Ethio Islamic page

Ethio Islamic page ኢትዮ ኢስላማዊ ገፅ

17/08/2024

እውነተኛ ደስታ

ታናሽ እህት ያለችህ ያለችሽልጅ ያለህ ሰብአዊነት የሚሰማው ሁሉ ለዝህች ተጫውታ ላልጠገበች ሲርባት እንኩን በስርዓት መናገር ለማትችል ህመሙውን ማስረዳት ተስኑዋት ተደፍራ ተገድላ ለሞተችው ህፃ...
17/08/2024

ታናሽ እህት ያለችህ ያለችሽልጅ ያለህ ሰብአዊነት የሚሰማው ሁሉ ለዝህች ተጫውታ ላልጠገበች ሲርባት እንኩን በስርዓት መናገር ለማትችል ህመሙውን ማስረዳት ተስኑዋት ተደፍራ ተገድላ ለሞተችው ህፃን ድምፅ እንሁናት

ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን ሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ ሚቅባስ ወደ አኼራ ሄዱየታዋቂው የእስልምና ሊቅ ሙጃሂድ ሸይኽ ሰዒድ ሙሐመድ ቡዴላ (የአብሬት ሸህ) ልጅ የነበሩት ሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ ሚ...
14/08/2024

ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን

ሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ ሚቅባስ ወደ አኼራ ሄዱ

የታዋቂው የእስልምና ሊቅ ሙጃሂድ ሸይኽ ሰዒድ ሙሐመድ ቡዴላ (የአብሬት ሸህ) ልጅ የነበሩት ሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ ሚቅባስ ኑር ወደ አኼራ ሄደዋል::

ሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ ሚቅባስ በርካታ ኪታቦችን የፃፉ ሲሆን በርካታ ደረሶችንን ያቀሩ አሊም ነበሩ::

በአዲስ አበባ መግቢያ ላይ ወለቴ በተባለ አካባቢ ነዋሪ የነበሩ ሲሆን እውቅ የባህል ህክምና አገልግሎት በመስጠትም የሚታወቁ ነበሩ::

ከዚህ ቀደምም በመሪነት ህይወታቸው ለ11 ዓመት ያህል እነሞርና ችሃን ከማስተዳደር ባሻገር “ጉንቺሬ” የምትባልን መንደር መስርተዋል፡፡

የአባታቸውን ፈለግ በመከተል የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ የነበሩ አሊም ሲሆኑ በዛሬው እለት ወደ አኼራ ማለፋቸው ታውቋል::

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው ፣ለተማሪዎቻቸው እና ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ አላህ መፅናናቱን ይወፍቅ

ለሸይኽ ሰይድ ሙሐመድ ሚቅባስም መልካም ስራቸውን አላህ እንዲቀበላቸው፣ ምህረቱንም እንዲለግሳቸው፣ በጀነተል ፊርዶስም ማረፊያቸውን እንዲያደርግላቸው አላህን እንማፀነዋለን

ሰዎች ሆይ! በፍቅሩ ወድቃችሁ! ታሪኩን ሁሌም የምትናፍቁለት! ምልጃውን የምትከጅሉትን ዕንቁ ነቢይ ላይ ሶለዋት አውርዱ!💛❤❤አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዐለይህ!❤♥ #ሼር
14/08/2024

ሰዎች ሆይ! በፍቅሩ ወድቃችሁ! ታሪኩን ሁሌም የምትናፍቁለት! ምልጃውን የምትከጅሉትን ዕንቁ ነቢይ ላይ ሶለዋት አውርዱ!💛❤

❤አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዐለይህ!❤♥

#ሼር

  🥰 ------
13/08/2024

🥰
-
-
-
-
-
-

ረሱል ሰለላሁ አለይህ ወሰለም 👍🥰
13/08/2024

ረሱል ሰለላሁ አለይህ ወሰለም 👍🥰

የዙህር ሰላት ደርሶ ቢላል አዛን እያደረገ ነው። ነቢም ሰ ዐ ወ እያደመጡ ነበር። የቢላልን አዛን እየተከተለ እዛን የሚል ሰው ድምፅ ከርቀት ይሰማል። ቢላል አዛኑን ካጠናቀቀ በኋላ ረሱል ሰዐ...
12/08/2024

