Ethio Journal

Ethio Journal This page is greater to deliver news from �Ethiopia and other parts of the world.

04/02/2024

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Abayne Fute, ጁሀር መሀመድ

04/02/2024
 ዛሬ ላይ የምንተክለዉ ችግኝ ብቻ አይደለም የነገይቱን የበለፀገችና የለመለመች ኢትዮጵያን እንጂ !!
25/07/2023



ዛሬ ላይ የምንተክለዉ ችግኝ ብቻ አይደለም የነገይቱን የበለፀገችና የለመለመች ኢትዮጵያን እንጂ !!

ኢትዮጵያን ወክለው በ7ኛው የሁዋዌ ዓለም አቅፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር የተሳተፉት ተማሪዎች የሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀቁ።
29/05/2023

ኢትዮጵያን ወክለው በ7ኛው የሁዋዌ ዓለም አቅፍ የአይሲቲ ፍጻሜ ውድድር የተሳተፉት ተማሪዎች የሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀቁ።

የቱርኩ ፕሬዝዳንት በድጋሜ በመመረጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ ** የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶኻን በድጋሜ በመመረጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ...
29/05/2023

የቱርኩ ፕሬዝዳንት በድጋሜ በመመረጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የደስታ መልዕክት አስተላለፉ
**
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶኻን በድጋሜ በመመረጣቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላፈዋል።
ፕሬዝዳንቱ በድጋሜ መመረጣቸውን ተከትሎ በኢትዮጵያ እና ቱርክ መካከል ያለው የቆየ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

  : Halala kela resorts on another leve መንገዶች ሁሉ ወደ ሃላላ ኬላ ያመራሉ:: ኢትዮጵያዊያን ይህን ውብ ስፍራ ከነታሪኩ ማየት ይኖርባቸዋል!
28/05/2023

: Halala kela resorts on another leve መንገዶች ሁሉ ወደ ሃላላ ኬላ ያመራሉ:: ኢትዮጵያዊያን ይህን ውብ ስፍራ ከነታሪኩ ማየት ይኖርባቸዋል!

በመስቀል ሰሞን ጎልታ የምትታየን ነገር ግን ሁሌም አብራን ያለችው 'የመስቀል ወፍ'፨፨፨፨፨፨፨የመስቀል ወፍ ለወራት ጠፍታ ቆይታ አዲስ ዓመት ሲገባ በተለይ ደግሞ መስከረም ሲጋመስ እንደምትከሰ...
27/09/2022

በመስቀል ሰሞን ጎልታ የምትታየን ነገር ግን ሁሌም አብራን ያለችው 'የመስቀል ወፍ'
፨፨፨፨፨፨፨
የመስቀል ወፍ ለወራት ጠፍታ ቆይታ አዲስ ዓመት ሲገባ በተለይ ደግሞ መስከረም ሲጋመስ እንደምትከሰት በብዙዎች ዘንድ ይታመናል።

በአባባልም አንድ ሰው ለረጅም ጊዜ ጠፍቶ ቆይቶ ድንገት ሲከሰት ' ምነው የመስቀል ወፍ ሆንክ' ይባላል። ይህም ለረጅም ጊዜ ሳይታዩ ወይም ጠፍቶ ቆይቶ መታየትን ለማመልከት ማህበረሰቡ የሚጠቀምበት አባባል ነው።

አእዋፋትን በቅርበት የሚያጠኑት አቶ ይልማ ደለለኝ ግን "እነዚህ የመስቀል ወፍ ተብለው የሚታወቁት አእዋፋት እንደሚባሉት ለረጅም ጊዜ ተሰውረው ቆይተው በመስቀል ሰሞን የሚከሰቱ ሳይሆኑ ዘወትር አብረውን የሚኖሩ ናቸው" ይላሉ።

እንደባለሙያው ከሆነ በኢትዮጵያ በመስቀል ወፍ ስም የምትታወቀው አንድ አይነት ዝርያ ያላት ወፍ ብቻ ሳይሆን ቁጥራቸው ከአራት በላይ የሆኑ የተለያዩ ዝርያ ያለቸው አእዋፋት እንደሆኑ ይናገራሉ።

ለዚህም እንደምሳሌ የሚጠቅሱት ቁራ በሚል የሚጠሩ አእዋፋት ቢኖሩም በውስጣቸው የተለያዩ ዝርያዎች እንዳሉት ሁሉ የመስቀል ወፍ ውስጥም የተለያዩ የወፍ አይነቶች መኖራቸውን ነው።

