Liyu Mereja

Liyu Mereja Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Liyu Mereja, Media/News Company, Addis Ababa.

በቦረና እና ጉጂ ዞን የተከሰተው ድርቅና ጉዳቱየኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቦረናና ጉጂ ዝናብ አጠር በሆኑ ቆላማአካባቢዎች የተፈጠረው ድርቅ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል ግብረኃይልበማቋቋም የድጋ...
17/10/2021

በቦረና እና ጉጂ ዞን የተከሰተው ድርቅና ጉዳቱ
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቦረናና ጉጂ ዝናብ አጠር በሆኑ ቆላማ
አካባቢዎች የተፈጠረው ድርቅ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል ግብረኃይል
በማቋቋም የድጋፍ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የክልሉ መንግሥት 100 ሚሊዮን ብር በጀት
በመያዝ የተጠናከረ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን አስውቋል፡፡
በቦረና ዞን 8 ወረዳዎች በጉጂ ዞን ደግሞ 5 ወረዳዎች ወቀቱን የጠበቀ ዝናብ
ባለመዝነቡ ከፍተኛ የመኖ እና ውሃ እጥረት ተከስቷል። ይህም በእንስሳት ላይ
ጉዳት እያስከተለ ነው፡፡
የክልሉ የመስኖ ልማትና አርብቶ አደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሮባ ቱርጬ በዞኑ
የዝናብ እጥረት እንደሚያጋጥም የክልሉ መንግሥት የቅድመ ትንበያ መረጃ
ስለነበረው ከ6 ወራት በፊት ጀምሮ የክትትልና የድጋፍ ሥራ ሲሰራ መቆየቱን
ገልፀዋል፡፡
በዚህም 100 ሚሊየን ብር በጀት ተመድቦ ቢሮው ሲንቀሳቀስ እንደነበረ ነው
ያስረዱት፡፡ ይሁን እንጂ እንደዛም ሆኖ ይጠበቅ የነበረው ዝናብ ሳይዘንብ
በመቆየቱ ችግሩ ሊያጋጥም ችሏል ነው ያሉት፡፡
ያጋጠመው የዝናብ እጥረት ቀጣይነት ሊኖረው የሚችልበት እድል ስላለ
መንግሥት እርሱን ያገናዘበ መልሶ የማቋቋም ሥራ ለመስራት በሚያስችል
አደረጃጀት የድጋፍና ክትትል ሥራዎችን በቀጣይነት ይሰራል ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግሥትም ያጋጠመውን ድርቅ ዘላቂነት ለመፍታት የተቀናጀ ሥራ
እየሰራ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
ልዩ መረጃ!!!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮችለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈሕዝበ ሙስሊሙ ለአገራዊ ለአንድነት ሉአላዊነት እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነት...
17/10/2021

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
ሕዝበ ሙስሊሙ ለአገራዊ ለአንድነት ሉአላዊነት እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነት እና
እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም የኢፌዴሪ የህዝብ
ተወካዮች ምክር ቤት ጥሪ አቅርቧል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
ለ1496ኛው የነብዩ መሐመድ መውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
አስተላለፈ።
ምክር ቤቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ፥ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር
የነብዩን መንገድና አስተምህሮ በመከተል ያጡና የተቸገሩ ወጎኖችን በመደገፍና
በማገዝ ሊሆን ይገባል ነው ያለው።
ሕዝበ ሙስሊሙ ለአንድነቱና ሉአላዊነቱ እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት እና እያደረገ
ያለውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።
"ባለንበት በአዲስ ምዕራፍ እንደ አባቶቻችን ሁሉ የራሳችንን ደማቅ ታሪክ ልንፅፍ
ይገባል" ያለው የምክር ቤቱ መግለጫ ፥ "ይህ የሚሆነውም ጀግኖች አባቶቻችን
በደምና በአጥንታቸው በከፈሉት መስዋዕትነት አንድነቷነና ሉዓላዊነቷን
አስጠብቀው ያስረከቡንን አገር እኛም እንደነሱ ወቅቱ የሚጠይቀው አስፈላጊውን
ትግል በማድረግና መስዋዕትነት በክፈል ታፍራና ተከብራ የቆየች ኢትዮጵያን
ማስቀጠል ስንችል ነው" ብሏል ምክር ቤቱ በመግለጫው።
ኢትዮጵያ የበለፀገችና እውነተኛ ዴሞክራሲ የሚተገበርባት እንድትሆን ሁሉም
በያለበት መስክ የበኩሉን እንዲወጣም ምክር ቤቱ መልዕክት አስተላልፏል።
ልዩ መረጃ!!!

