Christ prophecy internation church

Christ prophecy internation church Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Christ prophecy internation church, Film/Television studio, Addis Ababa.

10/12/2022
12/07/2022
21/10/2021

ይህንን አስተማሪ ፁሁፍ እድታነቡት ጋብዤቹሃለው።
ባሏን የገደለው 'መርዝ'
///////////////////////////
ከለታት አንድ ቀን አንዲት ውብ የሆነች ልጃገረድ ባገባች በ ሁለተኛው ዓመት ትዳሯ ምርር ስላላት ባሏን ለመግደል ፈለገች።
ይህች ቆንጆ ልጅት አንድ ቀን ጠዋት ወደ እናቷ ቤት ብርር ብላ በመሄድ፦ "እማዬ የባሌ ነገር አድክሞኛል የሚያደርጋቸው የማይረባ ነገሮች ሰልችተውኛል ለኔ አያስብልኝም ዞር ብሎ አያየኝም እኔንጃ ከሌላ ሴት ጋር የጀመረው ነገር አለ እርሱን ገድዬ መገላገል ፈልጋለው በሌላ በኩል ህግ ያስረኛል ብዬ እፈራለው እባክሽ እርጂን " አለቻት።
እናቷም "እሺ ውድ ልጄ እረዳሻለው ነገር ግን አንዳንድ የምታደርጊያቸው ነገሮች አሉ"። አለቻት።
ልጅቷም " አንቺ ያልሽኝን ሁሉ አደርጋለው አለች"
እናትየውም "ባልሽ ሞቶ ሬሳው ከቤትሽ እስከሚወጣ ድረስ ከዛሬ ጀምሮ የምታደርገውን 6 ነገሮች በጥንቃቄ ፈጽሚው አለች፦
1. የገደለችው እሷናት ብለው ጎረቤት እንዳይጠረጥሩሽ ከአሁን ሰዓት ጀምረሽ ከባልሽ ጋር ሰላም ፍጠሪ
2. ሁልግዜ ውበትሽን ጠብቀሽ ወጣትና ቆንጆ ሆነሽ ታይ
3. በደንብ አድርገሽ ተንከባከቢው ጥሩ ሁኚለት አበረታችው
4. ትዕግስት አድርጊ ብዙም አትቅኚ ብዙ ግዜ አዳማጭ ሁኝ በማክበር ታዘዥው
5.በእጅሽ ያለውን ገንዘብ ለእሱ ጥቅም ብቻ አድርጊው እንዲች ብለሽ ለራስሽ እንዳትጠቀሚ ገንዘብ ከከለከለሽ አትናገሪ ዝም በይ