ከእነዚህ የመስቀል ወፎች መካከልም አዘውትረን የምናያቸው በቅርብ የምናውቃቸው ትንንሽዬዎቹና ድንቢጥ ተብለው የሚታወቁት አእዋፋትም በመስቀል ወፍነት ከሚጠሩት ውስጥ ይካተታሉ።

እንደየቋንቋውና እንደየአካባቢው እነዚህ ወፎች የየራሳቸው ስያሜና መጠሪያ ሊኖራቸው እንደሚችል የሚጠቅሱት አቶ ይልማ የመስቀል ወፍ የሚለው ግን በርካታ አይነት ወፎች በውስጡ አካትተዋል ይላሉ።

በእንግሊዝኛው እነዚህ አዕዋፋት ኢንዲጎ በርድስ፣ ዋይዳ፣ ቢሾፕ ወይም ዊዶ በርድ ተብለው እንደሚታወቁ በእነዚህ ውስጥም የተለያዩ ዝርያዎች መኖራቸውን ያስረዳሉ።

ወፎቹ የሚታዩበት ጊዜ

እነዚህ የመስቀል ወፍ ተብለው የሚጠሩት አእዋፋት በስፋት ታይተው በበርካቶች ዓይን ውስጥ የሚገቡት የክረምቱ ወራት አብቅቶ የበጋው ወቅት በሚጀምርበት ጊዜ ነው።

አእዋፋቱ በአብዛኛው ዘር በል በመሆናቸው በዚህ ወቅት ደግሞ የሚደርሱ ሰብሎች በስፋት የሚገኙበትና ወፎቹም የሚራቡበት አመቺ ወቅት በመሆኑ በስፋት እንደሚታዩ አቶ ይልማ ይናገራሉ።

እነዚህ አእዋፋት ባሕሪያቸው ከአንድ አካባቢ ወደሌላ አካባቢ ወቅቶችንና የአየር ሁኔታዎችን እየተከተሉ የሚሰደዱ በመሆናቸው በሌሎች ሃገራት ውስጥም ይገኛሉ።

አቶ ይልማ እንደሚሉት የተለያዩ አእዋፋት በተለያዩ ወቅቶች በተለይ ከሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ወደ አፍሪካ የሚመጡ ሲሆን በሌላ ጊዜ ደግሞ ወደዚያው የሚሄዱም አሉ።

ወደኢትዮጵያ ወቅቶችን ጠብቀው የተለያዩ ወፎች ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከስካንዴኔቪያን ሃገራት፣ ከምስራቅ አውሮፓ ሃገራት እንዲሁም ከሩሲያ የሚመጡ እንዳሉና እነዚህም በስደተኛ ወፍነት በባለሙያዎች እንደሚታወቁ ይገልጻሉ።

የመስቀል ወፍ ተብለው የሚታወቁት አብዛኞቹ ግን በኢትዮጵያ ውስጥና በዙሪያዋ ባሉ ሃገራት ውስጥም እንደሚገኙ ይነገራል። ስለዚህ አእዋፋቱ ከኢትዮጵያ ባሻገር በኬንያ፣ በኡጋንዳና በታንዛንያ ውስጥ እንደሚገኙ ይጠቅሳሉ።

አብረውን ያሉ ግን እንግዶች

አቶ ይልማ እንደሚሉት በልምድ እንደምንለው የመስቀል ወፍ ለረጅም ጊዜ ጠፍተው ቆይተው በመስቀል ወቅት የሚከሰቱ እንዳልሆኑና በዙሪያችን አብረውን የሚኖሩ ናቸው።

አእዋፋቱ አዲስ የሚሆኑብን አብረውን በዙሪያችን በሚቆዩበት ጊዜ የሚኖራቸው ገጽታ በመስከረም ወር ላይ በተፈጥሯዊ ሂደት ቀለማቸው ተለውጦ አይነ ግቡ ስለሚሆኑ የዚያ ወቅት አዲስ ክስተት እንደሆኑ ስለሚታሰብ ነው።

"ለዚህም የአዕዋፋቱን ተፈጥሮ መረዳት ያስፈልጋል" የሚሉት አቶ ይልማ እነዚህ ወፎች ላይ ይህ ተፈጥሯዊ ለውጥ የሚታየው በዋናነት በመስከረም ወር ላይ የሚራቡበት ጊዜ በመሆኑ ነው። ይህ ደግሞ ከመስቀል በዓል ጋር ተቀራራቢ በመሆኑ የተለየ ገጽታን ተላብሰው እንዲታዩ ያደርጋቸዋል።

