Werabe MEDIA / ወራቤ ሚዲያ

Werabe MEDIA / ወራቤ ሚዲያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Werabe MEDIA / ወራቤ ሚዲያ, Media/News Company, Addis Ababa.

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ብልካ የስራ ርክክብ አደረጉ!ነሃሴ-27/2016 ስልጤ ዞን ኮሙዩኒኬሽን:የስልጤ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ...
02/09/2024

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ብልካ የስራ ርክክብ አደረጉ!

ነሃሴ-27/2016 ስልጤ ዞን ኮሙዩኒኬሽን:
የስልጤ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ የሾማቸው አቶ ዘይኔ ብልካ ከቀድሞው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል።

አቶ ዘይኔ ብልካ ከቀድሞው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር የስራ ርክክ በፈጸሙበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልማትና በመልካም አስተዳደር የተያዙ ውጥኖችን ከዳር ለማድረስ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በዞን አስተባባሪዎች የተጀመረውን የሪፎርም ስራ በሁሉም መዋቅሮች በማካሄድ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ጥረት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

የዞኑን ህዝብና ሌሎች አከባቢዎች የሚኖሩ የስልጤ ተወላጆችን አንድነት በስልጤ ልማት ማህበር አማካኝነት በማስተሳሰር የዞኑን ልማት ለማፋጠን የጀመሩ እንቅስቃሴዎችን በማጠናከር እንደሚሰራም አቶ ዘይኔ ተናግረዋል።
የዞኑን የኢንቨስትመንት አቅሞችን ማስተዋወቅና ባለሀብቶችን መሳብ፣በየደረጃው የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ ማድረግ ሌላኛው የመንግስታቸው የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነም አቶ ዘይኔ አብራርተዋል።

አቶ ዘይኔ ብልካ በምክር ቤት እንደተሾሙ በዞኑ በጎርፍ የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመጎብኘት ስራቸውን በይፋ መጀመራቸው የሚታወስ ነው።

የቀድሞው የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር በበኩላቸው በቀጣይ የዞኑ አስተዳደር በሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ስልጤ ዞን : የጎርፍ አደጋ    | በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ስልጢ እና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች በሚገኙ ከፍተኛ ስፍራዎች ከባድ ዝናብ በሚጥልበት ወቅት የሚፈጠረው ጎርፍ ማረቆ ወ...
27/08/2024

ስልጤ ዞን : የጎርፍ አደጋ

| በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን ስልጢ እና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች በሚገኙ ከፍተኛ ስፍራዎች ከባድ ዝናብ በሚጥልበት ወቅት የሚፈጠረው ጎርፍ ማረቆ ወረዳን አቋርጦ በኦሮሚያ ክልል በመቂ አልፎ ወደ ዝዋይ ሀይቅ ይቀላቀል ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ለመስኖ በሚል በማረቆ ወረዳ ከዓመታት በፊት የተሰራው የመስኖ ግድብ በከፍተኛ ደለል በመሞላቱ ምክንያት ውሃው መውራጃ ሲያጣ በአካበቢው እየተፈጠረው ያለው የጎርፍ አደጋ ጉዳት እያስከተለ ይገኛል፡፡

ሰሞኑን ስልጤ ዞን ስልጢ እና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች ከ6 ቀበሌዎቸ በላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ እስከሁን ከ9 መቶ በላይ ቤቶች በጎርፍ ሲዋጡ፤ ከ6 ሺህ በላይ ዜጎች ለከፋ አደጋ ተጋልጠዋል፡፡

የስልጤ ዞን ኮሚኒኬሽ ሃላፊ አቶ ሳሊ ሃሰን በተለይም ለኢቢሲ ሳይበር አንዳሉት በአደጋው ምክንያት ከ1200 ሄክታር በላይ የበቆሎ፣ ስንዴ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ እና ቡና ምርት ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኗል፡፡

Mumera  ማኑፋክቸሪንግ ለክረምቱ ፍቱን መድሃኒት ይዞ መተዋል አለን ይጎብኙን !!በቀን እስከ 1000 ልብሶችን ማምረትም እንችላለን ዕርሶ ብቻ ይዘዙን 💃¶_የተለየዩ የስፌት ስራዎችን ይዘዙ...
17/07/2024

Mumera ማኑፋክቸሪንግ ለክረምቱ ፍቱን መድሃኒት ይዞ መተዋል አለን ይጎብኙን !!
በቀን እስከ 1000 ልብሶችን ማምረትም እንችላለን ዕርሶ ብቻ ይዘዙን 💃

¶_የተለየዩ የስፌት ስራዎችን ይዘዙን በፍጥነት በሚፍልጉት መልኩ ሰርተን እናስረክባለን!!
¶_አልባሳትም እየመጣቹህ ግዙን በማሳያ ሱቆቻችን ይገኛሉ

እንዲሁም ጥራታቸውን የጠበቁ ሸሚዞችን አምርተን ለገበያ አቅርበናል! ይዘዙን🤙

ማሳያ መዓከሎቻችን
📍ቤቴል ፖስታ ቤት አጠገብ ከሚገኘው ህንፃ ምድር ላይ
📍 ቀራኒዮ ቤተክርስቲያን አጠገብ እንገኛለን

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁ0909599091/0912707778
ይደውሉልን እንዲሁም በቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ በመሆን ምርቶቻቻን ገብተው ይጎብኙ ይዙዙን የፍጠነ ባሉበት እናደርሳለን!!
https://t.me/mumerafashion

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Werabe MEDIA / ወራቤ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share