Eliannah የአባቷ ልጅ

Eliannah የአባቷ ልጅ the answer of God ❤️

አንዳንዴ ህመምቻችን ሳይሆኑ የሚያሙን ከህመሞቻችን ጀርባ ያሉ ልክ ያልሆኑ ስሜቶች እንደነበሩ የተረዳን ለት ነው !! ✍️2016                                ゚       ...
11/11/2025

አንዳንዴ ህመምቻችን ሳይሆኑ የሚያሙን ከህመሞቻችን ጀርባ ያሉ ልክ ያልሆኑ ስሜቶች እንደነበሩ የተረዳን ለት ነው !! ✍️2016

የሆነ ሰው አለ `እከሌ` አናኗሩን ስትመለከቱ አጠቃላይ ህይወቱ ዓለሙን ሊኖሮው የቻለው ግን እንደት ነው? ስትሉ ልይነቱ ይህ ነው 😏  እከሌን ሊኖሮው የቻለው እንደት እንደሆነ ስመለከት ትኩር...
03/11/2025

የሆነ ሰው አለ `እከሌ` አናኗሩን ስትመለከቱ አጠቃላይ ህይወቱ ዓለሙን ሊኖሮው የቻለው ግን እንደት ነው? ስትሉ ልይነቱ ይህ ነው 😏 እከሌን ሊኖሮው የቻለው እንደት እንደሆነ ስመለከት ትኩር ብዬ አየሁት🕶::

እከሌ ውስጥ የበራች የሆነች መብራት አለች።እኛ ጋርም አንዳንዴ ትበራለች ግን፤ቶሎ ነው የምትጠፋው።እሱ ጋር በርታ ቀርታለታለች ብዬ አስባለሁ።

ምን ማለቴ እንደሆነ በደንብ ላስረዳችሁ።አንዳንዴ በጣም የምናውቀው ሰው በድንገተኛ አደጋ የሚሞትበት አጋጣሚ አለ።ጠዋት ላይ ተገናኝታችሁ፤ከሰዓት ላይ ሞተ የሚባል ዜና ትሰማላችሁ።

መጀመሪያ ማመን አለመቻል እና ድንጋጤ ይኖራል።ከዛ ግን ከቀብር ስንመለስ ስለህይወት እናስባለን።”ህይወት ለካ አጭር ናት።እኛ ራሳችንን በቁም ነገር እናያለን እንጂ ዛሬ ምን እንደሚፈጠር፤መኖር መሞታችንን አናውቅም።ከሞትን በኃላ ደግሞ እንረሳለን” የሚለው እውነት ይገባናል።

ከዛ እዛው ለቅሶ ቤት ውስጥ እያለን ህይወትን እስከ ጥግ መኖር እንዳለብን፤መፍራት እንደሌለብን እንወስናል።ይሄ ነፃነት የሚሰማን በመጥፎ ሳይሆን በመልካም ነው።

በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ከ2 ቀን በኃላ ወደ ቀድሞ ስሜታችን እንመለሳለን።መልሰን ፈሪ እንሆናለን።ሰዎች ስለእኛ ስለሚያስቡት መጨነቅ እንጀምራለን።ያቺ ያልኳችሁ መብራት ጠፋች ማለት ነው።

እከ ጋር ግን ያቺ መብራት እንደበራች ቀርታለች።እኔ አንደኛ ከእከሌ ያስተዋልኩት ነፃነቱን ነው! ህይወትን እስከ ጥግ ለመኖር እንደወሰነ ያስታውቃል።ፍርሃቱን አሽቀንጥሮ ነው የጣለው! መስሚያው ጥጥ ነው።የዛሬ አመት በካንሰር ትሞታለህ ብንባል፤ልንኖር የምንችለውን ህይወት እየኖረ ያለ ይመስላል።

ህይወትን በቁም ነገር አይወስዳትም።ironically ስኬታማ እያደረገው ያለውም ህይወትን በቁም ነገር መውሰድ ማቆሙ ነው።ምክንያቱም ፍርሃት ውስጡ የለም።

ይቺ መብራት ስትበራላችሁ ህይወት ከሰዎች ጋር ውድድር ሳትሆን enjoy መደረግ ያለባት ነገር እንደሆነች ነው የሚሰማችሁ።የማስመሰል ኑሮ ይቆማል።የዛኔ እናንተም ደስተኛ ትሆናላችሁ፤ለሰዎችም ደግ ትሆናላችሁ።ልጁ ወደዚህ መረዳት ከመድረሱ በፊት ብዙ እንደተጋጋጠ ግልፅ ነው።