የተፈጥሮ ሂደት

በመስከረም ወር ላይ እንስት አእዋፋቱ እንቁላል ለመጣል የሚዘጋጁበት በመሆኑ ተባዕቱ ለእሱና ለተጣማሪው እንዲሁም ለሚፈለፈሉት አእዋፋት የሚያስፈልገውን ምግብና መጠለያን በሚያገኝበት ቦታ ላይ አንድ የተወሰነ አካባቢን ከልሎ ይይዛል።

መራቢያ ጊዜ በመሆኑ ወንዱ ይህንን በሚያደርግበት ወቅት የላባው መጠን ይረዝማል ቀለሙም ይቀየራል። ቀለሙ ደማቅና ውብ ስለሚሆን የሰዎችን አይን በመሳብ እንደ አዲስ ወፍ ሊታይ ይችላል ይላሉ አቶ ይልማ።

ይህ ቀለምም ከሩቅ የሚታይ እንደሚሆን የሚናገሩት ባለሙያው በተለይ ፀሐይ በሚያገኘው ጊዜ በማንጸባረቅ ትኩረት የመሳብ አቅም አለው።

በተጨማሪም ለውጡ የሚከሰተው በመራቢያ ጊዜ በመሆኑ እንስት ወፎችን ለመሳብና ለማማለል ከመጥቀሙ በተጨማሪ በአንጸባራቂ ውበቱ በቀላሉ ስለሚታይ፣ እንዲሁም በዚህ ላይ ዝማሬን ስለሚጨምር ሌሎች አእዋፋት የእርሱን አካባቢ እንዲርቁ ያስችለዋል።

እንግዲህ ይህ የአእዋፋቱ ሥነ አካላዊ ለውጥ ነው በሌለው ጊዜ በአካባቢያችን ይኖሩ የነበሩትን እነዚህን አእዋፋት ለረጅም ጊዜ ጠፍተው በመስቀል ወቅት ብቅ ያሉ እንዲመስሉ ያደረጋቸው ይላሉ አእዋፋቱን በቅርበት የሚያጠኑት አቶ ይልማ ደለለኝ።

ባለሙያው እንደሚሉት "በአካባቢያችን ያሉትን አእዋፋት በቅርበት የመከታተል ልምድ ስለሌለንና ክረምቱ አልፎ መስከረም አጋማሽ ላይ አእዋፋቱ ላባቸው በቀለማት አሸብርቆ በቀላሉ አይናችን ውስጥ ሲገቡ በዙሪያችን የነበሩት ወፎች ሳይሆኑ ጊዜ እየጠበቁ ብቅ የሚሉ ይመስሉናል።"

ቀለማቸውና ዝማሬያቸው ከአዲስ ዓመትና ከመስከረም የፀሐይ ወቅት ጋር ተዳምሮ ከሚፈጠረው መልካም ስሜት ጋር የሁሉንም ቀልብ ስለሚስቡ ሁሉም ይመለከታቸዋል ሁሉም አዲስ ወፍ የመስቀል ወቅትን ጠብቆ እንደመጣ ይታመናል።

የመስቀል ወፍ ብለን የምንጠራቸው አእዋፋት ከሌሎች ለየት የሚሉት ተባዕቶቹ በጣም ደማቅ ቀለም ሲኖራቸው፣ ሴቷ ግን ቡኒ ወይም ወደ ግራጫ የሚያደላ ቀለም ነው ያላት፤ በመራቢያ ወቅት ወንዱ ከበርካታ እንስት አእዋፋት ጋር የመሆን ባሕሪ እንዳለውም አቶ ይልማ ይጠቅሳሉ።

ስለዚህ የአእዋፋት አጥኚ የሆኑት አቶ ይልማ ደለለኝ እንደሚሉት የመስቀል ወፎች ለረጅም ጊዜ ሳይታዩ ቆይተው መስከረም ወር ላይ የሚከሰቱ ዓመታዊ እንግዶች ሳይሆኑ አብረውን ቆይተው በተፈጥሮ ሂደት የላባቸው ቀለም የሚቀየር ቤተኛ አእዋፋት ናቸው ማለት ነው።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።

"መንግስት የሀገሪቱን ሉአላዊነት ለማስከበር በአሸባሪው ሕወሓት ላይ የትኛውንም እርምጃ ይወስዳል" - አቶ ደመቀ መኮንን መንግስት የሀገሪቱን ሉአላዊነት ለማስከበር በሕወሓት የሽብር ቡድን ላይ...
01/09/2022

