
14/08/2025
✨💦 💫
✨በጋሞ ብሄረሰብ ባህል ግለሰቦች በማህበረሰቡ ውስጥ ማህበራዊ ደረጃ እንዲኖራቸው የሚሰጣቸው የመጀመሪያ ዕርከን የማዕረግ ስም ZUGA SUNTHA ይባላል፡፡
✨በዚሁ አጋጣሚ ZUGA SUNTHA የመጀመሪያ የማዕረግ ስሞች እና የአማርኛ አቻ ትርጉማቸው
👉 #አባ፦ ባህሩ፣ቻዩ፣ ታጋሹ፣ ሩኁሩህ፣
👉 #አፋ፦ ሰማዩ፣ ትልቁ፣
👉 #አሻ፦ ጥላው፣ ከለላው፣ አዳኙ
👉 #አይሳ፡-አሳዳሪው፣ ለጋሹ፣ ረዳቱ፣
👉 #ቦላ፡- የበላዩ፣ የተሻልከው፣
👉 #ቦርቃ፡- ገንዳሹ፣ ረፍራፊው፣
👉 #ጮልቦ፡- ጨማሪው፣ ሞልቶ ሰጪው
👉 #ጮሻ፡- አጥጋቢው፣ ጋባዡ፣
👉 #ዳዳ፦ መብረቁ፣ ኃይለኛው፣ ጀግናው፣
👉 #ዲቻ፡- አሳዳጊው፣ ተንከባካቢው፣
👉 #ሀርቃ፦ አርበጅባጁ፣ አጣሪው፣
👉 #ካራ፡- ውብ፣ ጥበበኛው፣
👉 #ካልሣ፡- መጋቢው፣ አጥጋቢው
👉 #ካማ፦ ጥላው፣ ከለላው፣
👉 #ካንሳ፡- ዘላቂው፣ ተቋቋሚው፣
👉 #ፔራ፡- አሟሟቂው፣ ቀስቃሹ
👉 #ፖሻ፡- ተርታራው፣ በታኙ፣
👉 #ቶልባ፦ እላፊ ሰጪው፣ ያለስስት ሰጪው፣
👉 #ሳሎ፡ ሰማዩ፣ ሩቅ አሳቢው፣
👉 #ሻራ፡ ደመናው፣ ንጹህ፣
👉 #ዎጋ፡- ታላቁ፣ የተከበርከው፣
👉 #ዎልቃ፡- መከታው፣ ጉልበቱ፣
👉 #ፄራ፦ ጠርዙ፣ ጫፉ፣ ከሁሉ የላቅከው፣
👉 #ፆና፦ አሸናፊው፣ ባለድሉ፣
👉 #የልኣ፡- አድባሩ፣ ሰብሳቢው፣
👉 #ዙማ፡- ተራራው፣ ከፍ ያልከው፣
💎ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ለሀገርና ለዞኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ " #አባ" የሚል የክብር ማዕረግ ስም በጋሞ አባቶች እንደተሰጣቸው ይታወሳል።👏
💎ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ደግሞ ለአንዲት ለተከበረች ፣ ለሀገሯ አስተዋጽአ ላበረከተች ሴት የሚሰጠውን " #እርጼ" የተሰኘ የማዕረግ ስም በጋሞ አባቶች ተሰጥተዋል ።💫
📷 firew abebe Habite