Eyob Media Agency

Eyob Media Agency Eyob Media Agency Focuses all Creating an open and free discussion platform be exploring current and
(1)

16/03/2024

ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል!
ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት ይሰጣል!
************
ለውድ የባንካችን ደንበኞች በሙሉ፡

በሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቅርንጫፎች አገልግሎት የጀመረ መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችን እየገለፅን፣ የባንኩ ቅርንጫፎች ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጡ እናሳውቃለን፡፡

በተመሳሳይ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን (ኢንተርኔት ባንኪንግ፥ ሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም ሲቢኢ ብር) ለማስጀመር እየሠራን መሆኑን እየገለፅን፣ ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል በድጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን።

ይህ የምትመለከቱት ወጣት እናቱን በምታዩት መንገድ ሲረዳ በገጠመኝ አይቼው ነው፤ እናም ይህ ወጣት ለዘመኑ ወጣት አርአያ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በቀጣይ ሙሉ ቪዲዮውን አስጎበኛችኋለሁ።
31/08/2023

ይህ የምትመለከቱት ወጣት እናቱን በምታዩት መንገድ ሲረዳ በገጠመኝ አይቼው ነው፤ እናም ይህ ወጣት ለዘመኑ ወጣት አርአያ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በቀጣይ ሙሉ ቪዲዮውን አስጎበኛችኋለሁ።

TikTok

አትሌቶቻችን የዓለም መታወቂያዎቻችን ከመሆናቸውም በላይ የሀገራችን የከፍታ ዘመን መንደርደሪያ ሆነዋል፦ እንክብካቤና አድናቆት ሊሰጣቸው ይገባል ። የመታወቂያችን ባለቤት ፈጣሪ ይመስገን፤Eyob...
26/08/2023

አትሌቶቻችን የዓለም መታወቂያዎቻችን ከመሆናቸውም በላይ የሀገራችን የከፍታ ዘመን መንደርደሪያ ሆነዋል፦ እንክብካቤና አድናቆት ሊሰጣቸው ይገባል ።
የመታወቂያችን ባለቤት ፈጣሪ ይመስገን፤
Eyob Media Agency
ነሐሴ 20_2015 ዓ.ም

24/08/2023

በለው ግፋ እያልነው ጥይት የሚጠብሰው ፥
እየገፋ በላን እዴት አይለይም ሰው ፥
Eyob Media Agency
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 18_2015 ዓ.ም

15/08/2023

ሊቁ ጠበብተኛው መድኀሐኒት ያጣልሽ
እምዬ ኢት/ያ ኧረ የቱ ጋ ነው ስውሩ ህመምሽ
እንደው ተያይዘን ሳናልቅ ለጆችሽ
በገባልሽ ኪዳን በፈጠረን አምላክ በአብ ልማፀንሽ
መመኪያዬ ሀገሬ ንገሪኝ እማማ ምንሽንነው ያመመሽ

"እኔ ለሀገሬ መድሐኒት እንጂ ራስ ምታት አልሆንም"
Eyob Media Agency
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም

12/07/2023

ሀገር የሚጠበቀውና የሚበለፅገው በዜጎች አንድነትና የጋራ ርብርብ እንጂ በመንግስትና እንደራሴዎች ጫንቃ ላይ ብቻ ተወስኖ አይደለምና ዜጎች ተግባብተንና ተባብረን በመስራት አሁን ያለውን የሰላምና የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ለመቀየርና ሠላም ሰፍኖ ኢኮኖሚው እንዲሻሻል የበኩላችንን ድርሻ እንወጣ። ያለንባት ምድርና ሀገር መኖሪያችንም ማረፊያችንም ይህችው ኢትዮጵያ ናትና ለራሳችንና ለመጪው ትውልድ መልካሙን ለማቆየት እንትጋ እንጂ ለስልጣን ጥመኞችና በወሬ ገቢያቸውን ለሚያጧጡፉ ባንዳዎች መሳሪያ አንሁን ።
"ሠላምና ልማትን ለሀገር ኢትዮጵያ እንመኝ"
Eyob Media Agency
ሐምሌ 05_2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

30/06/2023

ሀገር መውደድ የጥቅመኞች ኘሮፖጋንዳና እውነታውን በመለየት የዜግነት ድርሻን መወጣት ሲቻል ነውና፤ አስተውለን አንመንዝረውና ለሰላም ተግተን እንስራ።
Eyob Media Agency
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ሰኔ 22_2015 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ሀገራችን ያጣችው አንድ ነገር ቢኖር የምሁራኖቿ  ሀገር ፍቅር አልባ ግን ደግሞ በስልጣን ፍቅር በመታወር ማስተዋላችንን የተነጠቅን ካልሆነ በስተቀር የጎደለን አለ ለማለት ያዳግታልና ...
11/05/2023

ኢትዮጵያ ሀገራችን ያጣችው አንድ ነገር ቢኖር የምሁራኖቿ ሀገር ፍቅር አልባ ግን ደግሞ በስልጣን ፍቅር በመታወር ማስተዋላችንን የተነጠቅን ካልሆነ በስተቀር የጎደለን አለ ለማለት ያዳግታልና ቅድሚያ ለሀገርና ለዜጎች ሰላም ብንጨነቅ መልካም ነው እንላለን።

04/03/2023

A Symbol of African People's Independence.The Pride and Honor of Ethiopianism.Happy 127th Adwa Victory Day!