"መንግስት የሀገሪቱን ሉአላዊነት ለማስከበር በአሸባሪው ሕወሓት ላይ የትኛውንም እርምጃ ይወስዳል" - አቶ ደመቀ መኮንን

መንግስት የሀገሪቱን ሉአላዊነት ለማስከበር በሕወሓት የሽብር ቡድን ላይ የትኛውንም እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

ከሚወሰደው እርምጃ ጎን ለጎን አሁንም የመንግስት የሰላም በሮች ክፍት መሆናቸውን ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

አቶ ደመቀ ወቅታዊ የሀገሪቱን ሁኔታ አስመልክተው መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ አምሳደሮች፣ የሚሲዮን መሪወች እና የአለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

መንግስት ለሰላማዊ ውይይት ብዙ ርቀት መጓዙን የተናገሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ሕወሓት ይህንን እድል እንዳመከነው አብራርተዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በቀጣይ በኢትዮጵያ ጉዳይ ገለልተኛ አቋሙን እንዲያንፀባርቅም ጠይቀዋል።

የሽብር ቡድኑ በተለያዩ አካባቢዎች ወረራ እየፈጸመ መሆኑን ያነሱት አቶ ደመቀ መንግስት ህገ መንግስታዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት ሁሉንም እርምጃወች እንደሚወስድ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል ሲል ከኢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሐረር የፍቅር እና የሰላም መገኛ ነች። የዚህ ዓመት  #አረንጓዴዐሻራ መርሐ ግብር በሚጠናቀቅበት ምሽት፣ ተፈጥሮ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄያችንን ውጤት በገለጠችበት ሥፍራ ዐሻራችንን አሳርፈናል...
13/08/2022

ሐረር የፍቅር እና የሰላም መገኛ ነች። የዚህ ዓመት #አረንጓዴዐሻራ መርሐ ግብር በሚጠናቀቅበት ምሽት፣ ተፈጥሮ የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄያችንን ውጤት በገለጠችበት ሥፍራ ዐሻራችንን አሳርፈናል።

Harar bakka jaalalaafi nagaati. Galgala itti sagantaan xumuramutti, bakka itti uumamni bu'aa sochii Ashaaraa Magariisaa keenya mul'ftetti ashaaraa keenya keewwanneerra.

The historic Harar hosted a ceremony during which Prime Minister Abiy Ahmed and First Lady Zinash Tayachew were present together with high level government officials.

በቡናና ቅመማ ቅመም ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎች እና የምርምር ተቋማት  እውቅና ተሰጠ********************በደቡብ  ክልል በ2014 በጀት አመት በቡናና...
05/07/2022

በቡናና ቅመማ ቅመም ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖች፣ ልዩ ወረዳዎች እና የምርምር ተቋማት እውቅና ተሰጠ
********************

በደቡብ ክልል በ2014 በጀት አመት በቡናና ቅመማ ቅመም ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች እና የምርምር ተቋማት እውቅና ተሰጠ።

በእውቅና አሰጣጥ ኘሮግራሙ የተገኙት የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ እርስቱ ይርዳ ጠላቶቻችንን ከብልጸግና ጉዟችን ለማሰናከል የቱንም ያህል ቢፈትኑንም ተስፋቸውን እያመከንን ኢትዮጵያን ወደከፍታ እንወስዳለን ብለዋል።

ሰላም ወዳድ፣ ለም አፈርና ታታሪ ህዝብ ያለን በመሆኑ እነዚህን አቅሞች አስተባብረን ወደከፍታ የምናደርገውን ጉዞ አጠናክረን እንቀጥላለንም ነው ያሉት።

የቡናና የቅመማ ቅመሙ ዘርፍ አለም አቀፍ ተቀባይነት እያገኘ በመምጣቱ ስራውን አስፋፍቶ በመስራት በቀጣይ የህዝቡን ህይወት ለመቀየር መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በቁጥቁጥ ከማምረት በአጭር ጊዜ ሚሊዮኖችን ተደራሽ ያደረገ ስራ በየደረጃው መስራት እንደሚገባ ያሳሰቡት ርእሰ መስተዳደሩ ጥራትና ብዛት ያለው ዘር አቅርቦት ላይ በትኩረት እንዲሰራም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የቡናና የቅመማ ቅመም ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማገዝ እንደሚገባ እንዲሁም ከምርምር ተቋማት ጋር ተቀናጂቶ መስራት እንደሚገባ አመልክተው ዩኒየኖችና ህብረት ስራ ማህበራት ቴክኖሎጂዎችን ወደ አርሶ አደሩ እንዲያቀርቡ ማበረታታት ይገባል ብለዋል።

