
25/05/2023
በቅሬታ አፈታትና አወሳስን ላይ ስልጠና ተሰጠ።
#ዋዩ ወረዳ ኮምዩኒኬሽን፤ግንቦት 17/2015
****
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋዩ ወረዳ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ለአመራርና ቡድን መሪዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቅሬታና አቤቱታ አቀራረብ ፣ ምርመራ፣ አወሳሰን እና የተጠያቂነት ስርዓት ለመወሰን የወጣ
በደንብ ቁጥር 143/2015 ላይ ስልጠና ተሰቷል።
ስልጠናዉን የሰጡት የወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሴናተር ሳሙኤል ሲሆኑ አጠቃላይ ድንጋጌዎችን፣ የቅሬታና አቤቱታ አቀራርብ ስነ-ስርዓት ላይ ትኩረት በማድረግ ስልጠናዉን ሰተዋል።
በተጨማሪም በአገልግሎት አሰጣጥ እና በባለሙያ ስምሪት ላይ ትኩረት በማድረግ የሪፎርም ዉይይት ተካሂዷል።በዉይይቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ከ90 ቀን ተግባራት ዉስጥ አንዱ በመሆኑ በተለይ እሮብና አርብ ኮሚቴዉ የሚያደርገዉን ምልከታ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።በምልከታዉ የተገኙ በጥንካሬና በክፍተት ተጠምሮ ሪፖርት እንደሚቀርብም የ/ቤት ሀላፊዉ አቶ ሙሉቀን ጥላሁን ገልፀዋል።እንዲሁም የስራ ቦታን ምቹና ማራኪ ለማድረግ ሁሉም ተቋማት የደንብ ልብስ በማዘጋጀት ቀልጣፋና ፍትሀዊ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ አቶ
ሙሉቀን ገልፀዋል።
ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የግብዓት እና የሰዉ ሀይል ችግር፣ የሰራተኛ ጥቅማ ጥቅም የመሳሰሉት ጥያቄዎች ከቤቱ በስፋት ተነስተዋል።
በተነሱት ጥያቄዎች ላይ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉቀን ከግብዓት ጋር በተያያዘ ከፋይናንስ ፅ/ቤት ጋር በመነጋገር ለቀጣይ በጀት ዓመት ለማሟላት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።