20/07/2026
አርጀንቲናን ብቻውን እንዲሸከም ፈርደውበታል። በአለም ቁጥር አንድ ተጫዋች በመሆኑ ብቻ አርጀንቲናን ተሸክሞ ሁሌም ሻምፒዮን እንዲያደርጋት ይፈልጋሉ።
ሊዮኔል ሜሲ ለሀገሩ የሚሰስተው ነገር የለም። አርጀንቲናን ብቻውን ተሸክሞ የስኬት ጫፍ ለመድረስ የሚችለውን አድርጓል። ሶስት ጊዜ ለአለም ዋንጫ ፍፃሜ አድርሷል። ከዲያጎ ማራዶና በላይ ለሀገሩ የቻለውን ሁሉ አድርጓል።
በሌሎች ተጫዋቾች ስህተትና ድክመት አርጀንቲና ብትሸነፍ እንኳን ለክለቡ የሚሰጠውን ለአርጀንቲና መስጠት አልቻለም ብለው ስሙን ለማጥፋት ሚዲያዎች ሰንፈው አያውቁም።
በከፍተኛ ብቃት ተጫውቶ አርጀንቲና ዋንጫውን ካላገኘች የውድቀት ካባ ያከናንቡታል። ሊዮኔል ሜሲ በግሉ ያሳካውን የእግር ኳስ ስኬት በብሔራዊ ቡድኑ ብቻውን በተደጋጋሚ እንዲያሳካ የተፈረደበት ኮኮብ ነው።
የዛሬውን የአለም ዋንጫ ማጣቱ የሊዮኔል ሜሲን ስኬት ቅንጣት ያህል አይሸረሽረውም። በእግርኳስ ሜዳ ያሳካቸውን ፣ የሰራቸውን ታሪኮች ፣ የነገሰባቸውን የጨዋታ መድረኮች ፣ ያሳካቸውን ዋንጫዎች አያደበዝዘውም።
የእግርኳስ ንጉስ ሆኖ ከሃያ አመታት በላይ ዘውዱን እንደፋው ዛሬም ነገም ይቀጥላል። ማን እንደ ሊዮ ?? ... ወጣት ሆኖ ቀርቶ እድሜው ገፍቶ እንኳን እሱን ሜዳ ላይ ለማየት ያሳሳል ... ኳስን እንዳሻው ሲያደርጋት ማየት ከምንም በላይ ያስደስታል ...
ሊዮ በአርጀንቲና ማሊያ የመጨረሻውን ጨዋታ ዛሬ አድርጓል። በብሔራዊ ቡድን መለያ እሱን አለማየት ከምንም ነገር በላይ አሳዛኝ ነው። እሱን በዚህ መልኩ መሰናበት ያሳምማል። ሊዮኔል ሜሲን በተአምረኛ ግራ እግሩ ሜዳ ላይ ያሻውን እያደረገ ዘውዱን ሲደፋ በዘመናችን መመልከታችን እድለኛ ነን 🙏🙏