
05/07/2025
◾️የኤርትራ ሪፈረንደም(April 23-25/1993 (ሚያዚያ 15-17/1985)
➢➢➢➢➢➢➢➢➢➢➢➢➢➢➢➢➢➢➢
#በነዚህ ቀናት የኤርትራን ነፃነት ያረጋገጠው ህዝበ ውሳኔ ተካሄደ። በሪፈረንደሙ ከተሳተፈው ህዝብ መካከል ከ98% በላይ የሚሆነው ኤርትራ ነፃ ሀገር እንድትሆን ድምፁን ሰጥቷል። በሕዝበ ውሳኔው ድምፅ በመስጠት ቀዳሚ የሆኑት ኤርትራ ነፃ ሀገር እንድትሆን ለሀምሳ ዓመታት የታገሉት ኦቦይ ወልደኣብ ወልደማሪያም ነበሩ።
#የኤርትራን ነፃነት በተመለከተ እስከ አሁን ድረስ ሁለት የተሳሳቱ ትርክቶች ይነገራሉ። አንደኛው ትርክት "በሪፈረንደሙ ለህዝቡ የቀረበው አማራጭ "ከነፃነት እና ከባርነት የትኛውን ትመርጣለህ?" የሚል ነበር" እየተባለ የሚነገረው ነው። ይህ ማስረጃ የሌለው የፈጠራ ወሬ ነው። በዚያ ሪፈረንደም ለህዝቡ የቀረበው የማማረጫ ጥያቄ "ኤርትራ ነፃ እና ሉዓላዊት ሀገር እንድትሆን ትደግፋለህን?" የሚል ነው። ህዝቡም "እደግፋለሁ" ወይንም "አልደግፍም" ከሚሉት መልሶች አንዱን ይሰጣል። በዚህም መሠረት የኤርትራን ነፃነት የደገፈው ወገን አሸንፏል።
Ethiopian History and Tourism/የኢትዮጵያ ታሪክና ቱሪዝም