Tigist Ngussie ትዕግስት ንጉሴ

Tigist Ngussie ትዕግስት ንጉሴ የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ መረጃወችን ለማግኘት ይህንን ድህረ-ገፅ Like ያድርጉ

እውነት ምንጊዜም አሸናፊ ናት

31/07/2022
ሌላ ትኩሳት...የነዳጅ ትራንስፖርት ባለንብረቶች ማኅበር የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ የ10 ቀናት የጊዜ ገደብ አስቀመጠ።የነዳጅ ትራንስፖርት ባለንብረቶች ማኅበር በ10 ቀናት ውስጥ መንግስት ...
31/03/2022

ሌላ ትኩሳት...
የነዳጅ ትራንስፖርት ባለንብረቶች ማኅበር የሥራ ማቆም አድማ ለማድረግ የ10 ቀናት የጊዜ ገደብ አስቀመጠ።

የነዳጅ ትራንስፖርት ባለንብረቶች ማኅበር በ10 ቀናት ውስጥ መንግስት መፍትሄ የማይጠው ከሆነ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

የማህበሩ አባላት ዛሬ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ባደረጉት ጠቅላላ ስብሰባ፣ በተደጋጋሚ መንግስት ቸልተኛ በመሆኑ የነዳጅ አመላላሽ ቦቴ ቁጥር ከ3 ሺህ 500 በ20 እጅ ቀንሷል ብለዋል።

ጅቡቲ ደርሶ መልስ 2 ሺህ 5000 ብር እየከሰሩ መሆኑንና ይኸም የሆነውም የብር ዋጋ በመውረዱና መለዋወጫ በመወደዱ መሆኑንም ተናግረዋል።

በመሆኑም መንግስት በአስር ቀናት ውስጥ መፍትሄ የማይሰጣቸው ከሆነ የሥራ አድማ እንደሚጠሩ ማስታወቃቸውን ሪፖርተር ዘግቧል::

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፓርቲዎች 50 ሚሊዮን ብር ሊያከፋፍል ነው፡፡ቦርዱ ይህን ያለው ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በመከረበት ውይይቱ ነው፡፡የብሔራዊ ምር...
29/03/2022

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፓርቲዎች 50 ሚሊዮን ብር ሊያከፋፍል ነው፡፡

ቦርዱ ይህን ያለው ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በመከረበት ውይይቱ ነው፡፡
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ በአዲሱ የምርጫና የፖለቲካ ፖርቲዎች አዋጅ መንግሥት ለፖለቲካ ፓርቲዎች በቋሚነት የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ መጠቀሱን አንስተዋል።
በዚህ መሠረት ምርጫ ቦርዱ ለዚህ ዓመት ከመንግሥት 230 ሚሊዮን ብር መጠየቁን ያነሱት ሰብሳቢዋ፤ አገሪቷ ካለችበት ወቅታዊ ችግር ምክንያት ገንዘቡ እንደማይሰጥ እንደተገለጸላቸው ተናግረዋል።
ሆኖም ምርጫ ቦርዱ ባለፈው የምርጫ ወቅት ከወረቀት ህትመት የተረፈውን 50 ሚሊዮን ብር ለፓርቲዎች ለማከፋፈል ከመንግሥት ፈቃድ ማግኘቱን ገልጸዋል።
ይህም ገንዘብ 30 በመቶ ለአገራዊ ፖርቲዎች፣ 20 በመቶው ለክልላዊ ፓርቲዎች እንዲሁም በፓርቲዎች የሴትና የአካል ጉዳተኞች አመራሮች ብዛት ታይቶ የሚከፋፍል ነው ተብሏል፡፡

በሳዑዲ አረቢያ በእስር ቤት እና በማዕከላት ውሰጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎች ከነገ መጋቢት 21 ቀን 2014 ጀምሮ ወደ አገር ቤት መመለስ እንደሚጀምሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ...
29/03/2022