I think ስኬታማ ለመሆን cheat codeኡ ህይወትን enjoy ማድረግ መቻል ነው።ከፍርሃት መውጣት ነው።ይሄ አንድ አባባልን ያስታውሰኛል።”We have two lives. The second one begins, when we realize we only have one”
😍

ጥያቄውን አለመመለስ አይቻልም😊👇i remember someone once ask somebody  what is the meaning of life? somebody  said life itself has no...
28/10/2025

ጥያቄውን አለመመለስ አይቻልም😊👇
i remember someone once ask somebody what is the meaning of life? somebody said life itself has no meaning!! life is an opportunity to creat a meaning.
me i realized
Eliannah said Meaning of life is your every heartbeat enabling us to experience opportunities ❤️
✍️ Eliannah የአባቷ-ልጅ, [10/28/2025 11:53 AM]

JT (nails, lashes ,makeup and ombre)
📞 0912864211 or 0938800010
゚ ゚

......አየሁት እራሴን የኖርኩት መሰለኝውስጤ ሰላም ሆኖ አይኔ ቢያማትር💞ያልነበረን ሊያይ በስሜት ቢታትርየሰፈነን ሰላም ሊያሸብር ቢጥርአልገለጥ አለኝ የብዥታው ሚስጥርባልሄድኩት ጎዳና ሄጄ ...
12/10/2025

......አየሁት እራሴን የኖርኩት መሰለኝ

ውስጤ ሰላም ሆኖ አይኔ ቢያማትር💞
ያልነበረን ሊያይ በስሜት ቢታትር
የሰፈነን ሰላም ሊያሸብር ቢጥር
አልገለጥ አለኝ የብዥታው ሚስጥር

ባልሄድኩት ጎዳና ሄጄ 💖ባስተውለው
ባልኖርኩት ህይወት ውስጥ ህይወቴን ባኖረው
ባላሰብኩት ማእበል ሰምጦ ቢገኝ ነፍሴ❤️
ሊቋረጥ ቢጣጣር ትንሹ እስትንፋሴ...........አየሁት እራሴን የኖርኩት መሰለኝ

゚viralシ

በህይወት ውስጥሳንፈልግ ስላደረግነው ነገር ነፍሳችን ስታስጨንቀን ፈልገን ስላጣነው ነገር አእምሮአችን ሰላም ሲነሳን በመሀል ሸንጋያችን አለች  እሷ ደግሞ ህይወት ናት። በህይወት ውስጥ ጥያቄና...
07/10/2025

በህይወት ውስጥ
ሳንፈልግ ስላደረግነው ነገር ነፍሳችን ስታስጨንቀን ፈልገን ስላጣነው ነገር አእምሮአችን ሰላም ሲነሳን በመሀል ሸንጋያችን አለች እሷ ደግሞ ህይወት ናት። በህይወት ውስጥ ጥያቄና መልስ ብሎ ነገር የለም ህይወት ጥያቄ ስትሆን መልስ ደግሞ መኖር ነው🔥 እናላቹ ወዳጆቼ እየኖራቹ .......በጊዜሁሉ ውብ ይሆናል❤️🙏
✍️ Eliannah የአባቷ ልጅ

#ፍቅርህ

መስታወት እንዴት?ዛሬ የሆነ podcast እያየሁ ነበር።በተነገረው ሀሳብ የምትስማሙ ወይም የማትስማሙ ከሆነ ትነግሩኛላችሁ።ስኬታማ የሚባል ሰው ነው ተናጋሪው።እና ምን አለ መሰላችሁ…..ሴት ል...
19/09/2025

መስታወት እንዴት?
ዛሬ የሆነ podcast እያየሁ ነበር።በተነገረው ሀሳብ የምትስማሙ ወይም የማትስማሙ ከሆነ ትነግሩኛላችሁ።ስኬታማ የሚባል ሰው ነው ተናጋሪው።እና ምን አለ መሰላችሁ…..