10/12/2022

አሁን ላይ ለሀገራችንና ዜጎቿ የማይበጅ ለእርስ በርስ ግጭት የሚያነሳሳ ጎራ የለየ አስተያየትና ትችት ለዜጎች ከማሰብና ከመቆርቆር የሚመነጭ
ሐሳብ ሳይሆን ሀገር የማፍረስ የባንዳነት ተግባር ስለሆነ እባካችሁ ተቆጠቡ፤ ዜጋውን የሚበላ አውሬ አንሁን ፦

03/12/2022

ሚዛኑን ያልጠበቀ ትችት ትርምስን ማስቀጠል ይሆናል ፤
ኢትዮጵያን እንቃኛት
ለውጡን ተከትሎ ሀገራችን ዘርፈ ብዙ ሁከትና አለመረጋጋቶችን አርግዛና ምጧ ፀንቶ በጭንቀት ሳትገላገል እስከ አሁን ድረስ መቆየቷ የገሀዱ ዓለም እውነታ ነው ።
የኑሮው ውድነትና የገበያው መቃወስም እንዲሁ ፤
በዚሁ መካከል ደግሞ የሚታዩ በርካታ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት ውጤቶች ተመዝግበዋል ሲባል ማንም አስታዋይ ግለሰብ ሊያረጋግጠው የሚችለው በሀገሪቱ የተሰሩ ስራዎች መሬት ላይ ያሉ ውጤቶች ናቸው ።
ታዲያ አንዳንድ ተንታኞችና አዋቂዎች ነን የሚሉ ግለሰቦች መንግስት ለውጥ ማምጣት እንዳልቻለ ፤ ሀገሪቱን የመለወጥ እንቅስቃሴም እንደሌለና ሪፍርም እንደዘገየም ሲተነትኑ ይደመጣል ።
ከሚያሳዝነው ደግሞ ዛሬም ክልልና ብሄር ተኮር ችግሮችን እንደ ማቀጣጠያ ቤንዚን መጠቀምም ይስተዋላል ።
ማንም ሀገር የመምራች አቅም ያለው ምሁር ቢኖር ምናልባት አንዳች የተለየ ምትሃታዊ ተዓምር እሰራለሁ የሚል ካልተከሰተ በስተቀር ባሳለፍናቸው የለውጡ ዓመታቶች የውስጥና የውጪውን ጦርነት ፤ ህዝብና መንግስትን ለማጋጨት የተሰገሰጉ ያልተጣሩ የሁት ዓለም በየደረጃው ያሉ የመንግስት አመራር አካላትን ነውጥ ፤ የጊዜውን ዓለም አቀፍ ወረርሽን በሽታና አይን ያወጣ ፈቃድ የተሰጠው የሚመስል ሙስናና ዘረፋ ተቋቁሞ ከዚህ የተሻለ ውጤት ሊያስመዘግብ የሚችል ሌላ ጥበበኛ አካል አለ ለማለት ነብይ መሆንን ይጠይቃል ።
ጦርነቱ ቆሟል ሲባልም ተጠናቋል የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰን መናገርም የግንዛቤ ጉድለት እንዳለ ያመላክታል ።
ምክንያቱም በጦርነቱ የወደመውንና የተፈናቀለውን መልሶ ማቋቋም በራሱ የጦርነቱ አለመጠናቀቅ አንዱ አካል ነውና ፤
ከዚሁ ጋር የተያያዘው የትጥቅ ማስፈታትና ያንን ሰራዊት በተሃድሶ ቀይሮ ቦታ ማስያዝና ማቋቋም በራሱ ጦርነት ነው ።
ለዚህ የውስጥ ሆዳሞችና ባንዳዎችም ይንኑ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም አለመረጋጋቱን ለማስቀጠልና መንግስትን ለማዳከም እንቅልፍ ሲያጡ የሚታዩት ።
በመሆኑም የፓለቲካ ተንታኞች የሀገር ውጥ የውጪ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች እውነቱን የማየትና የማመዛዘን ኃላፊነት እንዳለብን አስታዋሽ ስለማያስፈልገን ሀገራዊ የለውጥ አቅጣጫ ጠቋሚዎች መሆናችንን ሳንዘነጋና የምንሰጣቸውን የተዛቡ አስተያየቶች አርመን ለሀገር ለውጥ በፀዳ አዕምሮ ልንሰራ ይገባናል እንላለን ።
ዜጎቻችን በእርግጥ ሁሉን የለዩበትና እውነቱን ያረጋገጥንበት ወቅትና አስቻጋሪውን ትርምስ እየተሻገርነው መሆናችንን የተገነዘብን ለአተራማሽ ወሬ ጆሮ የማንሰጥ ህዝቦች ለመሆናችን ማረጋገጫው ለዛሬው ውጤት መድረሳችን ምስክር ነው የሚል እምነት አለን ።
ቀጣዩ ሪፎርም ሁሉን የዳሰሰ ለኢትዮጰያ ሽግግር ፋና ወጊ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን ።
የኢኮኖሚ ና ፖለቲካዊ ለውጥ ቅደም ተከተልን ስንገመግም ካለፈው ስርዓት ጋር ማነፃፀር ሳይሆን ጠቀሜተውን ማየት ተገቢና አዋቂነት ነው ። ምክንያቱም ሁለቱም የማይነጣጠሉና በአንድነት የሚከወኑ እንጂ አንዱ ባለበት ቆሞ አንዱ የሚከወን እንዳልሆነ ለመረዳት ትምህርት አይጠይቅምና ነው ።
"ሰላምና ብልፅግናለኢትዮጵያ"
Eyob Media Agency
ህዳር 24_2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eyob Media Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share