Ethiopian Radio /የኢትዮጵያ ሬድዮ/

Ethiopian Radio /የኢትዮጵያ ሬድዮ/ Ethiopian Broadcasting Corporation is a 24 hour working public media.
(1)

Ethiopian Broadcasting Corporation is a national media which disseminates its news and programs world wide via Television,Radio and Website.

14/10/2025

ዜና ፋይል .... 04/02/2018

አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ ****************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አ...
14/10/2025

አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ
******************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ሳንዶካን ደበበ የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ።

14/10/2025

ዜና ሀገር ....04 /02/2018

14/10/2025

የኢትዮጵያ ሬዲዮ | Ethiopian Radio ... ጥቅምት 04/2018 ዓ.ም
Ethiopian Radio | Ethiopian Radio

የትንሿ ደሴት የዓለም ዋንጫ አዲስ ምዕራፍ************ይሄ 50ኛ ዓመት የነጻነት በአሏን እያከበረች ያለችው ደሴቲቱ ሀገር በልፋቷ ያገኘችው የገዘፈ ሽልሟቷ ነው፡፡ በአትላንቲክ ውቂያኖስ...
14/10/2025

የትንሿ ደሴት የዓለም ዋንጫ አዲስ ምዕራፍ
************

ይሄ 50ኛ ዓመት የነጻነት በአሏን እያከበረች ያለችው ደሴቲቱ ሀገር በልፋቷ ያገኘችው የገዘፈ ሽልሟቷ ነው፡፡ በአትላንቲክ ውቂያኖስ ውስጥ ከሚገኙ ትንንሽ ደሴቶች አንዷ የሆነችው ኬፕ ቨርዴ በታሪኳ ለመጀመርያ ጊዜ በትልቁ የዓለም ዋንጫ መድረክ መሳተፏን አረጋጣለች፡፡

በ1975 ከፖርቹጋል ቅኝ ግዛት ነጻ የወጣችው ኬፕ ቨርዴ ነጻ ሀገር ሆና ከቆመች ገና 50 ዓመቷ ቢሆንም ታሪክ ለመስራት ግን ዕድሜ ከቁጥር ያለፈ ትርጉም እንደሌለው አሳይታለች፡፡

4 ሺህ ስኩየር ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋት ያላት ምእራብ አፍሪዊቷ ሀገር በ96 ዓመት የዓለም ዋንጫ ታሪክ በመድረኩ የተሳፈች ትንሿ ሀገርም ሆናለች፡፡ 5 ሺህ ስኩየር ኪሎ ሜትር ስፋት ያላት ትሪንዳድ እና ቶቤጎ በ2006ቱ የጀርመን ዓለም ዋንጫ ተሳታፊ የነበረችበት በክብረ ወሰንነት ተይዞ የነበረ ቢሆንም አሁን በሌላ ትንሽ ሀገር ተተክታለች፡፡

በሌላ በኩል 525 ሺህ ህዝብ ያላት ኬፕ ቨርዴ 325 ሺህ የህዝብ ቁጥር ካላት አይስላንድ በመቀጠል በዓለም ዋንጫ ማሳተፏን ያረጋገጠች ትንሽ ህዝብ ያላት 2ኛዋ ሀገርም ሆናለች፡፡ አውሮፓዊቷ ሀገር አይስላንድ በ2018ቱ የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ለመጀመርያ ጊዜ ተሳታፊ እንደነበረችም ይታወሳል፡፡

በአፍሪካ ሀገራት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ምድብ አራት ላይ የነበረችው ሀገር ካደረገቻቸው 10 ጨዋታዎች ሰባቱን አሸንፋ በሁለቱ ደግሞ ነጥብ ተጋርታ በ23 ነጥብ ምድቡን በበላይነት በማጠናቀቅ የዓለም ዋንጫ ትኬቷን ቆርጣለች፡፡

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ በኬፕ ቨርዴ ብሔራዊ ስቴዲየም ኢስዋቲኒን 3 ለ 1 ስታሸንፍ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ጆዜ ማሪያ ፔሬዝ ታሪካዊውን እና ሀገራቸው ለዓለም ዋንጫ ማለፏን ያረጋገጠችበትን ጨዋታ በስቴዲየም ተገኝተው ተመልክተዋል፡፡

