01/04/2024
እለቱ እሁድ ነው።
ብዙ ሰው አለባበሱ ዘና ያለ ነው።
ወንዶች ቱታ በሸበጥ ወይም ሸራ መሳይ ስኒከር ተጫምተው ሲንቀሳቀሱ ይስተዋላሉ።
ሴቶች ደግሞ ከሌሊት ልብስ መለስ ያሉ፣ ደረታቸው ከፈት ያለ ጉርድ ቀሚሶችን በብዛት ያለ ጡት መያዣ ለብሰው ከታች ነጭ ካልስ በሸበጥ ተጫምተው ሞንደል ሞንደል ሲሉ ይውላሉ። የተሰሩት ሹርባ እንዳይፈርስ አልያም የተቀቡት ቅባት በፀሀይ እንዳይቀልጥባቸው አናታቸውን በሻሽ ሸብ የሚያደርጉም ብዙ ናቸው። ሴቶች በእረፍት ቀናቸው የውስጥ ቁምጣ እንደማይለብሱም ይታማሉ።
አሁን በዚህ ሰሞን አንድ እሁድ እኛ ሰፈር የካ አባዶ ATM ለመጠቀም ጥቁር ቱታ ሱሪ በነጭ ሸሚዝ ለብሼ ሶሉ ነጭ የሆነ ጥቁር እስኒከሬን ተጫምቼ፣ በእጄ ላይ ደግሞ ከዱባይ የመጣልኝን ወርቃማ የብረት ሰዓቴን ገርግጄ፣ በጠዋት ሻወር የረሰረሰውን ፀጉሬን በፀሀይ እያሞቅሁ ወደ ባንክ አቀናሁ።
በመጀመሪያ ያገኘሁት አዋሽ ባንክ ሁለት ATM ማሽኖቹ ቢኖሩትም ከአገልግሎት ውጪ ሆነው አገኘኋቸው፣ ብዙ ሰው በአይኑ ገልመጥ እያደረግ This ATM Machin is out of service ከሚለው ፅሁፍ ጋር ፊት ለፊት እየተጋጨ ፊቱን ቅጭም እያደረገ ይመለሳል። እኔም የካ አባዶ በተለይ እሁድ እሁድ የሚሰራ ATM ማሽን ማግኘት ከባድ እንደሆነ ስለማውቅ ብዙም ሳይገርመኝ ወደ ቀጣዩ ማሽን አመራሁ።
ዘቅዘቅ ብዬ 50 ሜትር የሆነ ርቀት ከተጓዝኩ በኋላ አስፋልት ተሻግሬ ወደ ዳሽን ባንክ ATM አቀናሁ።
ዳሽንም በተመሳሳይ ሁኔታ ከአገልግሎት ውጪ መሆኑን በፈረንጅ አፍ ፅፎ የእሁድ እረፍቱን እያጣጣመ ነው።
ይህም አልደነቀኝ። የያዝኩት የአቢሲኒያ ATM ስለነበር ለምን ወደ ባለቤቱ አልሄድም ብዬ ከG7 ባንኩ ወዳለበት 500 ሜትር የሚሆን የቁልቁል ተጓዝኩ።
ፀሀዩ የሻወር ውሀዬን ከማድረቅ አልፎ ሌላ ውሀ ከሰውነቴ እስከማመንጨት ደርሷል። ATM ማሽኑ ጋር ስደርስ አንድ ሰው ብር አውጥቶ ሲመለስ፣ አንድ ሰው ደግሞ ማሽኑን እየሞከረ አገኘሁት። ማሽኑ በመስራቱ እና ወረፋማም ባለመብዛቱ ወደ ውስጤ እፎይ ብዬ አንዱን የበረንዳ ቋሚ ብረት ተደግፌ ቆምኩ።
ትንሽ ቆይቼ አይኔን ወደ ማሽኑ ስልክ እየሞከረ ያለው ሰው ተጨናንቆ አየሁት። ጠጋ ብዬ ምነው አይሰራም እንዴ? ስል ጠየኩት
እሱም ኧረ ይሰራ ነበር፣ ከኔ በፊት የነበረው አውጥቶ ሄዷል። የኔን ካርድ ግን ጎረሰብኝ አለኝ።
ጠጋ ብዬ ስመለከት ማሽኑ ከወትሮው በተለየ መልኩ ካርዱን ሙሉ በሙሉ ሳይወስድ አብዛኛውን አካሉን ውጦ ጫፉ ይታያል።
በብረት አጣብቀን ለማውጣት እየሞከርን ሌላ ልጅ እግር መጣ፣ ልጁም ፣አይሰራም!? ብሎ ፊቱን ቅጭም አድርጎ ጠየቀን፣ ከጥያቄውና ከፊቱ ብዙ እንደዞረና እንደተበሳጨ ያስታውቃል።
አይ! ይሰራል ብለን የገጠመንን ነገርነው፣ ጠጋ ብሎ አየውና፣ መርፌ ብናገኝ አሪፍ ነበር አለና ባገኘው ነገር ወይ ወደ ውስጥ ለመግፋት ከቻለ ለማውጣት ይሞክር ጀመር።