ሴት ልጅ ለወንድ እንደ መስታወት ናት።መስታወት ጋር ስትቆሙ መስታወቱ አይዋሻቹም።ራሳችሁን እየጠበቃችሁ ከሆነ አሪፍ ላይ ናችሁ ይላችኃል።ራሳችሁን ጥላችሁም ከሆነ ይነግራችኃል።ንፁ ካልሆናችሁ እንዳልሆናችሁ ይጠቁማችኃል፤ካማረባችሁ ደግሞ ዛሬ ፅድት ብለሃል ይላችኃል።

እና ምን አለ ሰውዬው…ሴት ልጅም ለወንድ ልጅ እንደዛ ናት።መስታወት ናት።በምትሄድበት በሙሉ ሴቶች special treatment የሚሰጡህ ከሆነ፤ካንተ ጋር ሲሆኑ ልስልስ ያለ feminine ባህሪ የሚያሳዩ ከሆነ፤ ወደ ሴትነት ጫፍ የሚጠጉ ከሆነ፤ቢሮ ስትሄድ ፤ድግስ ላይም ስትሄድ ያንተን presence enjoy የሚያደርጉት ከሆነ፤በህይወት ጥሩ መንገድ ላይ እንዳለህ ማሳያ ነው።

ጠንክረህ እየሰራህ እንደሆነ፤ጊዜህን እየተጠቀምክ እንደሆነ፤በህይወት እያሳካኸው ያለ ነገር እንዳለ፤ፈጣሪ የሰጠህን አቅም እየተጠቀምክ እንደሆነ ምልክት ነው።

በተቃራኒው ደግሞ ለሴት ልጅ መኖር፤አለመኖርህ የማይታወቃት ከሆነ፤ከእናትህ በስተቀር ለአብዛኞቹ ሴቶች invisible ከሆንክ፤በምትሄድባቸው ቦታዎች ከሴቶች special treatment የማታገኘ ከሆነ፤መስታወቱ ላይ አትናደድ።መስታወቱ አንተን በግል አይጠላህም።it’s not personal.እውነታውን ነው እየነገረክ ያለው።ራስህን አስተካክለክ መስታወቱ ጋር ተመልስ።ከዛ ራስህን እየው።

እና ይሄ ሰውዬ ትክክል ነው ወይስ ዝም ብሎ ነው የሚቀባጥረው? ወንዶች ሴቶችን እንደ መስታወት መጠቀም እንችላለን?

゚viralfbreelsfypシ゚viral Eliannah የአባቷ ልጅ Page Six

ተጏዝ ሀሳብ ነኝ🚶‍♂️‍➡️....... እንደነገሩ አድርገን የሸኘናቸው ነገሮችና ሁኔታዎች  ብዙ ጊዜ በጣም ዋጋ ያስከፍሉናል ምክንያቱም በህይወት ውስጥ ምንም ነገር ካለ ምክንያት አይከናወንም...
17/09/2025

ተጏዝ ሀሳብ ነኝ🚶‍♂️‍➡️....... እንደነገሩ አድርገን የሸኘናቸው ነገሮችና ሁኔታዎች ብዙ ጊዜ በጣም ዋጋ ያስከፍሉናል ምክንያቱም በህይወት ውስጥ ምንም ነገር ካለ ምክንያት አይከናወንም እያንዳንዱ ነገሮች የራሳቸው የሆነ ምክንያትና ውጤት አላቸው ። ህይወት ሚስጢር ናት
ብዙ ጊዜ ሰዎች ስንባል አስተውላቹ የምታውቁ ከሆነ ብዙዎቻችን እኛ አውቀን ሆነ ሳናውቅ ከምናደርጋቸው ወይም ከምናስባቸው ነገሮች ኣልፎ ሳናስተውል ከምናስባቸው ነገሮች ራሱ የሆነ ሰው እንዲረዳን ለኛ እንዲኖርልን እንፈልጋለን ልክ እንደኛ😥 እውነታው ግን ማንም እንደራሳሁ የሚኖሩላችሁ የለም እናንተ የምታስቡት ሆነ የምታደርጉት ነገር በመጀመርያ በዚህ ምድር ከፈጣሪ ቀጥሎ እናንተ ናችሁ ለራሳችሁ ያላችሁት የኔ ሰው የምትሉት እራሱ የእናንተ ኣይደለም። ምክንያቱም እሱ ራሱ የራሱ አይደለምና !! ይህ ግልፅ እንዲሆንላችሁ ተወልዳችሁ አድጋችሁ ከወላጆቻችሁ ተለያይታችሁ መኖር ትጀምራላችሁ ከዛ የኔ ዓለም (የግል ህይወት ) የሚል ሀሳብ ማሰብ ትጀምራላችሁ ግን የኔ የምትሉት ዓለም 🌎የእናንተ ብቻ ነው እውነት? እስኪ አስቡት ማንም ሰው የሚሰራው ለራሱ ብቻ ይመስላቹሀል በልቶ ለማደር አይደለም ብዙዎቻችን ለሰው ነው የምንኖሮው ግን ለኛ የሆነ ሰው እንዳለን ማሰብ ስለምንፈልግ ነው ለምን ሲባል ህይወት ትርጉም እንዲኖራት የምንኖርለት ነገር ሲኖር እየኖርን እንደሆነ እንዲሰማን ስለሚያደርገን ነው ። ይህ የመልካምነት መንፈስ የተዋሃድነው በሱ አምሳል የፈጠረን ከክርስቶስ ፍቅር♥️ የተቀዳ ነው እናም ህይወታችሁ ፀፀት እንዳይሰማችሁ ትርጉም ያለው ህይወት ለመኖር መሞከር ማቆም የለባቹሁም። ሚስጢሩ ደግሞ ክርስቶስ ነው ። እግዚአብሄር ወቶ የሚፈልገው ንፁሀን ኣይደለም ሀፃተኞችን ነው ለማዳን ሰው ሲልክልን ፍቃድ ይኑረን እስኪ🍀 በእያንዳንዱ የህይወት እንቅስቃሴያችሁ ሆነ ሀሳባችሁ የመኖር ዓላማ ትርጉሙ ሊሆን የሚገባው እግዚኣብሄር የሚገለጥበት የህይወት መንገድ ስለመያዛችሁ እርግጠኛ ሁኑ ። ከሱ ውጭ ህይወት የሌለው ቁስ ነንና !! ✍️ Eliannah የአባቷ ልጅ
መልካም እለተ እሮብ ተመኘሁ 🙏
゚viralfbreelsfypシ゚viral

እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ          🌼🌼 በሰላም አሸጋገረን 🌼🌼በዓሉን:- የሰላም 🌻🌻🌻             የፍቅር  🌻🌻🌻              የአንድነት 🌻🌻🌻      ...
11/09/2025

እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ
🌼🌼 በሰላም አሸጋገረን 🌼🌼
በዓሉን:- የሰላም 🌻🌻🌻
የፍቅር 🌻🌻🌻
የአንድነት 🌻🌻🌻
እና የመተሳሰብ ያርግልን።🌻🌻🌻
መልካም በዓል🌻🌻🌻🌻

2018.........................🌼🌼🌼🌼

....🖤......confident women walks in to a men life and brings value but, she don`t make him her entire world. she has a l...
08/09/2025

....🖤......
confident women walks in to a men life and brings value but, she don`t make him her entire world. she has a life outside of him : her passion, her goal, her own happiness. she doesn't rearrange everything just to fit in to his schedule. she doesn`t beg for his time or attention. when a men sees that a women is securing herself it makes her more attractive confident is magnetic it tell a man that you don`t need him. you choose him its a big d\t when a man knows is being . chosen not top tolerated out of fear of being along. Eliannah የአባቷ ልጅ

አንተዬ ፍም ነው  #ፍቅርህ ለመሞቅ አይበቃም ወይ ክንድህአልገባበጥበት ብቻ ልተኛ ከደረትህ   አይሳሳትም እሱ ሚዛኑ ሲሰራ ልዩ ነው ተፈጥሮህ   እሳቱ  እንዲበርድልህ እኔን ውሃ አድርጎ ሰራ...
06/09/2025

አንተዬ ፍም ነው #ፍቅርህ
ለመሞቅ አይበቃም ወይ ክንድህ
አልገባበጥበት ብቻ ልተኛ ከደረትህ
አይሳሳትም እሱ ሚዛኑ ሲሰራ ልዩ ነው ተፈጥሮህ
እሳቱ እንዲበርድልህ እኔን ውሃ አድርጎ ሰራልህ
እንዳልጠፋ ከደረትህ እንድኖር ልቋደስ ከትንፏሽህ
አንተዬ ፍም ነው #ፍቅርህ በልብህ አኑረኝ ከነብስህ::

Instagram Quite Perry CrownShoot Ethiopian Airlines Eliannah የአባቷ ልጅ

አንዳንድ ህመሞች ህይወት ያለውን ስሜት ይገድላሉ ። በተቃራኒው ደግሞ አንዳንድ ህይወት ያላችው ስሜቶች በህመም ም/ት ህይወት ያጣሉ :: Eliannah የአባቷ ልጅ  ゚               ...
05/09/2025

አንዳንድ ህመሞች ህይወት ያለውን ስሜት ይገድላሉ ። በተቃራኒው ደግሞ አንዳንድ ህይወት ያላችው ስሜቶች በህመም ም/ት ህይወት ያጣሉ :: Eliannah የአባቷ ልጅ

✍️ no caption
04/09/2025

✍️ no caption



Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eliannah የአባቷ ልጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Eliannah የአባቷ ልጅ:

Share