6. ማንም ገድላዋለች ብሎ እንዳይጠረጥርሽ የጭቅጭቅና የጩኸት ድምፅ አታሰሚ ሰላምና ፍቅር ብቻ ከአፍሽ ይውጣ ... እስከ ምትገላገይው ድረስ ብቻ ነው።
እናትዮዋ፦ በድጋሚ "ሳታዛንፊ ያልኩሽ ታደርጊያለሽ?" አለቻት።
ልጅቷም " እሱ ብቻ ሞቶ ሬሳው ይውጣልኝ እንጂ አደርገዋለሁ" አለች።
እናትየዋም የሆነ ብልቃጥ እየሰጠቻት፦ " ይህንን መርዝ ያዥው ቀስ እያለ ውስጡን አመንምኖ እንዲገድለው በየቀኑ ምግቡ ውስጥ ጠብ እያደረግሽ ስጭው" አለች።
ልጅቷም ድስ እያላት ወደ ቤቷ ተመለሰች።
ከአንድ ወር ብሓላ ልጅቷ ወደ እናቷ ቤት ተመልሳ መጣች። እንዲህ አለቻት" ወይ ጉድ ሰውዬው ወሬ ሰምቶ ይሁን ወይ ቀልቡ ነግሮት? ድሮ ዞር ብሎ የማያየኝ ሰውዬ ፣ ፍቅሬ፣ማሬ ፣ወለላዬ፣ ህይወቴ፣ ንግስቴ፣ በዓለም ላይ የምታክልሽ ሴት የለችም ይለኝ ጀምሯል ብቻ እኔንጃ ጸባዩ ልውጥ አለብኝ"
እናትየውም፦ መርዙን እየሰጠሽው ነው? አለቻት
ልጅቷም አይኗ ላይ እንባ እየቀረረ ፦ አዎ ግን አሁን ጸባየ ሸጋ ጣፋጭ አፍቃሪ ባል ሆኗል እንዲሞትብኝ አልፈልግም ማርከሻ ሌላ መድሃኒት ካለ ፈልጊልኝ እባክሽ ጸጸቱ ሊገለኝ ነው።
እናትየዋ፦ ልጄ በብልቃጥ የሰጠሁሽ መርዝ አይደለም የእርድ ዱቄት ነው። ነገር ግን ቀስ በቀስ ጸባየ መጥፎውን ባልሽን የገደልሽው "መርዟ አንቺ ነሽ" ማለቴ እሱን ማፍቀር ፣ መታዘዝ፣ መንከባከብ፣ መታገስ፣ ማክበር እና ውብ ሆነሽ ስትገኚ ባልሽን መለወጥ ችለሻል። አንቺ ለሌላው ሰው ምንም ነገር ሳትሰጭ እንዴት ከሌላ ሰው ያልሰጠሽውን ትጠቢቂያለሽ? ፍቅር ማለት ሰጥቶ መቀበል ነው። ቅድሚያ ግን መስጠት ያስፈልጋል ፍቅር ከሰጠሽው ፍቅር ታገኝያለሽ ጸብና ጭቅጭቅ ይዘሽ የምጠብቂው ከሆነ ያንኑ ታገኛለሽ።ምላሽ ሳትጠብቂ ከራስሽ አስበልጠሽ በሁሉም ነገር ባልሽን አስቀድሚ ፍቅር ስጭው!!!