ከዚያ ባለቤቱ ፈንጠር ብሎ ሄደና መርፌ ገዝቶ መጣ፣ ልጅ እግሩ ተጠቃሚ በመርፌ ሙከራውን ቀጠለ።
ሶስታችን ሀሳብም እየተለዋወጥን፣ በመርፌውም እየሞከርን አንዲት ከላይ እንደገለፅኩት የእሁድ ልብስ የለበሰች ሴት ሞንደል ሞንደል እያለች መጣች
እሷም ወይኔ! ይሄም አይሰራም ስትል፣
ሁለቱ ካርዱን ለማውጣት ወይ ለማስገባት ሙከራ ላይ ስለነበሩ፣ አይ! ይሰራል፣ አንድ ሰው አውጥቶ ሄዷል፣ ከሱ ቀጥሎ ያለው ሲሞክር ካርዱን ጎርሶበት ነው አልኳት።
ይህን ሳስረዳት ፊት ለፊት እየተያየን ስለነበር እስከ ደረቷ በተገለጠው ስስ ልብሷ የጡቷ ማካፈያ ሸለቆ ሙሉ በሙሉ፣ ጡቶቿ ደግሞ በከፊል ይታዩኛል።
እስኪ እኔ ልሞክር ብላ ወደ ማሽኑ ስትራመድ ደግሞ የውስጥ ቁምጣ እንዳለበሰች የሚያሳብቀው ስስ እና አጭር ቀሚሷ ዳሌዋን ጎላ አድርጎታል። ያንን ዳሌ ክፉኛ እያበሳጨችው ሄደች።
ጎንበስ ብላ በመርፌው ካርዱን ለማውጣት ወይ ለማስገባት ስትሞክር ደግሞ ዳሌዋ ምን አባህ ታየኛለህ በሚመስል ግልምጫ አፈጠጠብን።
ባቷ እንደተወለወለ የክላሽ ሰደፍ ያበራል፣ ብር ለማውጣት ከፍተኛ ጉጉት እንዳላት ያስታውቃል። እያገላበጠችና እየተገላበጠች ሞከረች፣
በመርፌው አልሳካ ሲላት በተቀጠለው ጥፍሯ፣ ጥፍሩ እንኳን የእሷ አይደለም፣ በውበት ባለሙያዎች እገዛ የተቀጠለላት ሰው ጥፍር እንደሆነ ያስታውቃል፡፡
በዚህ ጥፍሯ ሞከረች፣ የህመም ስሜት ሲሰማት፣ አይኗን ስልምልመ አድርጋ፣ ውይ! ብላ ጣቶቿን ወደ አፏ ከታ ዘገም ባለ አላላስ የማቀዝቀዝ አገልግሎት ሰጠችው፣ ወጣ ገባ ስታደርገው ጣት ሳይሆን ሌላ ነገር እያስገባች፣እያስወጣች ይመስላል፡፡
ቀጠለችና በመርፌው ሙከራዋን ቀጠለች፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ ተሳካላት፣ ካርዱ ወደ ውስጥ ገባላት። ዋው ብላ ዘለለች። ያን ጊዜ የሸበጧ ድምፅ ለጆሯችን ደረሰ፣ አይናችን ደግሞ ስትዘል ክፉኛ የሚበሳጨውን ዳሌዋን ተሳለመ።
በዚህ ጊዜ የተጠቃሚዎች ቁጥር ጨምሯል። መጀመሪያ እሷ አወጣች፣ ቀጥሎ እኔ ነበርኩ ተረኛ፣ ዳሩ ግን ያንን የሚበሳጭ ዳሌ በደንብ ለማየት ካለኝ ጉጉት ገንዘቧን ይዛ ስትመለስ እስከ አስፋልቱ በአይኔ ሸኘኋት።
አንድ ሰው ካወጣ በኋላ፣ ጀለስ አታወጪም እንዴ ካልሆነ እኛ እናውጣ ሲል አንዱ ከኋ ያለ ተጠቃሚ በማጉረምረም ድምፅ አባነነኝ፣ እኔም ከእንቅልፉ እንደባነነ ጡት የሚጠባ ህፃ ብንን ብዬ በመስገብገብ ስሜት ተንደርድሬ ካርዴን ማሽ ላይ ሰካሁት፡፡
ልቤ እየተበሳጨ በሄደው ዳሌላ ልቡ ተሰቅሎ፣ ያንን በሸለቆ የተከፈለ ጡት እያስታወስኩ፣ ብሬን አውጥቼ ሄድኩ።
ብሬን እየቆጠርኩኝ፣ ልጅቱን እያሰብኩኝ ወደ ቤቴ ስመለስ የአባዶ ATM አገልግሎት እያብከነከነኝ ቤቴ ደረስኩ
አባዶ ATM ማሽን ላይ ቆሞ የራሱን ገንዘብ ለማውጣት የሚፀልየውን ሰው በተደጋጋሚ ስታዘብ ባንኮች የሚሰጡን የራሳችንን ገንዘብ ሳይሆን የራሳቸውን ገንዘብ እየመፀወቱን ሲመስለኝ ድፍን ሁለት አመት ሞላኝ።