የሚገርመው እዚህ ምድብ ላይ በመድረኩ ትልቅ ልምድ ያላት የአንድሬ ኦናና እና ሳሙኤል ኢቶ ሀገር ካሜሩን ብትኖርም ኬፕ ቨርዴን ተከትላ ከማጠናቀቅ ውጭ አማራጭ አልነበራትም፡፡ የሀገሪቱ ዜጎችም በትልቋ ከተማቸው ፕራያ ጎዳናዎች ደስታቸውን ሲገልጹ አምሽተዋል፡፡

ለሀገሪቱ ዜጎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ያስተላለፉት የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ፌደሬሽኖች ማህበር ፊፋ ፕሬዝደንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ “የሀገራችሁ ሰንደቅ አላማ በትልቁ መድረክ ከፍ ብላ የምትታይበት እና ብሔራዊ መዝሙራችሁ በዓለም የሚሰማበት ይሆናል” ብለዋል፡፡

የእግር ኳሷ ዋናው የስኬት ምስጢር የኬፕ ቨርዴ የዘር ሀረግ ያላቸውን እና በአውሮፓ የሚኖሩ ልጆቿን ማሰባሰቧ እንደሆነ የሚነገርላት ደሴቲቷ ሀገር እግር ኳሷ ላይ በፈጠረችው አቢዮት 15 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከአህጉሩ ትልቁ መድረክ ተሻግራ በዓለም ዋንጫ ተከስታለች፡፡

ኬፕ ቨርዴ በአፍሪካ ዋንጫ ለመጀመርያ ጊዜ የተሳተፈችው በ2013 የደቡብ አፍሪካ ዋንጫ ሲሆን ሁለት ጊዜ ደግሞ ለሩብ ፍጻሜ የደረሰችበትን ውጤት ማስመዝገቧም ይታወሳል፡፡

የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ የቀድሞው የኬፕ ቨርዴ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ቡቢስታ በአምስት ዓመታት ቆይታው በሁሉም መንገድ የተዋጣለት ቡድን ገንብቶ አዲስ ታሪክ ጽፏል፡፡

በፊፋ የሀገራት የደረጃ ሰንጠረጅ 70ኛ ላይ የተቀመጠችው ሀገር እንደ ኡዝቤኪስታን እና ጆርዳን ሁሉ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ በጣምራ በሚያዘጋጁት የዓለም ዋንጫ ለመጀመርያ ጊዜ የምትሳተፍ ሀገርም ሆናለች፡፡

በአንተነህ ሲሳይ

ከዓመታት ስቃይና ደም መፋሰስ በኋላ የጋዛ ጦርነት አብቅቷል - ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ**********************ከዓመታት ስቃይ እና ደም መፋሰስ በኋላ የጋዛ ጦርነት አብቅቷል ሲሉ...
13/10/2025

ከዓመታት ስቃይና ደም መፋሰስ በኋላ የጋዛ ጦርነት አብቅቷል - ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ
**********************

ከዓመታት ስቃይ እና ደም መፋሰስ በኋላ የጋዛ ጦርነት አብቅቷል ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ፡፡

አሜሪካ፣ ቱርኪዬ፣ ግብፅ እና ኳታር በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ የተፈረመው በግብፅ እየተካሄደ በሚገኘው የሻርም ኤል ሼክ የሰላም ጉባኤ ላይ ነው፡፡

ስምምነቱን የሀገራቱ መሪዎች የፈረሙ ሲሆን፤ ሰነዱ ቀጣዩን የጋዛ አስተዳድር በተመለከተ፣ በቀጠናው ዘላቂ ሰላም ማስጠበቅ በሚቻልበት ሁኔታ እና በመልሶ ግንባታ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስምምነቱ በይፋ ከተፈረመ በኋላ ባደረጉት ንግግር፤ ከዓመታት ስቃይ እና ደም መፋሰስ በኋላ የጋዛ ጦርነት አብቅቷል ብለዋል፡፡

ይህ ለውጥ እንዲመጣ ላደረጉ የአረብ እና የሙስሊም አገራትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አሁን በጋዛ የመልሶ ግንባታ ስራ ተጀምሯል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ይህ ቀን እንዲመጣ በቀጠናው እና በአለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ሲጥሩ፣ ሲመኙ እና ሲጸልዩ ነበር ብለዋል፡፡