1 ሺህ 496ኛው የመውሊድ በዓል ሰኞ ይከበራል"አገራችንን አማን አላህ ያድርግልን፣ የአውሬ ጸባይ ከሰው ጸባይ ላይ አላህያንሳልን፣ የሚያፈቃቅር የሚያቀራርብ የሚያመካክር ነገር አላህ ይስጠን"...
17/10/2021

1 ሺህ 496ኛው የመውሊድ በዓል ሰኞ ይከበራል

"አገራችንን አማን አላህ ያድርግልን፣ የአውሬ ጸባይ ከሰው ጸባይ ላይ አላህ
ያንሳልን፣ የሚያፈቃቅር የሚያቀራርብ የሚያመካክር ነገር አላህ ይስጠን" ሲሉ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ
ሃጂ ዑመር እድሪስ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
1 ሺህ 496ኛው የነብዩ መሀመድ ልደት (መውሊድ) ከነገ በስትያ ሰኞ ጥቅምት
8 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር
ቤት አስታወቀ።
በዓሉን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የምክር
ቤቱ ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ የእንኳን አደረሳችሁ
መልዕክት አስተላልፈዋል።
"ነቢዩ መሐመድ የተወለዱት መልካም ነገሮችን ሊያስተምሩና መጥፎ ነገሮችን
ደግሞ ሊቃወሙ በመሆኑ መልካም ስራቸውን በማየት በእስልምና እምነት
ተከታዮች ዘንድ መውሊድ ይከበራል" ብለዋል።
በዓሉ ሲከበር የነቢዩ መሐመድን በረከቶች በማስተዋልና መንገዳቸውን በማሰብ
መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።
ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አቅም የሌላቸውን በመጎብኘትና ካለው
በማካፈል እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል።
ተቀዳሚ ሙፍቲው በአገሪቷ ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ገንዘብ በማሰባሰብ
በሠላም ሚኒስቴር በኩል በተዘጋጀ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ መደረጉን
ገልጸዋል።
መንግስት በተለያየ ችግር ላይ ያሉ ዜጎችን መደገፍና ድጋፉም ለተጎዱ
መድረሱን ሊያረጋግጥ እንደሚገባም ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ
አመልክተዋል።
የመውሊድ በዓል የሠላም እንዲሆን መልካም ምኞታቸውንም አስተላልፈዋል።
"አገራችንን አማን አላህ ያድርግልን፣ የአውሬ ጸባይ ከሰው ጸባይ ላይ አላህ
ያንሳልን፣ የሚያፈቃቅር የሚያቀራርብ የሚያመካክር ነገር አላህ ይስጠን" ሲሉ
መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ልዩ መረጃ!!!

"ከሃገር ልማት እስከ እናት ሌማት"ዛሬ በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በ217 ሚሊዮን ብር ወጪ በአዲስ አበባከተማ የተገነባውን ዘመናዊ የዳቦ ፋብሪካ መርቀን ለአገልግሎት ክፍትአድርገናል።ፋብ...
16/10/2021

"ከሃገር ልማት እስከ እናት ሌማት"
ዛሬ በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በ217 ሚሊዮን ብር ወጪ በአዲስ አበባ
ከተማ የተገነባውን ዘመናዊ የዳቦ ፋብሪካ መርቀን ለአገልግሎት ክፍት
አድርገናል።
ፋብሪካውን ቁልፍ ከክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እጅ
ተረክቢያለሁ::
የፋብሪካው መገንባት በዳቦ አቅርቦት እና ፍላጎት አለመጣጣም በኑሮ ውድነት
እየተጎዳ ላለው የከተማችን ማህበረሰብ ታላቅ የምስራች ነው።
በ6 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባው የዳቦ ፋብሪካው በቀን 1 ሚሊዮን ዳቦ
በማምረት አቅም ያለው ሲሆን ለ450 ዜጎች በተለይ ለእናቶች የስራ እድል
ይፈጥራል።
በመሆኑም ክብርት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና ጽህፈት ቤታቸውን
በከተማው ነዋሪ ስም ላመስግን እወዳለሁ።
- ወ/ሮ አዳነች አበቤ
ልዩ መረጃ!!!

