06/11/2022
#መልዕክት🕊
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የፕሪቶሪያውን የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ስምምነት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ መላው ህዝብ በጦርነቱ ሳቢያ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ እና ለዘላቂ ሰላም እንዲነሳ ጥሪ አቅርቧል።
የካውንስሉ ፀሀፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ ካስተላለፉት መልዕክት ፦
" የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲሆንና ሕዝባችን ከፍርሃት፣ ከጭንቀት፣ ከስድትና መከራ ያርፍ ዘንድ የሁሉንም ወገኖች ጥረት ይጠይቃል።
መላው ሕዝባችን አፍራሽ ከሆነ ተግባር በመራቅ እና ባለፉት ሁለት ዓመታት በደረሰባቸው ጉዳት ያዘኑትን ወገኖች በማጽናናት፣ ቤታቸውና ንብረታቸው የወደመባቸውን መልሶ በማቋቋም፤ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን በመደገፍ እና በማበርታት ለዘላቂ ሰላም በአንድነት እንድንነሳ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።
ስምምነቱ እውን እንዳይሆንና ተመልሰን ወደ ግጭት እንድንገባ የሚያደርጉ ቅስቀሳዎች ሊኖሩ ይችላሉ ፤ በልዩ ልዩ የመገናኛ ዘዴዎች የሚተላለፉ አፍራሽ መልዕክቶችን ቸል በማለት ለስምምነቱ ተግባራዊ መሆን ተግተን ልንሰራ ይገባል።
ከዚህ በተጨማሪም በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የትግራይ፣ የአማራና የአፋር ሕዝቦች ለጋራ ሰላምና ዕድገት በይቅርታ ተቀራርበው እውተኛ እርቅ እንዲያከናውኑ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በአንድነት በመቆም መስራት ይገባል።
.. የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል አቅም በፈቀደው ሁሉ ለሀገር ሰላምና ለሕዝቦችዋ ዕድገት አስፈላጊውን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም። "
DDAILY News EthiopiaNDAILY News EthiopiaEDAILY News Ethiopia