Mehal Media

Mehal Media All about truth

https://youtu.be/3KX7woIRSHY
24/01/2023

https://youtu.be/3KX7woIRSHY

“Mehal Meda” is an Amharic phrase, which, in essence, means a “central venue”. This channel is dedicated to provide a platform where various perspectives are...

አፍሪካ ህብረት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ይጀምራል ተብሎ ጥበቃል።ለዚሁ የሰላም ንግግር የህወሓት ልዑክ ስፍራው መድረሱ ተነግሯል። ከዚህ ...
24/10/2022

አፍሪካ ህብረት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ይጀምራል ተብሎ ጥበቃል።

ለዚሁ የሰላም ንግግር የህወሓት ልዑክ ስፍራው መድረሱ ተነግሯል። ከዚህ በፊት ህወሓት የሰላም ድርድር የሚያደርጉት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳይ እንደሆኑ መግለፁ የሚዘነጋ አይደለም።

በኢትዮጵያ መንግስት በኩል፤ የሰላም ንግግሩ ተካፋዮችን ወደ ደቡብ አፍሪካ ዛሬ ማቅናታቸውን አመልክቷል።

ከወራት በፊት የፌዴራል መንግሥት የሰላም ተደራዳሪ ቡድን አባላቱ አቶ ደመቀ መኮንን (ሰብሳቢ)፣ ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ (አባል)፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ (አባል) ፣ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር (አባል)፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን (አባል) ሌ/ል ጀኔራል ብርሀኑ በቀለ (አባል)፣ ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር (አባል) መሆናቸውን መግለፁ ይታወሳል።

አፍሪካ ህብረት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ይጀምራል ተብሎ ጥበቃል።ለዚሁ የሰላም ንግግር የህወሓት ልዑክ ስፍራው መድረሱ ተነግሯል። ከዚህ ...
24/10/2022

አፍሪካ ህብረት የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ንግግር ዛሬ በደቡብ አፍሪካ ይጀምራል ተብሎ ጥበቃል።

ለዚሁ የሰላም ንግግር የህወሓት ልዑክ ስፍራው መድረሱ ተነግሯል። ከዚህ በፊት ህወሓት የሰላም ድርድር የሚያደርጉት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳይ እንደሆኑ መግለፁ የሚዘነጋ አይደለም።

በኢትዮጵያ መንግስት በኩል፤ የሰላም ንግግሩ ተካፋዮችን ወደ ደቡብ አፍሪካ ዛሬ ማቅናታቸውን አመልክቷል።

ከወራት በፊት የፌዴራል መንግሥት የሰላም ተደራዳሪ ቡድን አባላቱ አቶ ደመቀ መኮንን (ሰብሳቢ)፣ ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ (አባል)፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ (አባል) ፣ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር (አባል)፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን (አባል) ሌ/ል ጀኔራል ብርሀኑ በቀለ (አባል)፣ ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር (አባል) መሆናቸውን መግለፁ ይታወሳል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ " የፈተና ስርቆት እና ኩረጃ ከፍተኛ የደንብ ጥሰትና  #ወንጀል " መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን እንዲህ ያለው ድርጊት በህግ እንደሚያስጠይቅ ያስገነዝባል...
18/10/2022

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ " የፈተና ስርቆት እና ኩረጃ ከፍተኛ የደንብ ጥሰትና #ወንጀል " መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን እንዲህ ያለው ድርጊት በህግ እንደሚያስጠይቅ ያስገነዝባል።

የማህበረሰብ የጋራ ሀብት በሆነው ፈተና ላይ ሚፈጸም ማንኛውንም አይነት ወንጀል በጋራ መከላከል ይገባል ይላል አገልግሎቱ።

የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተና ከማክሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከ አርብ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በጣና ፎረም የተናገሩት ፦" ያለፈው ታሪካችን ሊያስተምረን ይገባል፤ ስለችግሮቻችን ማንንም አንወቅስም መውቀስ ካለብን ራሳችንን ነው ብለዋል...
18/10/2022

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በጣና ፎረም የተናገሩት ፦

" ያለፈው ታሪካችን ሊያስተምረን ይገባል፤ ስለችግሮቻችን ማንንም አንወቅስም መውቀስ ካለብን ራሳችንን ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ በአክሱም ዘመን የነበረንን ስልጣኔ ተመልከቱ፤ በግብጽ የነበረንን የቀደመ ስልጣኔ አስቡ፤ ችግራችን የነበረንን ጥንታዊ ስልጣኔ እና ታሪክ በተገቢው መንገድ ለልጆቻችን አለማስተማራችን ነበር። አሁን ግን ለልጆቻችን ከማስተማራችን በፊት ስለራሳችን የተሳሳተውን እይታችን ማረም ይገባናል።

አዎ ! ላለፉት 40 እና 50 ዓመታት #አሜሪካ ለሀገሬ ኢትዮጵያ በመቶ ሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር አውጥታ ምግብ እረድታ ይሆናል፤ ነገር ግን አሜሪካ የረዳችን ከችግራችን በምንወጣበት መንገድ አልነበረም።