15/10/2021

ሃያ ምርጥ የማርቲን ሉተር አባባሎች
1. ‹‹ ሕልም አለኝ! ››
2. ‹‹ መብረር ካልቻልክ ሩጥ፡፡ መሮጥ ካልቻልክ ተራመድ፡፡ መራመድ ካልቻልክ ዝግ ብለህም ቢሆን ሂድ፡፡ ምንም ነገር ስታደርግ ወደፊት መሄድህን አታቋርጥ፡፡ ››
3. ‹‹ ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ ጊዜ ሁል ጊዜ ትክክለኛው ሠዓት ነው፡፡ ››
4. ‹‹ ከፍቅር ጋር ለመጣበቅ ወስኛለሁ፡፡ ምክንያምቱም ጥላቻ ሊሸከሙት የማይችሉ ታላቅ ቀንበር ነውና፡፡ ››
5. ‹‹ በስተመጨረሻ ከጠላቶቻችን ንግግር ይልቅ የወዳጆቻችንን ዝምታ ነው የምናስታውሠው፡፡ ››
6. ‹‹ በየትኛውም አካባቢ ያለ ህገወጥነት ለዓለም ፍትህ አደጋ ነው፡፡ ››
7. ‹‹ እምነት ምንም እንኳን ሙሉው የሕይወት መሰላል ባይታይህም የመሠላሉን የመጀመሪያውን እርካብ መርገጥ ነው፡፡ ››
8. ‹‹ እውነተኛው የትምህርት ዓላማ አዋቂነት እና መልካም ባህሪን አንድ ላይ ማድረግ ነው፡፡ ››
9. ‹‹ የማያልቀውን ተስፋ አጥብቀን በመያዝ የበዛውን ውድቀታችንን በፀጋ መቀበል አለብን፡፡ ››
10. ‹‹ ብርሃን ጨለማን ያሸንፋል እንጂ ጨለማ ጨለማን አይገፍም፡፡ ጥላቻም በጥላቻ አይሸነፍም፡፡ ያን ማድረግ የሚቻለው ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ››
11. ‹‹ በዓለም ላይ ከመሃይምነት እና ከጅልነት የበለጠ አደገኛ ነገር የለም፡፡ ››
12. ‹‹ ጠላትን ጓደኛ ማድረግ የሚችለው ሃያሉ ፍቅር ብቻ ነው፡፡ ››
13. ‹‹ ማንም ሠው ቢሆን ሕገወጥ ለሆኑ ህጎች ያለመገዛትና ያለመታዘዝ ሞራላዊ ሃላፊነት አለበት፡፡ ››
14. ‹‹ ሁላችንም አብረን ተስማምተን ለመኖር መማር አለብን፡፡ አልያ ግን ልክ እንደ ጅል እርስበራስ መጨራረስ ሊኖርብን ነው፡፡ ››
15. ‹‹ ይቅርታ ማድረግ በሆነ ጊዜ ላይ ብቻ የምናደርገው ሳይሆን ቋሚ የሆነ የሁልጊዜ አመለካከት መሆን አለበት፡፡ ››
16. ‹‹ በዓለም ላይ እንደ ፍቅር ፅኑ እና ቋሚ ሃይል ምንም የለም፡፡ ››
17. ‹‹ ታሪክ ሠሪዎች ሳንሆን በታሪክ የተሠራን የታሪክ ፍጡራን ነን፡፡ ››
18. ‹‹ ጥላቻ ጠዪውን አጥፊ ነው፡፡ ››
19. ‹‹ ነፃነት በጨቋኞች ነቃ ፈቃድ የሚገኝ ሳይሆን በጭቁኖች የሚፈለግና ሚጠየቅ ነው፡፡ ››
20. ‹‹ ክዋክብቶችን ማየት የሚቻለው በጨለማ ብቻ ነው፡፡ ››

09/09/2021

* ለደቂቃዎች ይህን ማንበብ
ለዘላለም ሕይወትህን ይለዉጣል!
በኢዩኤል ዮሐንስ ( Eyuel J Yohanne )

በርግጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ይማልዳል ?
' የእግዚአብሔር በግ '