ዛሬ የተፈረመው የጋዛ የተኩስ አቅም ስምምነት ሰነድ ታሪካዊ ነው ሲሉም መግለፃቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በሰላም ውይይቱ ላይ 20 የሚሆኑ የሀገራት ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ የቱርክ፣ የፍልስጤም፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ኳታርና የሌሎች ሀገራት መሪዎች እንዲሁም የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በአፎምያ ክበበው

በጊቤ ሸለቆ የፍራፍሬ መንደር የመሰረቱት ወጣቶች **************በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የም ዞን በሳጃ ዙሪያ ወረዳ በዲቻ ቀበሌ ከ20 ሔክታር በላይ ማሳ በተደራጁ ወጣቶች በፍራፍሬ...
13/10/2025

በጊቤ ሸለቆ የፍራፍሬ መንደር የመሰረቱት ወጣቶች
**************
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የም ዞን በሳጃ ዙሪያ ወረዳ በዲቻ ቀበሌ ከ20 ሔክታር በላይ ማሳ በተደራጁ ወጣቶች በፍራፍሬ እየለማ ነው።

አካባቢው ቀደም ሲል የማይታረስና ለልማት ያለዋለ እንደነበር የገለጸልን የዞኑ ግብርና መምሪያ ከ2012 ጀምሮ ከዞኑ ሁሉም ቀበሌዎች ስራ አጥ ወጣቶችን በአካባቢው በማስፈር ውጤታማ ስራ መከናወኑን ገልጿል።

በዚህም ቁጭት በወለደው ተነሳሽነት እስካሁን 14 ሔክታር መሬት በሙዝና 6 ሔክታር መሬት ደግሞ በፓፓያ ለምቷል።

በፍራፍሬ ልማቱ የተሰማሩ ወጣቶችም ቀደም ሲል ስራ አጥ እንደነበሩ ገልጸው በአሁኑ ወቅት ምርታቸውን ለገበያ በማቅረብ ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አካባቢው በፍራፍሬ ሊለማ የሚችል ሰፊ ተስማሚ መሬት ቢኖረውም ሳያለሙ መቆየታቸው አሁን በቁጭት እንዲሰሩ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል።

በአካባቢው ያለውን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው በቀጣይ ይበልጥ በማልማት ምርታቸውን ወደ ማእከላዊ ገበያና አልፎም ወደ ውጭ ለመላክ ማቀዳቸውንም ወጣቶቹ ተናግረዋል።
በኑርዬ አባተ

13/10/2025

ዜና ፋይል .... 03/02/2018

ተፈላጊነቱ የጨመረዉ ሮዝመሪ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል! *******************በኢትዮጵያውያን ዘንድ አዝመሪኖ ወይም የስጋ መጥበሻ እየተባለ ይጠራል፡፡ ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ስያሜው በቀ...
13/10/2025

ተፈላጊነቱ የጨመረዉ ሮዝመሪ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል!
*******************
በኢትዮጵያውያን ዘንድ አዝመሪኖ ወይም የስጋ መጥበሻ እየተባለ ይጠራል፡፡ ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ስያሜው በቀጥታ ወስደው የሚጠሩት ደግሞ ሮዝመሪ ይሉታል፡፡
ብዙውን ጊዜ ወጥ ለማጣፈጥ፣ በርበሬ ለመደለዝና አይብ ሳይበላሽ እንዲቆይ ስለሚጠቅም በእናቶቻችን ጓዳ ውስጥ አይጠፋም፡፡ አልፎ አልፎ ደግሞ ከሌሎች የእጽዋት አይነቶች ጋር ተዳብሎ ሲተከል ግቢን ያሳምራል ብለው የሚያምኑ አንዳንድ ግለሰቦች ይተክሉታል፡፡ ነገር ግን ይህ መአዛማና መድሀኒታማ እፅዋት በሰፊው ከተመረተ ለአለማቀፉ ገበያ መቅረብ ይችላል፡፡