ከዘርፉ አልተጠቀምንም የሚል ቁጭት በመፍጠር መላው አመራርና ባለሙያ በየደረጃው በመንቀሳቀስ የበለጠ የቡናና የቅመማ ቅመም ምርት ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚቀርብበትን መንገድ በፍጥነት ማመቻቸት እንደሚገባም አሳስበዋል።

በምክትል ርእሰ መስተዳደር ማእረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር የቡናና የቅመማ ቅመም ዘርፍ ለኢኮኖሚው ዘርፍ ከፍተኛ ትርጉም ያለው በመሆኑ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ዘርፉ ይበልጥ እያደገ በመምጣት አርሶ አደሮችና አገራችን ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አመራሩ ስራውን ይበልጥ ትኩረት ሰጥቶ እንዲመራው አሳስበው መንግስት ዘርፉ እንዲጎለብት ድጋፉን እንደሚያጠናክር አረጋግጠዋል።

ሽልማቱ የተበረከተላቸው አካላትም በእውቅናው በመበረታታት ጥራትና ብዛት ያለው ምርት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች እንዲመረት ሁሉንም የልማት አቅሞች አስተባብረው እንዲረባረቡም አቅጣጫ ተቀምጧል። መረጃው የጋሞ ዞን የመንግስት ኮምንኬሽን ነው።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸው የመኖሪያ አፓርትመንቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተመረቁ ነውአዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014  የፌዴራል ቤቶች ኮር...
12/06/2022

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸው የመኖሪያ አፓርትመንቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተመረቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2014
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባው የመኖሪያ አፓርትመንቶች የምረቃ ስነ - ስርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ፕሮጀክቱ አሉሙኒየም ፎርም ወርክ ቴክኖሎጂ” የተሰኘ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ያዋለ ሲሆን÷ ኢትዮጵያውያን ሙያተኞች ቴክኖሎጂውን በማላመድ ግንባታውን በፍጥነት ያከናወኑበት መሆኑም ተገልጿል፡፡

ቴክኖሎጂው የግንባታ ጥራትና ፍጥነትን የሚያቀላጥፍ ሲሆን፥ ኮርፖሬሽኑ ይህን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በማዋል በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ አስር ወለል ያላቸውን 16 ህንጻዎች ያየዘ የመኖሪያ መንደር መገንባት ችሏል።

የመኖሪያ መንደሩ ዘመናዊ የደህንነት ጥብቃ ስርዓት የተገጠመለት፣ ከ800 በላይ መኪና ማቆም የሚያስችል ስፍራ፣ የጋራ መጠቀሚያ አዳራሽ፣ የተለያዩ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ ካፌና ሬስቶራንት፣ መናፈሻ፣ አምፊ ቴአትር፣ የልጆች መጫወቻና መዋኛ ገንዳን ያካተተ መሆኑም ተገልጿል።

የመኖሪያ መንደሩ ግንባታ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥሯልም ተብሏል፡፡

የገርጂ መኖሪያ መንደር ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂን ማስተዋወቅ ያስቻለ፣ ብቃት ያላቸው የመንግስት ፕሮጀክት መሪዎች የታዩበት፣ አሰሪ፣ የግንባታ አማካሪ እና ተቋራጮች ለአንድ ዓላማ በትብብር በመስራት ትልቅ ነገር እውን ማድረግ እንደሚችሉ ያሳየ ነው ተብሎለታል፡፡

በተመሳሳይ ኮርፖሬሽኑ በቀበና ሳይት ያስገነባቸውን ሁለት ባለ አስር ወለል ህንጻዎች ግንባታ ያጠናቀቀ ሲሆን÷ ፕሮጀክቱ ለንግድና መኖሪያ ቤት የሚውሉ ቤቶች ያሉት በ1 ሺህ 167 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ዘመናዊ ህንጻ ግንባታ ነው ተብሏል።

የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽህፈት ቤት ያስገነባው የረገ ኤያት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ*********የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽህፈት ቤት  በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ...
11/06/2022

የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽህፈት ቤት ያስገነባው የረገ ኤያት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ
*********

የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽህፈት ቤት በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ያስገነባው የረገ ኤያት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምረቃ ስነስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

የትምህርት ቤቱ መገንባት የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ከማስቻሉም በተጨማሪ ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ሆነው እንዲማሩ እድል ይፈጥራል።

በትምህርት ዘርፉ የሚስተዋለውን መጠነ ማቋረጥን ለማስቀረት የጎላ ሚና እንዳለው ከዞኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
#ኢፕድ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Journal posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Journal:

Share