የዙህር ሰላት ደርሶ ቢላል አዛን እያደረገ ነው። ነቢም ሰ ዐ ወ እያደመጡ ነበር። የቢላልን አዛን እየተከተለ እዛን የሚል ሰው ድምፅ ከርቀት ይሰማል።

ቢላል አዛኑን ካጠናቀቀ በኋላ ረሱል ሰዐወ፦‹‹ማን ነው አዛን ሚለው ከወደ ውጭ በኩል? ›› ሲሉ ጠየቁ። አባ መሕዙራ የተባለ እረኛ በማላገጥ ስሜት አዛን እያለ ግመሎቹን እንደሚያግድ ነገሯቸው።

ረሱልም ሰዐወ በተረጋጋ ስሜት ይህ ሰው ተይዞ እሳቸው ዘንድ እንዲቀርብ ዐሊይን እና ዙበይርን ላኳቸው። ሁለቱም ወደተላኩበት ሂደው አላጋጩን ከነ ግብረ-አበሮቹ ጠፍረው አመጧቸው።

ሁሉም አቀርቅረው ረሱል ሰዐወ ፊት ቆሙ።
‹‹ ከናንተ ውስጥ ማን ነበር አዛን ሲል የነበረው?›› ረሱል ስዐወ ጠየቋቸው።
ፍርሀት ስላደረባቸው ሁሉም ዝም አሉ።

ዝምታቸውን ያስተዋሉት ነቢይም፦‹‹እንግድያ ማን አዛን እንዳለ ለመለየት እያንዳንዳችሁ በየተራ አዛን በሉ›› አሏቸው። ሁሉም አዛን ካሉ በኋላ የአባ መሕዙራ ተራ ደርሶ አዛን ሲል እሱ መሆኑ ታወቀበት።

‹‹ስምህ ማን ነው?›› አሉት ነቢ ወደሱ ጠጋ ብለው።
‹‹አባ መሕዙራ እባላለሁ›› አለ ፈራ ተባ እያለ።
‹‹የመልአክ ድምፅ ይመስል እየተጠበብክ አዛን ትል የነበርከው አንተ ነህ?›› ነቢ ጠየቁት።

ቅጣቱን ለመቀበል ሲዘጋጅ የነበረው ሙሽሪክ በቅጠቱ ፈንታ ይህንን ልብ የሚማርክ ንግግር ሲሰማ ውስጡ ተናወጠ። ረሱል ሰዐወ ከአላጋጩ እረኛ ፊት ቁመው በጭንቅላቱ የጠመጠመውን ፎጣ ከጭንቅላቱ ላይ አውልቀው ፀጉሩን እየዳበሱ፦‹‹አላህ በረካ ያድርግህ፣ ወደ እስልምናም ልብህን ይምራልህ›› አሉት።

በስብዕናቸው የተማረከው አላጋጩ እረኛም የመልዕክተኛው እጅ ከራስ ቅሉ ሳይወርድ ጓደኞቹ እየተመለከቱ ሸሀዳውን ያዘ።

የድምፁን ውበት የመሰከሩለት ይህን እረኛም ረሱል ሰዐወ ወደ መካ ሂዶ አዛን እንዲል ሾሙት።ከዝያች ቀን አንስቶ ወደ መካ የተመመው ይህ እረኛም የመካ ሙአዚን ሁኖ‹‹ነቢ የዳበሱትን ፀጉር መቼም አልላጨውም›› ሲል ስለት ተሳለ።

መካ ላይ ቁጭ ብሎም እስከ እለተ ሞቱ ድረስ የነቢን ሰዐወ ትዕዛዝ እየፈፀመ ከረመ። ከሱ ህልፈት በኋላም ልጆቹ እና የልጅ ልጆቹ ለ300 አመታት ያህል መካ ላይ አዛን ይሉም ነበር።

Sefwan Ahmedin

ምንጭ፦

سنن النسائي
سنن ابو داود
مسند أمام احمد

ረሱል ሰለላሁ አለይህ ወሰለም 👍🥰
12/08/2024

ረሱል ሰለላሁ አለይህ ወሰለም 👍🥰

12/08/2024

ዘመናት የማይሽረው
የሙሉ ስብዕና ባለቤት
ረሱል ﷺ

Miami Beach ⛱️ Florida USA 🇺🇸💖
12/08/2024

Miami Beach ⛱️ Florida USA 🇺🇸💖

Address

Addis Ababa

Telephone

+251973510566

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Islamic page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share