ግብርናችን እንዲሻሻል፣ ቴክኖሎጂ እንድንጠቀም እና የተሻሻለ አሰራርን እንድንተገብር ተደጋጋሚ ድጋፍ የጠየቅናት አሜሪካ በፖሊሲ ሰበብ ፈቃደኛ አልነበረችም።

ኢትዮጵያዊቷ ንግስት ሳባ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ተሻግራ እንደ ሀገር ንጉስ ሰለሞንን ስትጎበኝ አሜሪካ እንደ አህጉርም እንደ ሀገርም አትታወቅም ነበር።

ከኋላ እየመጡ ለሚቀድሙን ሁሉ እርግጥ ነው ኅላፊነቱን መውሰድ ያለብን ራሳችን ነን።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ አገልግሎት መጀመሩን እየሰጠ በሚገኘው መግለጫ በይፋ አሳውቋል።መግለጫውን በዙም መከታተል የሚቻል ሲሆን ጥያቄ / አስተያየት ያላችሁ ጥያቄያችሁን / አስተያየታ...
06/10/2022

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ አገልግሎት መጀመሩን እየሰጠ በሚገኘው መግለጫ በይፋ አሳውቋል።

መግለጫውን በዙም መከታተል የሚቻል ሲሆን ጥያቄ / አስተያየት ያላችሁ ጥያቄያችሁን / አስተያየታችሁን በዙም #በቀጥታ ማቅረብ ትችላላችሁ።

29/09/2022
29/09/2022

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እያካሄደ የሚገኘውን የሙከራ ኔትዎርክ አገልግሎቱን እያስፋፋ ይገኛል።

ዛሬ በተላከልን መልዕክት ፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራውን በአወዳይ እና ጎንደር ከተሞች አስጀምሯል።

ይህ የደንበኞች ሙከራ የሳፋሪኮምን ኔትወርክ እየሞከሩ ያሉትን ከተሞች ቁጥር 10 አድርሶታል። ከዚህ በፊት በድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሐረማያ፣ ባሕር ዳር፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሞጆ እና ደብረ ብርሃን ላይ ሙከራ መጀመሩ ይታወቃል።

የአወዳይ እና ጎንደር ደንበኞች የሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ፣ የአየር ሰዓት እና የስልክ ቀፎዎች ግዢ እንዲሁም የደንበኞች ድጋፍ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

በአወዳይ አንድ በቀበሌ ዐ1 የሚገኝ የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈበት መደብር እና በጎንደር አራት (በፒያሳ፣ አራዳ፣ አዘዞ እና ኮሌጅ) የሳፋሪኮም መለያ የተለጠፈባቸው መደብሮች ደንበኞችን ለማገልገል ክፍት ናቸው ሲል በላከልን መልዕክት አሳውቋል።

 የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም መታሰቢያ እና ዓመታዊ ኮንፈረንስ መስከረም 22 ቀን 2015 ዓ/ም ሊካሄድ ነው።የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ፋውንዴሽን በላከልን መልዕክት ፤ መስከረም ...
29/09/2022



የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም መታሰቢያ እና ዓመታዊ ኮንፈረንስ መስከረም 22 ቀን 2015 ዓ/ም ሊካሄድ ነው።

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ፋውንዴሽን በላከልን መልዕክት ፤ መስከረም 22 ቀን 205፣ ከ7፡30 አንስቶ ለግማሽ ቀን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋካልቲ " እሸቱ ጮሌ አዳራሽ " በርካታ እንግዶች በተገኙበት ታላቅ ጉባዔ ይካሄዳል ብሏል።

" የተመራማሪ፣ መምህር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ደራሲ፣ የሰላማዊ ትግል አቀንቃኝ እና የፍትሕ ተቆርቋሪ በሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም ስም የተመሰረተው ፋውንዴሽን በሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ተመዝግቦ በሕጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል " ሲል ፋውንዴሽኑ አስታውሷል።

የድርጅቱ ዋና ዓላማ ከችግርና ድህነት የተላቀቀች፣ ሰላም የሰፈነባት፣ ሰብዓዊ መብትና የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው ብሏል።

ፋውንዴሽኑ ዓላማውን ለማሳካት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ በሰብዓዊ መብትና ማሕበራዊ ፍትሕ፣ አገራችን ከድህነትና ችጋር ልትላቀቅ ስለምትችልበት መንገዶች፣ ቅራኔን በሰላማዊ መንገድ ስለመፍታት፣ በመስኩ ሰፊ የሆነን ልምድ እና እውቀት ባካባቱ ሰዎች ጥናታዊ ወረቀት በማቅረብ ሰፋ ያለን ውይይት በዓመታዊው ጉባኤ ማካሄድ ዋነኛው ነው ሲል ገልጿል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mehal Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share