በሳዑዲ አረቢያ በእስር ቤት እና በማዕከላት ውሰጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎች ከነገ መጋቢት 21 ቀን 2014 ጀምሮ ወደ አገር ቤት መመለስ እንደሚጀምሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
16 የመንግስት ተቋማትን በአባልነት የያዘው ብሄራዊ ኮሚቴ ዜጎችን መመለስ ለመጀመር የተደረጉ የመጨረሻ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በትላንትናው ዕለት የገመገመ ሲሆን፤ ከነገ ረቡዕ ጀምሮ ዜጎችን መመለሱ እንደሚጀምር ይፋ አድርጎል። በውይይቱ እንደተገለፀው የበረራ፣ የማቆያ ማዕከላት ዝግጅት፣ የመገልገያ ቁሳቁስ፣ የምግብ እና መጠጥ አቅርቦት፣ የአልባሳት፣ የትራንስፖርት እንዲሁም የህክምና አገልግሎትን ለተመላሾች በበቂ ሁኔታ ለማቅረብ በመቻል ረገድ የተደረጉ ዝግጅቶች በግብረ ሃይሉ አባላት ውይይት ተደርጎባቸዋል። የኮሚቴው ሰብሳቢ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንዳሉት፤ የመመለሱ ተግባር ተመላሽ ዜጎችን ካሉበት አምጥቶ እስከ መኖሪያ ቀያቸው የማድረስ ሥራን የሚሸፍን ነው። ይህንኑ ከመነሻው እስከ መድረሻው በተሳለጠ ቅብብሎሽ ለመፈፀም ተቋማት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አምባሳደር ብርቱካን አሳስበዋል። ተመላሾች አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ ክልሎች ከየማዕከላቱ ቶሎ በማንሳት ወደ መኖሪያቸው መውሰድ ያለባቸው በመሆኑ ያደረጉት ዝግጅትም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ክልሎቹ ያልተጠናቀቁ የዝግጅት ሥራዎችን በቀሪ ቀናት እንዲያጠናቅቁ አሳስበዋል።

“መንግስት ከታጠቁ ሃይሎች ጋር ድርድር መጀመር አለበት ”የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ(ኦፌኮ) 2 መደበኛ ጉባዔ ከመጋቢት 17-18 ማካሄዱን ተከትሎ በሀገሪቱና...
28/03/2022

“መንግስት ከታጠቁ ሃይሎች ጋር ድርድር መጀመር አለበት ”የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ(ኦፌኮ) 2 መደበኛ ጉባዔ ከመጋቢት 17-18 ማካሄዱን ተከትሎ በሀገሪቱና በህዝቡ ያጋጠሙ ፈተናዎች ላይ በመወያየት የፓርቲውን ቀጣይ የትግል መዕራፍ እና እስትራቲጂ አቅጣጫውን አስቀምጧል
ከ 4 ዓመታተ በፊት የመጣው ለውጥ ሀገራችን ወደአዲስ የሰላም እና ዲሞክራሲ ያሸጋገራል የሚል ተስፋ ቢኖርም የለውጡ ሂደት ተቀልብሶ ወደ ዲሞክራሲ የነበርው ሽግግር እድል ባክኖ የእርስ በርስ ጦርነትና የሀገር መፍረስ አደጋ ተጋርጦብናል ሲል የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ(ኦፌኮ) የመደበኛው ግባዔ መጠናቀቁን ተከትሎ ባውጣው በመግለጫው አስታውቋል ።
በቅርቡም የፌደራሉ እና የትግራይ ክልላዊ መንግስት ጦርነትን ለማቆም ያሳለፉት ውሳኔ በፍጥነት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲለውጥ ጥሪውን አስተላልፏል ኦፌኮ።
መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋርም የገባበትን ጦርነት በሰላማዊ መንግድ ለመፍታት ቁርጠኝነቱን ሊያሳይ እንደሚገባም ፓርቲው አሳስቧል።
የተሳካ ብሔራዊ ምክከር ለማካሄድ መፍትሔ ያስፈልጋቸዋል ያልቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አስቀምጧል።
በሁሉም የአገሪት አካባቢዎች ግጭት እንዲቆም፤ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች በተለይም የኦፌኮ እና ኦነግ አባለት ከእስር እንዲፈቱ፤መንግስት ከታጠቁ ሃይሎች ጋር ድርድር እንዲጀምር እና ብሔራዊ ምክክሩ ላይ እንድሳትፉ የሚሉት ጉዳዮዎች ኦፌኮ በአቋም መግልጫው አጽኖት የሰጠባቸው ጉዳዮች ናቸው።

ሩሲያ ለውጭ ገበያ የምታቀርበውን የነዳጅ ዘይት ምርቷን በሩብል ወይም በቢት ኮይን ልትሸጥ እንደምትችል ይፋ አድርጋለች፡፡በሩሲያ ፓርላማ የኢነርጅ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ፓቬል ዛቫልኒ እንደገለ...
25/03/2022

ሩሲያ ለውጭ ገበያ የምታቀርበውን የነዳጅ ዘይት ምርቷን በሩብል ወይም በቢት ኮይን ልትሸጥ እንደምትችል ይፋ አድርጋለች፡፡

በሩሲያ ፓርላማ የኢነርጅ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ፓቬል ዛቫልኒ እንደገለጹት÷የአሁን ላይ በአገሪቱ በተጣለው ማዕቀብ ምክንያት በሞስኮ የተፈጥሮ ጋዝን በዶላር ወይም በዩሮ መሸጥ አስቸጋሪ ሆኗል፡፡

