዓለምአቀፍ ለጋሾች እስካሁን በትግራይ ላሉ እርዳታ ፈላጊዎች ያቀረቡት እገዛ የለም ይላሉ።

"ይህ የተጀመረው 'food for work' ምግብ ለስራ የሴፍትኔት ፕሮግራም ነው። እንደሚታወቀው ከጦርነቱ በፊትም የነበረ፣ ከ700 ሺህ እስከ 1 ሚልዮን የሚጠጋ የትግራይ ህዝብ ይሳተፍበት የነበረ ፕሮግራም ነው። ለተቸገረ የሕብረተሰብ ክፍል ወይ ለተፈናቃይ የሚሆን የተጀመረ የምግብ እርዳታ ግን የለም። ሴፍቲኔት፥ ፕሮግራም እንጂ አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት አይደለም" የሚሉት ኮምሽነሩ "በመቐለ እና ሌሎች ወረዳዎች መጋዝን ያለ እርዳታ ግን ለህዝቡ እንዲሰራጭ የተሰጠ ፍቃድ የለም" ሲሉ አክለዋል።በዚህ ጉዳይ ዙርያ በዓለም የምግብ ድርጅት (WFP) የመቐለ ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት በአካል እንዲሁም በአዲስአበባ ከሚገኙ የድርጅቱ ተወካዮች በስልክና ኢሜይል ምላሽ ለማግኘት የተደረገው ጥረት ለግዜው አልተሳካም።

09/08/2023

ወደ ባህር ዳር እና ጎንደር ከተሞች በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ‼️

አየር መንገዱ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ በረራ ነገ ነሐሴ 4 ቀን 2015 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን አስታውቋል።

መንገደኞችም በአቅራቢያቸው በሚገኙ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ቢሮዎች ወይም ወደጥሪ ማዕከል (6787/+251116179900) በመደወል መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል።

ETHIO FAM

09/08/2023

በመዲናዋ በሞተር ብስክሌቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተራዘመ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች ላይ ጥሎት የነበረውን እግድ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን አስታወቀ፡፡

ቢሮው ሐምሌ 27/2015 ባወጣው መመሪያ እስከ ነሐሴ 3/2015 ዓ.ም የሞተር ብስክሌቶችን በከተማዋ ማሽከርከር እንደማይቻል መግለጹን አስታውሶ እገዳው ዛሬ ማብቂያ ጊዜ መሆኑን ተከትሎ ነው መመሪያውን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙን የገለጸው፡፡፡

ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን የማያካትት ሲሆን የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶችም ሆኑ አሽከርካሪዎች እግዱ እሰኪነሳ በትዕግስት እንዲጠብቁ ማሳሰቡን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ethio fam

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Fam posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share