
25/10/2023
አስፋው “ተሽሎኛል!” አለ!
አስፋው “ተሽሎኛል” የሚል መለዕክቱን አስተላልፏል። አስፋው ለውጥ አለው። ዛሬ ከወትሮው በተሻለ ጠንካራ መንፈስ ላይ ይገኛል። አሁንም ህክምናውን በጥሩ ሁኔታ እየተከታተለ ነው።
የህመሙን መሰረታዊ መንስኤወች ለማወቅና ተጓዳኝ ህመሞችን በሚገባ ለመለየት፣ ብሎም ተገቢውን የህክምና መፍትሄ ተፈጻሚ ለማድረግ ናሙናወች ተወስደው ተከታታይ ምርመራወች እየተደረጉለት ነው። በቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ብቃት ባላቸው የህክምና ባለሞያወች ጥሩ ህክምናን እያገኘ ነው።
ህክምናው እረፍትና ቋሚ ክትትል ስለሚያስፈልገው፤ እንደልብ ለመጠየቅና ለማየት አይቻልም። በጣም በርካታ የዲሲ፣ የቨርጂኒያና የሜሪላንድ ነዋሪወች፣ እንዲሁም ኢትዮጵያውያን የህክምና ባለሞያወች እንክብካቤ እናድርግለት ብለው ሆስፒታል መጥተው ከበር ተመልሰዋል። አስፋው ለሁሉም፤ በአካልም፣ በመንፈስም፣ በጸሎትም አብረውት ላሉት ምስጋና ይድረስ ብሏል።
አሁንም ለጊዜው ሆስፒታል ውስጥ ለመጎብኘት ስለማይፈቀድ ሁላችሁም በያላችሁበት በጸሎት አስቡኝ ብሏል። የበለጠ ሲያገግም እና ህክምናውን በማያስተጓጉል መልኩ መጠየቅ ሲቻል፣ እናሳውቃለን።
በአበበ ፈለቀ