በዚህ ሳቢያም ሩሲያ ወደ ውጭ የምትልከውን የነዳጅ እና የጋዝ ምርት የአገር ውስጥ መገበያያ በሆነው ሩብል ወይም በቢት ኮይን ልትሸጥ እንደምትችል ነው የገለጹት፡፡

በአንጻሩ ለሩሲያ ወዳጅ ለሆኑ አገራትን ማለትም÷ለቱርክ እና ለቻይና የተሻለ አማራጭ የክፍያ መንገዶች እንደሚመቻቹ ም ሊቀመንበሩ ገልጸዋል፡፡

ፓቬል ዛቫልኒ የሩሲያው ሩብል እና የቻይናው ዩዋን እንደመገበያያ ለመጠቀም ቀደም ብለው ለቻይና ሀሳብ ማቅረባቸውን በመጠቆም÷ ከቱርክ ጋርም በሊይሬ እና በሩብል ግብይይት ይደረጋል ብለዋል፡፡

ከወዳጅ አገራት ጋር በምናደርገው ግብይት ቢት ኮይንንም እንደ አማራጭ መጠቀም እንችላለን ሲሉ ሊቀመነበሩ መግለጻቸውን ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን “ወዳጅ ያልሆኑ” አገራት የሞስኮን የነዳጅ ዘይት ምርት በሩብል እንዲገዙ ማሳወቃቸው ይታወሳል።

ጦርነቱን ተከትሎ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ህብረት አባላ ሀገራት የተጣሉ ማዕቀቦች በሩሲያ ሩብል ላይ ጫና በመፍጠር የኑሮ ውድነቱ ከፍ እንዲል ማድረጉን መረጃዎች ያመላክታሉ።

እራሱን የትግራይ መንግስት እያለ የሚጠራው አካል ጦርነት ማቆሙን አስታወቀ፡፡ ትላንት የኢትዮጺያ መንግስስት ጦርነቱ ማቆሙኑ ማወጁ የሚታወስ ነው፡፡
25/03/2022

እራሱን የትግራይ መንግስት እያለ የሚጠራው አካል ጦርነት ማቆሙን አስታወቀ፡፡
ትላንት የኢትዮጺያ መንግስስት ጦርነቱ ማቆሙኑ ማወጁ የሚታወስ ነው፡፡

ተመስገን!!! 🙏🙏🙏🌧🌧🌧🌧🌧የቦረና ምድር በዝናብ እርሷል።
24/03/2022

ተመስገን!!! 🙏🙏🙏
🌧🌧🌧🌧🌧
የቦረና ምድር በዝናብ እርሷል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሓት ጋር ያለው ጦርነት እንዲቆም ስለመወሰኑ የሰጠው ሙሉ መግለጫ፡፡የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ሰለመወሰኑ ...
24/03/2022

