Halala Media Network-HMN

Halala Media Network-HMN ይህ የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ፣ ወቅታዊ፣ፖለቲካዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን ወደ እናንተ ለማድረስና ለዳውሮ ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ድምጽ ለመሆን የተከፈተ ነው።

ለታርጫ ከተማ ውበትና ዕድገት መሠረት የጣለ ድንቅ ከንቲባ  እናመሰግናለን!
25/06/2025

ለታርጫ ከተማ ውበትና ዕድገት መሠረት የጣለ ድንቅ ከንቲባ

እናመሰግናለን!

የዳውሮ ወርቅ፣ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ❤
21/06/2025

የዳውሮ ወርቅ፣ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ❤

 !ዳውሮ ዛሬም በምሁራን መፍለቂያነቷ ቀጥላለች። በዛሬው ዕለት አንድ ዶክተር (PhD) ከጅማ ዩኒቨርስቲ ተገኝቷል። ዶ/ር ጎዳዬ ጎበና ይባላል። እንኳን ደስ አልዎት ዶ/ር!
17/06/2025

!

ዳውሮ ዛሬም በምሁራን መፍለቂያነቷ ቀጥላለች። በዛሬው ዕለት አንድ ዶክተር (PhD) ከጅማ ዩኒቨርስቲ ተገኝቷል። ዶ/ር ጎዳዬ ጎበና ይባላል። እንኳን ደስ አልዎት ዶ/ር!

  ዶ/ር ብርሃኑ ብላቴ፣ የደ/ም/ኢ/ህ/ክልል ምርጥ ዘር ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል።እንኳን ደስ አልዎት!
17/06/2025


ዶ/ር ብርሃኑ ብላቴ፣ የደ/ም/ኢ/ህ/ክልል ምርጥ ዘር ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል።
እንኳን ደስ አልዎት!

  😭😭😭😭በዛባ ጋዞ ወረዳ የጋራዳ እንታላ ቀበሌ ተወላጅ የሆነች እህታችን አበባየሁ በልቻ፣ በአሳዛኝ ሁኔታ መንትያ ልጆቿን እየወለደች በመንገድና እጦት ምክንያት የህክምና እርዳታ ሳታገኝ በመ...
15/06/2025

😭😭😭😭

በዛባ ጋዞ ወረዳ የጋራዳ እንታላ ቀበሌ ተወላጅ የሆነች እህታችን አበባየሁ በልቻ፣ በአሳዛኝ ሁኔታ መንትያ ልጆቿን እየወለደች በመንገድና እጦት ምክንያት የህክምና እርዳታ ሳታገኝ በመቅረቷ ሕይወቱዋ አልፏል። የመጀመሪያ ልጇን ለመውለድ ወደ እናቷ ቤት በሄደችበት ወልዳ ሳትታረስ የቀረችው እህታችን ናት ወ/ሮ አበባየሁ።

ዛባ ጋዞ ወረዳ በዞኑ በመንገድና በመሠረተ ልማት እጦት ህዝቡ ላይ ዘርፈ ብዙ ጉዳት የሚደርስበት እጅግ ትኩረት የተነፈገ አካባቢ ነው። ትኩረት ለዛባ ጋዞ ህዝብ! እህታችን ነፍሷን ይማር፤ ለቤተሰቦቿም መጽናናትን ይስጥ።

የዲዛይን ተመሳሳይነት ያላቸው የደቡብ ምዕራብና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቢሮዎችነገሩ እንዴት ነው ግን?
13/06/2025

የዲዛይን ተመሳሳይነት ያላቸው የደቡብ ምዕራብና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቢሮዎች

ነገሩ እንዴት ነው ግን?

በ90ዎቹ የተቆረቆረች፣ በምቹ መልከዓ ምድር ላይ ያረፈች፣ ለኑሮና ኢንቨስትመንት ተመራጭ የሆነች፣ በፈጣን ዕድገት ላይ የምትገኝ ውቢቷ  #ታርጫ ከተማ
12/06/2025

በ90ዎቹ የተቆረቆረች፣ በምቹ መልከዓ ምድር ላይ ያረፈች፣ ለኑሮና ኢንቨስትመንት ተመራጭ የሆነች፣ በፈጣን ዕድገት ላይ የምትገኝ ውቢቷ #ታርጫ ከተማ

በሳልና ልዩ የአመራርነት ብቃት የተካኑ የተከበሩ አቶ ዳዊት ገበየሁ፣ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የብልጽግና ፓርቲ ም/ቤት አባል፣እናከብርሃለን!
09/06/2025

በሳልና ልዩ የአመራርነት ብቃት የተካኑ የተከበሩ አቶ ዳዊት ገበየሁ፣ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የብልጽግና ፓርቲ ም/ቤት አባል፣

እናከብርሃለን!