እንደሀገር ቀደም ብለው በማምረት ወደውጭ ገበያ የማቅረብ እንቅስቃሴውን የጀመሩት በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን የሚኖሩ ጥቂት አርሶ አደሮች ናቸው፡፡ አሁን ላይ ይህ ተሞክሮ እየሰፋ በዚያው ክልል ወደሚገኘው የም ዞን ፎፋ ወረዳ ደጋማ መልክዓ ምድር መልማት ጀምሯል፡፡

ቦሮ በዞኑ ፎፋ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ የየም ብሄረሰቦች በአመት አንድ ጊዜ ጥቅምት 17 ላይ ተተገናኝተው ባህላዊ መድሀኒት ይሰበስቡበታል፡፡ የተራራው ተዳፋታማነት ከፍተኛ ስለሆነ ለእርሻ ስራ ምቹ አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት ለአመታት አፈሩ በጎርፍና በነፋስ ሲሸረሸር እንደኖረ የወረዳው ግብርና ጽህፈት ዋና ሀላፊ አቶ አቢዮት ሲሳይ ይገልፃሉ፡፡

አሁን ላይ በተራራው ወገብ ዙሪያ የጠረጴዛ እርከን በመስራት ሮዝመሪ ተክለው እያለሙበት ይገኛሉ፡፡ በወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት አማካኝነት ባለፈው አመት ተተክሎ አሁን ፀድቆ የሚታየው ሮዝመሪ አጠቃላይ ስፋቱ 15 ሄክታር እንደሚሆን ሀላፊዉ ተናግረዋል፡፡

ከቦር ተራራ ውጭ ከፎፋ ከተማ ትንሽ ወጣ ብሎ በሚገኝ ስፍራ በአንድ ኢንቨስተር የሚለማ የሮዝመሪ ማሳ አለ፡፡ የፎፋ ቸከራ ሮዝመሪ ፕሮጀክት ይባላል፡፡ ለስራው ይሆን ዘንድ ከወረዳው 50 ሄክታር የሚሆን ማሳ ተቀብለው ወደስራው እንደገቡ የሚናገሩት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ከማል ሙጌ ናቸው፡፡ በስልጤ ዞን እየለማ ከሚገኘው የሮዝመሪ ማሳ ልምድ እንደወሰዱ የገለጹት አቶ ከማል የየምን ደጋማ ምድር ካዩ በኋላ ወደስራው ሊገቡ ችለዋል፡፡

እስካሁን ከተረከቡት 50 ሄክታር ውስጥ 15 ሄክታሩን በሮዝመሪ እንደሸፈኑም ተናግረዋል፡፡ ከ3 አመት በፊት የተተከለው አሁን ላይ ለመሰብሰብ ደርሷል፡፡ ነገር ግን እንደፕሮጀክቱ አስተባባሪ ገለፃ አሁን ላይ የደረሰውን ምርት ከመሰብሰብ ይልቅ ያልተተከለውን ማሳ ለመሸፈን በችግኝነት እንደሚጠቀሙት ገልፀዋል፡፡

ለወደፊት ፕሮጀክቱ ከያዘው ማሳ በተጨማሪ ችግኙን ለአርሶ አደሮች በማከፋፈል የምርት መጠናቸውን በመጨመር ለገበያ እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል፡፡ እንደእቅዳቸው ሮዝመሪው በሁለት መልኩ ለገበያ ይዘጋጃል፡፡ አንደኛው ቅጠሉን አድርቆ ቀጥተኛ ምርቱን መላክ ሲሆን በሌላ ጎን ደግሞ ቅጠሉን ጨምቆ ወደ ዘይት የሚቀይር ፋብሪካ በማቋቋም ወደአለም ገበያ ለማቅረብ እቅድ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ካንሰርን ጨምሮ ከፍተኛ የራስ ምታትን እንደሚከላከል የሚጠቀስለት ሮዝመሪ ምግብ ቶሎ እንዳይበላሽም ይጠብቃል፡፡ ከባክቴርያ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጉዳቶችን ይቀንሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአፈር አሲዳማነትን በመቀነስ ምርትና ምርታማነት እንዲያድ ያግዛል ሲሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡

በአሳመረ አስፋዉ

እየተጠናከረ የመጣው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት*************በአውሮፓውያኑ ታኅሳስ 12 ቀን 2024 በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈረመው የአንካራ ስምምነት የሁለቱን ሀገራ...
13/10/2025

እየተጠናከረ የመጣው የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት
*************

በአውሮፓውያኑ ታኅሳስ 12 ቀን 2024 በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈረመው የአንካራ ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በከፍተኛ ሁኔታ አሻሽሏል።

የኢትዮጵያን የቀይ ባሕር መውጫ ጥያቄን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እንዲሻክር በሦስተኛ ወገን ጥረት ቢደረግም፣ ከጉርብትና አልፎ የደም ትስስር ያላቸው ሁለቱ ሀገራት ግን ወደ ተሻለው መንገድ መጥተዋል፡፡

በሦስተኛ ወገን በተደረገው ጫና ምክንያት ሶማሊያ የያዘችው አቋም ወደ ትክክለኛ መንገድ የመጣው ከሁለቱም ሀገራት ጋር ጠንካራ ግንኙነት በአላት ቱርክ በተመቻቸው የአንካራ ስምምነት ነው።

ሶማሊያ የኢትዮጵያ የቀይ ባሕር መውጫ ጥያቄ ትክክለኛ በመሆኑ እንደምትቀበለው ሰትገልጽ፣ ኢትዮጵያ የሶማሊያን የግዛት አንድነት በማክበር የባሕር በር ጥያቄዋን ለመቀጠል ተስማምተዋል።

ከዚያ ባለፈ ሁለቱ ሀገራት የቆየውን ታሪካዊ ግንኙነታቸውን በማጠናከር ለቀጣናው ሰላም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የሁለቱ ሀገራት ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ በመሪዎች ደረጃም በተደጋጋሚ ተገናኝተው መክረዋል።

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሐመድ በተደጋጋሚ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የሥራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሞቃዲሾ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል።

መሪዎቹ በሚያወጧቸው የጋራ መግለጫዎችም የደኅንነት ትብብርን ለማጠናከር እና ቀጣናው ላይ ስጋት የደቀነውን ሽብርተኝነት በጋራ ለመዋጋት ተስማምተው ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡

የመሠረተ ልማት ትስስርን በማስፋፋት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን፣ ንግድን እና ኢንቨስትመንትን ማጠናከርም ሁለቱ ሀገራት እየሠሩባቸው ያሉ ጉዳዮች ናቸው።

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሙሐመድ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ለመመረቅ ከተገኙ መሪዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ፣ የግድቡን ሪቫን እንዲቆርጡ መጋበዛቸው የግንኙነቱ መሻሻል ማረጋገጫ ነው፡፡

ፕሬዚዳንቱ በቅርቡ ከአል-ዓረቢያ ጋር ባደረጉት ቆይታም በርካታ ኢትዮጵያን የተመለከቱ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ በሰጡት ሀሳብ ግድቡ ማንንም እንደማይጎዳ አስምረውበታል፡፡

ኢትዮጵያ ረጅም ድንበር የምትጋራቸው የረጅም ጊዜ ጎረቤታቸው እንደሆነች ጠቅሰውም፣ የኢትዮጵያ ልማት ሶማሊያን እንደሚጠቅም አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ጥያቄም ትክክለኛ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ፣ በዚህ ምክንያት ማንም ግጭት ውስጥ መግባት እንደሌለበት ጠቁመዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ትላንትም በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝ በማድረግ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የመከሩ ሲሆን፣ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋትን ለማጠናከር ከኢትዮጵያ ጋር እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል፡፡

መሪዎቹ ሁለቱ ሀገራት በኢኮኖሚ፣ ኢንቨስትመንት እና ንግድ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የተስማሙ ሲሆን፣ ጠንካራ የኢኮኖሚ ትብብር በመፍጠር የንግድ ትስስራቸውን የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት መስመሮችን ለማስፋት እና የጋራ ብልፅግናቸውን ለማረጋገጥ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በለሚ ታደሰ

13/10/2025

ዜና ሀገር ....03 /02/2018

Address

Churchill Road
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Radio /የኢትዮጵያ ሬድዮ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Radio /የኢትዮጵያ ሬድዮ/:

Share

Category