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የኢትዮጵያ መንግስት ከህወሓት ጋር ያለው ጦርነት እንዲቆም ስለመወሰኑ የሰጠው ሙሉ መግለጫ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም ሰለመወሰኑ የወጣ መግለጫ
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ የተሳለጠ እንዲሆን የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። በዚህም መሰረት የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ እርዳታ የአየር በረራዎች ቁጥር እንዲጨምር እንዲሁም ለእርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች የነዳጅ እና የጥሬ ገንዘብ የሚቀርብበትን ስርዓት የተሳለጠ እንዲሆን ተደርጓል። ከዚህ ጋር በተያያዘም የአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ የአለም ጤና ድርጅት እና የአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ እርዳታዎችን ማደረስ እንዲችሉ የአየር በረራ ተመቻችቷል።ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ መንግስት በአብአላ-መቀሌ የየብስ ትራንስፖርት መስመር በኩል የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት መድረስ እንዲችል አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል።
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ነዋሪዎች የሰብዓዊ እርዳታን ፍለጋ ወደአጎራባች ክልሎች እየተጓዙ መሆኑ እየተስተዋለ ነው። በዚህም በትግራይ አጎራባች ክልሎች የሚኖሩ ዜጎች ከትግራይ ክልል የሚመጡ የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊ ዜጎችን ተቀብሎ በማስተናገድ እያሳዩ ያለው በጎ ተግባር በህዝቦች መካከል ያለውን የወንድማማችነት እና የአንድነት መንፈስ የሚያሳይ ነው። መንግስት እነዚህ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታው ከቀያቸው ሳፈናቀሉ ባሉበት እንዲርሳቸው ቢደረግ እንግልታቸውን እንድሚቀንስ በጽኑ ያምናል። በመሆኑም መንግስት በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎቹን ችግር በአፋጣኝ የመፍታት ኃላፊነቱ ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን በመረዳት የአስቸኳይ የሰብዓዊ አቅርቦቶች ወደትግራይ ክልል በበቂ ሁኔታ መድረስ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማሳካት የተቻለውን ሁሉ ጥረቶች ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል።
በዚህም መሠረት በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ እና የዜጎችን እንግልት ለመቀነስ ይቻል ዘንድ ከተለመደው የተለዩ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መንግስት ይህ ውሳኔ ከወጣበት ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት የማቆም ውሳኔ አስተላልፏል። በዚህ አጋጣሚ መንግስት ዓለም ዓቀፉ የለጋሾች ማህበረሰብ እያቀረበ ያለውን ድጋፍ እና እርዳታ በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ጥሪ ያቀረባል።
የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቱ በተሳለጠ ሁኔታ መድረስ እንዲችል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣል። ይህ የመንግስት ጥረት እና ቁርጠኝነት የሰብዓዊ ሁኔታውን በማሻሻል ረገድ የሚኖረው ስኬት የሚረጋገጠው በሌላኛው ወገን የሚገኘው አካል በተመሳሳይ ለዚህ አላማ በሚኖረው ቁርጠኝነት ልክ መሆኑን መንግስት ያምናል። ይህ በመንግስት በኩል የተላለፈው ውሳኔ አላማው የአስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ በነጻነት ተጓጉዞ ለእርዳታ ፈላጊ ዜጎች ለመድረስ እንዲችል ነው። በመሆኑም ለሰብኣዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዲችል መንግስት በትግራይ ክልል የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም የጥቃት እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ እና ን በጉልበት ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎችእንዲወጡ ይጠይቃል።
የኢትዮጵያ መንግስት ይህ ለሰብኣዊነት ግጭት የማቆም ውሳኔ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ ሁኔታ በእጅጉ ሊያሻሽል እንደሚችል ብሎም በቀጣይ ያለተጨማሪ ደም መፋሰስ ለግጭቱ መፍትሔ ሊያመጣ እንደሚችል ተስፋ ያደርጋል።

የፌደራል መንግስት ከህወሓት ጋር ያለው ጦርነት እንዲቆም ውሳኔ አሳለፈ።መንግስት በትግራይ ክልል የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም የጥቃት እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ እና በጉልበት ከያዟቸው የአጎራባች ...
24/03/2022

የፌደራል መንግስት ከህወሓት ጋር ያለው ጦርነት እንዲቆም ውሳኔ አሳለፈ።

መንግስት በትግራይ ክልል የሚገኙ አማጺያን ከማንኛውም የጥቃት እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ እና በጉልበት ከያዟቸው የአጎራባች ክልል አካባቢዎችእንዲወጡ ጠይቋል።

ይሄው ነው፡፡

የኢትዮጺያ አየር መንገድ ለ 8 ዓመት ያገለገሉትን የቦርድ አባላት በአዲስ ተክቷል።ከአዲሶቹ የቦርድ አባላት ውስጥም አቶ ተመስገን ጥሩ ነህ: ሌ/ጀ ይልማ መርዳሳ እና  አቶ ተክለ ወልድ አጥና...
24/03/2022

የኢትዮጺያ አየር መንገድ ለ 8 ዓመት ያገለገሉትን የቦርድ አባላት በአዲስ ተክቷል።
ከአዲሶቹ የቦርድ አባላት ውስጥም አቶ ተመስገን ጥሩ ነህ: ሌ/ጀ ይልማ መርዳሳ እና አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ ይገኙበታል።

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁአቶ ተወልደ ከኃላፊነታቸው በይፋዊ መንገድ የለቀቁት ከጤናቸው ሁኔታ ጋር በተገናኘ እ...
23/03/2022



የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ከኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ
አቶ ተወልደ ከኃላፊነታቸው በይፋዊ መንገድ የለቀቁት ከጤናቸው ሁኔታ ጋር በተገናኘ እንደሆነ ታማኝ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
አቶ ተወልደ፣ ከስድስት ወራት ላለፈ ጊዜም ህክምናቸውን በአሜሪካ እየተከታተሉ እንደሆነም ይታወቃል፡፡
አቶ ተወልደ አየር መንገዱን በዋና ሥራ አስፈፃሚነት ለ11 አመታት የመሩ ሲሆን፤ ለ37 አመታትም አየር መንገዱን አገልግለዋል፡፡(የኢትዮጵያ ንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ)

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tigist Ngussie ትዕግስት ንጉሴ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tigist Ngussie ትዕግስት ንጉሴ:

Share