26/05/2025

በዳውሮ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የ NGO project ገንዘብ ለግል ጥቅም በግለሰቦች አየተመዘበረ እንደሆነ ብዙ መረጃ እየወጣ ይገኛል። ችግሩ ጫፍ ከወጣባቸው አከባቢዎችም አንዷ የማሪ ማንሳ ወረዳ ናት።

04/05/2025

የህወሓት ህጋዊ ሰውነት በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት እንዲመለስለት የፓርቲው መካከለኛ እና ከፍተኛ አመራሮች ጠየቁ

በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው የህወሓት ጎራ መካከለኛ እና ከፍተኛ አመራሮች፤ ፓርቲው ዳግም ምዝገባ እንዲያካሄድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተላለፈውን ትእዛዝ በመኮንን፤ ህጋዊ ሰውነቱ በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት እንዲመለስለት ጠየቁ። እነዚሁ አመራሮች በክልሉ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትን ያቀፈውን የጊዜያዊ ምክር ቤት ህልውና እንደማይቀበሉትም አስታውቀዋል።

የፓርቲው አመራሮች ይህን ያስታወቁት፤ ከሐሙስ ሚያዝያ 23 ጀምሮ በመቐለ ከተማ በሚገኘው የሰማእታት ሃውልት አዳራሽ ሲያካሄዱት የቆዩትን ስብሰባ በትላንትናው ዕለት ሲያጠናቀቁ ባወጡት የአቋም መግለጫ ላይ ነው። “ብሔራዊ አንድነታችን ሉአላዊነታችን ለማረጋገጥ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ ስብሰባ፤ 1,337 የፓርቲው መካከለኛ እና ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል ተብሏል።

የስብሰባው ተሳታፊዎች በስብሰባቸው ማጠቃለያ ባወጡት ባለ 10 ነጥብ የአቋም መግለጫ ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ የህወሓት የህጋዊ ሰውነት የማግኘት ጉዳይ ነው። ህወሓት 50 ዓመት የሞላው እና “በህዝቡ ልብ የታተመ” መሆኑን በመግለጫቸው የጠቆሙት አመራሮቹ፤ የፓርቲው እውቅና “በትግራይ ህዝብ የሚወሰን ነው ብለን እናምናለን” ሲሉ አቋማቸውን አስታውቀዋል።

ከፕሪቶሪያ ስምምነት በተቃራኒ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን በድጋሚ ለመመዝገብ የሚያደርገውን ተደጋጋሚ ሙከራ እንደሚያወግዙም አመራሮቹ በአቋም መግለጫቸው ላይ አስፍረዋል።

🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15799/

ህወሃት የፌደራል መንግስት በትግራይ ሉዓላዊ ምድር ላይ የወረረውን የታጠቁ ሃይሎች  እና ሰፋሪዎች በአስቸኳይ እንዲያስወጣ ጠየቀ!የትግራይ ህዝብ ወረራውን በጠንካራ አገራዊ አንድነት በመታገል ...
03/05/2025

ህወሃት የፌደራል መንግስት በትግራይ ሉዓላዊ ምድር ላይ የወረረውን የታጠቁ ሃይሎች እና ሰፋሪዎች በአስቸኳይ እንዲያስወጣ ጠየቀ!

የትግራይ ህዝብ ወረራውን በጠንካራ አገራዊ አንድነት በመታገል ህልውናውንና ግዛቱን አረጋግጧል። የትግራይ ህዝብ ከትናንት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ታግሏል፣ አሁንም እየተዋጋቸውም ያሉትም የትግራይ ተወላጆችን ለማንበርከክ፣ ህልውናው ለመንጠቅና መሬቱ እንዲነጠቅ በማሰብ ወደ ሀገራቸው የገቡትን ወራሪዎችን ነው"ብሏል።

ህዝባችን በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ እያለ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ስልጣን የተቆጣጠረው ከሃዲ ቡድን ተልእኮውን ከመወጣት ይልቅ የትግራይን አንድነትና አቅም የማደፍረስ ግልፅ ተልዕኮ ይዞ እየሰራ ነው ሲል ወንጅሏል።

ይህ ቡድን አሁንም ከትግራይ ህዝብ ህልውና ውጭ ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት ከመሰረታዊ አጀንዳችን በማፈንገጡ የትግራይን ህዝብ ተወያይቶ የማስፈፀም አቅምን በማዳከም ላይ ይገኛል ብሏል።

በፕሪቶሪያ ስምምነት በጠላት ስር ለሚኖረው ህዝባችን ነፃ ለማውጣት፣ በስደትና በስደተኛ ካምፖች የሚገኙ ወገኖቻችን በሰላም እንዲመለሱ እና የትግራይ ሉዓላዊ መሬት እንዲረጋገጥ መስራት የሁሉም ቀዳሚ አጀንዳ ነው። ስለሆነም የፌደራል መንግስት በትግራይ ሉዓላዊ ምድር ላይ የወረረውን የታጠቁ ሃይሎች እና ሰፋሪዎች በአስቸኳይ እንዲያስወጣ በወራሪው ሀይል ህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይና ሞት ለማስቆም በገባው ስምምነት መሰረት እንዲወጣ እንጠይቃለን"ብሏል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Halala Media Network-HMN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share