ነቢዩ ኢሳያስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር ከመምጣቱ ከሰባት መቶ ዓመት በፊት በመገለጥ ዝም ብሎ ለመታረድ እንደሚሄድ በግ አየዉ :- ' ለመታረድ እንደሚነደ ጠቦት ፥ በሸላቶቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ ፥ እንዲሁ አፋን አልከፈተም ' ኢሳ 53 : 7 ከሰባት መቶ አመት በሗላ መጥምቁ ዮሐንስ ክርስቶስ ኢየሱስን የዓለምን ሁሉ ሐጢአት እንደተሸከመ የእግዚአብሔር በግ አየዉ ጮህም ለሰዎችም የዓለምን ሁሉ ሐጢአት የተሸከመ/ የሚያስወግድ እዉነተኛ የእግዚአብሔር በግ አለ ( ዮሐ 1 : 36 ) በሶስተኛ ደረጃ ሐዋሪያዉ ዮሐንስ ጌታ ኢየሱስን በሰማይ እንደታረደ በግ ቆሞ አየዉ :- ' በዙፈኑ እና በአራቱ እንሰሶች መካከል በሽማግሌዎችም መካከል እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ ፥ ' ራዕ 5 : 6 ሚስጥሩ ያለዉ እዚህ ጋር ነዉ ? ' የታረደ በግ ' እንዴት ይቆማል ?! በግ ሲታረድ ይወድቃል እንጂ አይቆምም ሐዋሪያዉ ዮሐንስ ጌታ ኢየሱስን እንደ ታረደ በግ በሰማይ ቆሞ ሲያየዉ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ለዘላለም ሕያዉና የሚሰራ ( Alive and Active ) እንደሆነ በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሁሉ ሊያድን እንደሚችል ነዉ ያየዉ ፤ ብዙ ሰዎች እዚህ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ ' ኢየሱስ ክርስቶስ የነገስታት ንጉስ የጌቶች ጌታ አምላክ ሆኖ ወደ ማን ነዉ የሚማልደዉ ' ይላሉ ስለ እግዚአብሔር ( Godhead ) ስለ ኢየሱስ መለኮትነት ( his DIVINITY ) እና ሰዉነት ( his HUMANITY ) ካወቅን ለዚህ ጥያቄ መልስ እናገኛለን . ኢየሱስ ክርስቶስ የዛሬ ሁለት ሺ ዓመት ሰዉ ሆኗል ( he became a GOD - MAN forever) ከሞት ከተነሳም በሗላ የትንሳኤ አካልን ( RESURRECTED /GLORIFIED BODY ) ለብሶ ለዘላለም በሰዉነቱ የመለኮት ሙላት ተሸክሞ ይኖራል ( The fullness of DEITY lives in him BODILY FORM ) ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር ያስታረቀን የሚያስታርቀን በሰዉነቱ ነዉ ፤ አንድ ጊዜ በመስቀል ላይ ደሙን ለዘላለም አፍስሶ ( once and forever ) ለዘላለም እኛን ለማዳን ሕያዉ ሆኖ ይኖራል !ይህም ብቻ አይደለም ሁል ጊዜ ( 24/7 ) በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ እየታየ በድካማችን ሁሉ የሚራራልን ታላቁ ሊቀ ካህናችን ፤ ሰለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ጠበቃ (Advocate,mediator and lawyer ) ሆኖ ለዘላለም ይኖራል ! ለምን እንደ ሆነ አላዉቅም ' ማስታረቅን ' ብዙ ሰዎች ከትንሽነት ጋር ያያዙታል ነገር ግን ሰዉን ከሰዉ ፣ መሪዎችን ከመሪዎች እና ሃገርን ከሃገር ያስታረቁ ትልቅ እንጂ በምንም ሂሳብ ትንሽ ሊባሉ አይችሉም ! ኢየሱስ ክርስቶስ ሰማይን ከምድር ያስታረቀ ( Universal Reconciler ) ነዉ ስንል ' ' ለምን ክብሩን ዝቅ ታደርጋላቹ ይሉናል ? ' እዉነቱ ግን ከዚህ በጣም የተለየ ነዉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመዋጀት ( Redemption ) ስራ ሲሰራ የመጨረሻ ክብሩን የገለጠዉ ሰማይና ምድርን በመፍጠሩ ሳይሆን ጥልቁ ጥበቡና ሃይሉ የተገለጠዉ የሰዉ ልጆችን በመስቀል ላይበማዳኑ ነበር :: በነገራችን ላይ ኢየሱስ ከርስቶስ ብዙ ስሞች እያሉት በ ራዕይ 21 እና 22 መሰረት ለዘላለም መጠሪያ አድርጓ የመረጠዉ ስም :- ' በጉ ' ወይም ' የእግዚአብሔር በግ ' የሚለዉ ነዉ ይህም ማለት እርሱ እንደ ሕያዉ የእግዚአብሔር በግ መስዋዕት የሆነልንን የመስዋትነቱን ስራ እንዳንረሳ ለዘላለም ' የእግዚአብሔር በግ ' የሚል ስም ይይዛል ኢየሱስ ክርስቶስ ድል የነሳዉ ያሻነፈዉ ታርዶ መስዋት ሆኖ ነዉ!

9-10 መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥

ክብር ለታረደዉ መስዋት ለሆነዉ ለእግዚአብሔር በግ!
Worthy is the lamb!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Christ prophecy internation church posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share