
15/09/2025
‘’ኧረ በገብርኤል! ኧረ በገብርኤል!
ምን አይነት ስህተት ነው የሠራነው?
ምን አይነት ታክቲክ ነው የተጠቀምነው?
አትሌቶቻችን ከአሰልጣኞቻቸው ጋር ምንድን ነው የተነጋገሩት? ’’
ፍቅር ይልቃል ከጃፓን ቶኪዮ የ3000 መሰናክል ፍጻሜን በቀጥታ በዘገበበት ወቅት የተናገረው!
እሱም አስቀድሞ እንደተናገረው የኢትዮጵያን አትሌቲክስ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ሁኖ መዘገብ ፈተና ነው፡፡
የሀገር ፍቅር ስሜት፣ ንዴት፣ እልህ፣ ቁጭት……ደምሴ ዳምጤን ነበር ያስታወሰኝ፡፡
የደምሴ አንዲያ እያነቀው ቢዘግብም ወርቁን አይቶ ፈንድቋል፡፡ የፍቅር ስሜት የብዙዎቻችን ስሜት፣ የእሱ እንቆቅልሽ የሁላችንም እንቆቅልሽ ይመስለኛል፡፡
ኢትዮጵያ በዓለም ፊት የሚያቆማትን ብቸኛ የሚባል መድረክ ቀስ በቀስ እያስረከበች ነው፡፡ ታሪክ ሁኖ ሊቀር ነው እንዴ ጎበዝ?
ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሕይወት ባለባት ሀገር?
እኔ ተንታኝ ስላልሆንሁ ዝም ልበል፡፡
እውነት ምን ሁነን ነው?
* * *
መስከረም ጌታቸው