በፍጥነት ሼርርር ይደረግ 100%መርዛማ ነዉ ልጆች አዋቂ አዛዉንት ማንምእንዳይጠቀምሲሪስ አፕል ጁስ 100% የተሰኘው ጭማቂ በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታየመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት ምርቱ...
16/10/2021

በፍጥነት ሼርርር ይደረግ 100%መርዛማ ነዉ ልጆች አዋቂ አዛዉንት ማንም
እንዳይጠቀም
ሲሪስ አፕል ጁስ 100% የተሰኘው ጭማቂ በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ
የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት ምርቱን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም
የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን አሳሰበ፡፡
በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰት ማይኮቶክሲን የተሰኘው ከሻጋታ የሚመነጭ
መርዛማ ኬሚካል በሲሪስ አፕል ጁይስ ውስጥ 100% ስለተገኘ ህብረተሰቡ
እንዳይጠቀም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስጠንቅቋል፡፡
ይህ ምርት የዓለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ማስጠንቀቂያ (INFOSAN)
በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርቱ ጥቅም ላይ እንዳይውል ያስጠነቀቀ ሲሆን፥
በተመሳሳይ የሲሪስ አፕል ጁስ 100% አምራች የሆነው የደቡብ አፍሪካ
የምግብና የመጠጥ አምራች ኩባንያ፤ የፍራፍሬ ጭማቂው ማይኮቶክሲን
የተሰኘው ከሻጋታ የሚመነጭ መርዛማ ኬሚካል በውስጡ እንዳለ በመግለጽ
ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው ነው ያሳሰበው፡፡
በመሆኑም ህብረተሰባችን የሲሪስ አፕል ጁይስ 100% ምርት በሀገራች ገበያ
ውስጥ እንዳለ በመገንዘብ ምርቱን እንዳይጠቀም ያስጠነቀቀ ሲሆን÷ ምርቱን
በማንኛውም አጋጣሚ ገበያ ላይ ሲገኝ በፌዴራል ደረጃ በነጻ ስልክ መስመር
በ8482 እንዲሁም በአቅራቢያ ለሚገኙ የክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጥቆማ
እንዲቀርብ ባለስልጣኑ ጠይቋል፡፡

" ደንበኞች በሚበዙበት አካባቢ የፖስ ማሽን የሙከራ አገልግሎት እየተሰጠ ነው "  - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች በሚበዛ...
16/10/2021

" ደንበኞች በሚበዙበት አካባቢ የፖስ ማሽን የሙከራ አገልግሎት እየተሰጠ ነው " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች በሚበዛባቸው አካባቢዎች የሚስተዋለውን መጨናነቅ ለመቀነስ የሚያስችል የፖስ ማሽን የሙከራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አሳውቋል።
የፖስ ማሽን የሙከራ አገልግሎቱ በስራ ላይ የዋለው በአዲስ አባባ በአራቱም ዲስትሪክቶች በሚገኙና ደንበኛ በሚበዛባቸው የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ነው፡፡
በሙከራ ደረጃ አገልግሎት መስጠት የጀመሩት ፖስ ማሽኖች ብዛት 15 ሲሆኑ በቀጣይም አዋጭነታቸው እየታየ ደንበኛ በሚበዛባቸው ማዕከላትና በተመረጡ የንግድ ድርጅቶች፣ ሱፐር ማረኬቶች እንዲሁም ተደራሽ በሆኑ አካባቢዎች አገልግሎቱ የሚሰጥ ይሆናል ብሏል ተቋሙ።
ተጨማሪ ፖስ ማሽኖችን በስራ ላይ ለማዋል ከአቅራቢ ድርጅቶች ጋር የኮንትራት ውል ስምምነት ፈርሞ ማሽኖችን ለማስገባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝም ገልጿል።
በሌላ በኩል ፥ ተቋሙ የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞችን ድካምና እንግልት ለማስቀርትና ካርድ ለማስሞላት የሚያጠፉትን ጊዜ ለማስቀረት በእጅ ስልካቸው አፕልኬሽን በመጫን ኤሌክሪክ ሃይል መሙላት የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል።
ልዩ መረጃ!!!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Liyu Mereja posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share