
21/07/2024
አምባገነኖች ከአንድ ወንዝ ይቀዳሉ !
" ቁርጥ'ሷን ''
ከሰሞኑ ሊዊስ ናኒ አዲስ አበባ መጥቶ ነበር። ለምን እንደመጣ ራሴን ስጠይቅ ሰነበትኩ ፡ የካኑ እንኳን ብዙም ግድ አልሰጠኝም ።
ልጅነቴን የጨረስኩት ማንቸስተር ዩናይትድን ከልቤ በመደገፍ ነበር ለዛም ነው ናኒ ለምን መጣ ያልኩት።
(የኳስ ነገር ምንም ለማይገባችሁ ናኒ የማንቸስተር ዩናይትድ የአንድ ወቅት ፈርጥ ነው)
እናም በውስጤ ይብሰለሰል የነበረው ጥያቄ ድንገት መልሱ ፊቴ ላይ ድግን አለ።
ስሎቦዳን ሚሊሶቪች የሚሉት ዩጎዝላቪያን 1989-1997 G.C የመራ አምባገነንና ቦስኒያዎችን በዘር መርጦ ሲጨፈጭፍና በጅምላ ሲያስር የነበረ "ቡቸር" መሪ ድንገት ትዝ አለኝ።
ይህ አምባገነን በጊዜው እየፈረሰች ያለችውን ዩጎዝላቪያ ፡ዓለም በሌላ መልክ ይይልኝ ብሎ (ገፅታ ግንባታ መሆኑ ነው) የዓለማችን ምርጥ የእግር ኳስ ተጨዋች የሆነውን አርጀንቲናዊ ተጫዋች ዲያጎ አርማንዶ ማራዶናን …ና !ሀገሬን ጎብኛት ፡በዛውም አድንቃት ብሎ ጋበዘው ።
ማራዶናም 150 ሺ $ ተከፍሎት ወጭው ተሸፍኖለት ፡ዩጎዝላቪያ ገባ። ያየውን ፡የሰማውን አደነቀ ። በርታ ሚሊሎሶቪች አለ ። (ምን'ኳ የማራዶና አድናቆት ኃላ ላይ ሚሎሶቪችን ህግ ፊት ከመቆም ባያስጥለውም ቅሉ)
የኛም ነገር ይሄው ነው ። ሊዊስ ናኒ በርቱ ብሎ ይሆናል ፡፡ ነገር ግን በዘራችንና በማንነታችን ብቻ ያለምንም ወንጀላችን ግድያ'ና ጅምላ እስር የሚፈፅሙብንን መጨረሻ ላይ ህግ ፊት ቀርበው መልስ ይሰጡበታል።
አዎ። ማራዶና ሚሎሶቪችን ካላዳነው ሊዊስ ናኒ ማንን ከህግ ሊያስጥል ነው ?
ኤርሚያስ አለባቸው