haileyesus mekonnen

haileyesus mekonnen LG

እባካችሁ እናግዘው!ቴዎድሮስ ካሳሁን ተክሌ  የመዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢነው። በኢቢኤስ ቴሌቭዥን እና በፋና ቴሌቭዥንየፋና ላምሮት የድምፃዊያን ውድድርን በራሱ ቀለም እና ፈጠራ በብቃት በመምራት...
28/05/2025

እባካችሁ እናግዘው!

ቴዎድሮስ ካሳሁን ተክሌ የመዝናኛ ፕሮግራም አቅራቢ
ነው። በኢቢኤስ ቴሌቭዥን እና በፋና ቴሌቭዥን
የፋና ላምሮት የድምፃዊያን ውድድርን በራሱ ቀለም እና ፈጠራ በብቃት በመምራት ይታወቃል።

የፋና ላምሮት የመጀመሪያው የመድረክ አስተዋዋቂ ነበር።
ከምዕራፍ 1 እስከ ምዕራፍ 4
የመጀመሪያውን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድርን በብቃት አቅርቦ ነበር።

ቴዲ በአሁኑ ወቅት ሁለት ልጆቹን በኪራይ ቤት ጥሎ ፀበል ቦታ ነው የሚገኘው። የገንዘብ እጥረትም አጋጥሞታል።
''እባካችሁ እርዱኝ፤ አግዙኝ'' እያለ ነው።

ደጋግ ኢትዮጵያውያን ቴዲን ለመርዳት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር፦

1000298227707 የቻልነውን እንርዳው!

የጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤልያስ አዲስ መጽሐፍ !
19/04/2024

የጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤልያስ አዲስ መጽሐፍ !

እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!
06/04/2024

እንኳን ለሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጨምበላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!

አርሰናል ዋንጫ ይበላል ! ማንቼ ሻምፒየንስ ሊግ ይገባል !--እግር ኳስን የምንወደው እንዲህ ተለዋዋጭ ፣ ሂደት እና ውጤት የተሰናሰሉበት በመሆኑ ነው ።ትናንት ገናና የነበረ ዛሬ ሊንኮታኮት ...
29/03/2024

አርሰናል ዋንጫ ይበላል ! ማንቼ ሻምፒየንስ ሊግ ይገባል !
--
እግር ኳስን የምንወደው እንዲህ ተለዋዋጭ ፣ ሂደት እና ውጤት የተሰናሰሉበት በመሆኑ ነው ።

ትናንት ገናና የነበረ ዛሬ ሊንኮታኮት ፣ ሀያል የተባለው ውራ ሆኖ የሚታይበት ሀቅን ሊጋፈጥም ይችላል ።

በድሮ በሬ ያረሰ የለም ።

በአርሰናልም ሆኖ በሲቲ ቤትም ያለው እውነታ ይህ ነው ።

የዛሬን አያድርገው ኢትሃድ እነ Santi Cazorla የሚቀልዱበት ሜዳ ነበር ፣ petrodollar የኢትሃድን መልክ ቀይረው ፣ ኢምሬትስን የበይ ተመልካች አድረገው አረፉት እንጂ ።

በሰንበቱ ጫወታም - ሌላ አዲስ መልክ የሚገልጥ ይመስለኛል ። rob holding, kolasinac የሉም እንጂ

አርሰናል - ፍጼም በተለየ አቋም ላይ ይገኛል ፣ በኔ እይታ ከደጋፊዎቹም ፣ ከቋጣሪዎቹም ግምት ውጪ ድንቅ ቁመና እያስመለከተን መጥቷል ።

ራያ ተብዬ መዳፋ ረጅም ፣ ሳሊባ ይሉት ግድግዳ ፣ ሼፍ jorginho ከጣፋጭ ሩዝ ጋር በነ ሳካ እና ካይ አሳላፊነት ነው የሚጠብቋቹሁ ።

ለዚህም ነው መነጽራቹን አውልቁና የለውጡን ፍሬ በኢትሃድ ለመልቀም ተዘጋጁሁ የምለው ።

ተማሪው ፣ ከአስተማሪው በቀሰመው ቀለም የመድፈኛውን ድል እንደሚያደምቀው አልጠራጠረም ።

ሲቲን አሳምኖ ካላሸነፈ ዋንጫውን ማንሳቱ እርግጥ ይሆናል ።

ግን ዛሬም ከ10 አመት በፊት በነበረ እይታቹሁ ልትገምቱት የምትሞክሩ ተመልካቾች አሁን ፈንጠዝያውን ብቻ ለመመልከት ትገደዳላቹሁ ።

መልካም ጥምቀት !@ Gamo
20/01/2024

መልካም ጥምቀት !

@ Gamo

18/12/2023

Our Sporting Director has reflected on us being paired with FC Porto in the Champions League round of 16

የአለም ዋንጫ የኒዉኩለር ደርቢ 💥💥💥አያቶላዎቹን ከዋሽንግተን ሰዎች ጋር አይን እና ናጫ ያደረጋቸው የጂኦ ፓለቲካ ፍጥጫ አስርት አመታትን ያለ እረፍት እየጦዘ እንጂ እየሰከነ አልሄደም ።የኑዉ...
18/11/2022

የአለም ዋንጫ የኒዉኩለር ደርቢ 💥💥💥

አያቶላዎቹን ከዋሽንግተን ሰዎች ጋር አይን እና ናጫ ያደረጋቸው የጂኦ ፓለቲካ ፍጥጫ አስርት አመታትን ያለ እረፍት እየጦዘ እንጂ እየሰከነ አልሄደም ።

የኑዉኩለር መርሃ ግብር ፣ የነዳጅ ፓለቲካ እና የርእዮተ አለም መራራቅ ለአለም ዜና የሆኑ ሀገራት እንዲሆኑ አድርጓቸዋል ።

አሜሪካ vs ኢራን

ምእራብና ምስራቅ መሳይ በሆነው 🌎 ግራና ቀኝ ናቸው ።

የኢራን ጠላቶች ጋር ሁሉ አሜሪካ በፍቅር ጨርቋን ትጥላለች ፤ ኢራንም እንዲሁ የነ ቻይና እና ሩሲያ አበልጅ በሏት ።

የሳውዲ የመካከለኛው ምስራቅ አለቃ የመሆን ምኞትን ተገዳዳሪ በየመን የመሀመድ ቢን ሰልማን ጦርነትን ነጥብ ያስጣለች ፤ በድሮን ቴክኖሎጂ ሞስኮን ጭምር ያስታጠቀች በማእቀብ ጡቻ ከመድቀቅ ይልቅ ጡንቻዋ የፈረጠመላት ሀገር ናት ።

ወደው አይስቁ ይላሉ ተንታኞች አሜሪካ የከበዳትን Hypersonic ቴህራን ከሰሞኑ እጇ አስገብታለች ።

እንዲህ አይጥና ድመት የሆኑት ሀገራት ናቸው በአለም ዋንጫ የተፍጠጡት 🤛

የእግር ኳስ አለም ካርታው ላይ ግን የማይታዩ ደካማ ሀገራት ናቸው ማለት ይቻላል 😜

ኳስ ግን አገናኛቸው ።

በምድብ ሁለት ምሽት 1 ሰአት ህዳር 30 🇺🇸 vs 🇮🇷

#የሚገርመው የዋሽንግተን ቡና አጣጯ እንግሊዝም በዚሁ ምድብ ናት ።

11/11/2022

Address

Addis Abeba
Addis Ababa
704

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when haileyesus mekonnen posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to haileyesus mekonnen:

Share